Get Mystery Box with random crypto!

Ewnet Media

የቴሌግራም ቻናል አርማ ewnetmedia1 — Ewnet Media E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ewnetmedia1 — Ewnet Media
የሰርጥ አድራሻ: @ewnetmedia1
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.06K

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2023-04-20 11:59:18 መንግስት በሱዳን የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ሁኔታ በቅርበት እየተከታተለ መሆኑን አስታወቀ

የኤፌዴሪ መንግሥት በሱዳን ባለው ወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታ ምክንያት በሀገሪቱ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን ሁኔታ በቅርበት እየተከታተለ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በዋናው መስሪያ ቤት እና ካርቱም በሚገኘው የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ኤምባሲ አማካኝነት የኢትዮጵያውያንን ደኅንነት ለመጠበቅ እየሠራ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የሚመለከታቸው ሴክተር መስሪያ ቤቶች እና አጎራባች ክልሎች አባል የሆኑበት ግብረ ኃይል በሀገር አቀፍ ደረጃ መቋቋሙም ነው የተመለከተው፡፡

አስፈላጊ መረጃዎችን በቀጣይ እንደሚያሳውቅም ነው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የገለጸው፡፡
212 views08:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 11:33:43 የዒድ አልፈጥር በዓል መቼ ነው ?

የፌዴራል ጠቅላይ ሼሪዓ ፍርድ ቤት ፥ የዒድ አልፈጥር በዓል ጨረቃ ዛሬ ሀሙስ ማታ ከታየች ነገ፣ ካልታየች ደግሞ ቅዳሜ ይከበራል ሲል አሳውቋል።

ይህ ያለው ዛሬ በሰጠው መግለጫ ነው።

1 ሺህ 444ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል ፤ ለኢትዮጵያና ለመላው ዓለም ህብረተሰብ የሰላም፣ የደስታና የፍቅር እንዲሆን መልካም ምኞቱን የገለፀው ሼሪዓ ፍርድ ቤቱ ሙስሊሙ ህብረተሰብ በዓሉን ሲያከብር ያጡና የተቸገሩ ወገኖችን በማሰብና በመርዳት እንዲሆን ጥሪ አቅርቧል።

#ኤፍቢሲ
213 views08:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-18 21:39:48 በሱዳን ውጊያ ኢትዮጵያውያን መሞታቸው ተገለጸ

በሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ በውጊያው ኮሞቱ መካከል ኢትዮጵያዊን እንደሚገኙበት መረጃዎች እየደረሱኝ ነው ብሏል። በሱዳን ጦርና ፈጥኖ ደራሽ መካከል በተፈጠረው ውጊያ ከ200 በላይ ሰዎች መሞተቸው ተነግሯል።

በሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ፤ በሱዳን እየተካሄደ ባለው ውጊያ በርካታ ሲቪሎች ለጉዳት መዳረጋቸውና ህይወትም እየተቀጠፈ መሆኑን ገልጿል።

ከእነዚህ መካከል ኢትዮጵያውያን እንደሚገኙበት መረጃዎች እንደደረሱት አመልክቷል።

ኤምባሲው ምን ያህል ኢትዮጵያውያን እንደሞቱ እና እንደተጎዱ በዝርዝር አልገለፀም።

ነገር ግን በኢትዮጵያውያን ሞት እና ጉዳት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን እደተሰማው እና ለሟች ቤተሰቦች እና ወዳጅ ዘመዶቻቸው መፅናናትን ተመኝቷል።

" ይህን አስቸጋሪ ጊዜ ለማለፍ ኢትዮጵያዊን የተቻላቸውን ሁሉ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ በድጋሜ እናሳስባለን " ብሏል።

መረጃ ለመለዋወጥ እና ለምክክር የኤምባሲው ባልደረባ የሆኑትን አቶ ነጅብ አብደላ በስልክ ቁጥር +249911646547 ማነጋገር እንደሚቻል በሱዳን ካርቱም የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ አሳውቋል።
324 views18:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-18 20:28:52 #SUDAN

በሱዳን የEU አምባሳደር ጥቃት ተፈፀመባቸው።

በሱዳን ካርቱም ሚገኙት የአውሮፓ ህብረት (EU) አምባሳደር በመኖሪያ ቤታቸው ጥቃት እንደተፈፀመባቸው ተሰማ።

አምባሳደሩ ጥቃት እንደተፈፀመባቸው ያሳወቁት የአውሮፓ ህብረት ከፍተኛ ዲፕሎማት ጆሴፕ ቦሬል ናቸው (በትዊተር ገፃቸው)።

ቦሬል ስለ ጥቃቱ ምንም አይነት ዝርዝር ነገር ባይገልጹም አምባሳደሩ ግን " ደህና ናቸው " ብለዋል።

የዲፕሎማቲክ ቦታዎችን እና ሰራተኞችን ደህንነት ማስጠበቅ የሱዳን ባለስልጣናት ቀዳሚ ኃላፊነት ነውም ሲሉ ገልጸዋል።

ምንም እንኳን ቦሬል ፤ በሱዳን የአውሮፓ ህብረት አምባሳደርን ስም ባይፅፉም ስማቸው አይዳን ኦሃራ የሚባሉ ሲሆን የ
#አየርላንድ ዲፕሎማት ናቸው።

ቦሬል ካርቱም ውስጥ የተፈፀመው ጥቃት ፤ በሌሎች ሀገራት የሚሰሩ ዲፕሎማቶች ጥበቃን የሚደነግገውን የተመድ ስምምነት የ " ቪይና ኮንቬንሽን " በእጅጉ የጣሰ ነው ብለዋል።

በሌላ በኩል ፥ የአውሮፓ ህብረት ቃል አቀባይ ናቢላ ማስራሊ ለAFP በሰጡት ቃል " የሰራተኞች ደህንነት ቅድሚያ የምንሰጠው ጉዳይ ነው " ብለዋል፤ የተፈፀመውን ጥቃት ተከትሎ የአውሮፓ ህብረት ልዑካን ቡድን ከካርቱም እንዲወጣ እንዳልተደረገ ተናግረዋል።

ቃል አቀባይዋ ፤ በሱዳን ያለው የፀጥታ እና ደህንነት ሁኔታ እየተገመገመ ነው ብለዋል።
295 views17:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-18 00:08:26 #Sudan

በሱዳን የአሜሪካ ኤምባሲ ተሽከርካሪ በጥይት ተደበደበ።

በሱዳን የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ብረት ለበስ ተሽከርካሪው " ሆን ተብሎ " በጥይት መደብደቡን አስታወቀ።

ድርጊቱን የፈፀመው ሄሜቲ የሚመሩት RSF ቡድን መሆኑን ኤምባሲው ለአል አረቢያ ገልጿል።

ኤምባሲው ተሽከርካሪው በ100 ጥይት መደብደቡን ገልጾ ድብደባው ያደረሰው ምንም ጉዳት የለም ብሏል።

በሌላ በኩል ፤ የአሜሪካ መንግሥት ጦርነት ውስጥ ካለችው ሱዳን ዜጎቹን የማስወጣት እቅድ እንደሌለው ዋይትሃውስ አሳውቋል።
301 views21:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-17 18:16:24 ማስታወቂያ!!

የተባበሩት ኤምሬትስ የሰጠውን ስኮላርሽፕ እየተጠባበቃችሁ ላላችሁ ተማሪዎች ሁሉ
የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ መንግስት በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስደው ጥሩ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች ነፃ የትምህርት ዕድል ለመስጠት በፈቀደው መሰረት ቀደም ሲል በተማሪዎች ቃል የተገባላችሁ ተማሪዎችና በዕድሉ ለመጠቀም ፍላጎት ያላቸው ተማሪዎች Application Form link:
http://survey.ethernet.edu.et/index.php/518562?lang=en --
በመግባት ከዛሬ 09/08/15 ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 5 ቀናት ከላይ በተቀመጠው ሊንክ በመግባት፡-
1.  የ12ኛ ክፍል የማትሪክ ውጤት ኮፒ (Grade 12 Result) copy
2.  ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ኮፒ (Grade 9-12 transcript) copy
3.  CV/ Curriculum Vitae copy
4.  የልደት የምስክር ወረቀት ኮፒ (Birth Certificate) copy እና ሌሎች በሊንኩ የተጠቀሱ መረጃዎችን  እንድትሞሉ እናሳስባለን ።
መረጃዎች ተጣርተው ለፈተና የሚቀረቡ ተማሪዎችን ስም ዝርዝር በቀጣይ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች የምናሳውቅ መሆናችንን እንገልጻለን።

የኢፌዲሪ ትምህርት ሚኒስቴር
290 views15:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-17 14:52:20 በሱዳን ጦርነት የሞቱ ሰዎች ቁጥር 97 ደረሰ

በሱዳን ጦርነት ምክንያት ህይወታቸው ያለፈ ንጹሃን ሰዎች ቁጥር 97 መድረሱ ተገለፀ።

የሱዳን ዶከተሮች ኮሚቴ በጦርነቱ የተጎዱ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን ያስታወቀ ሲሆን፤ እስካሁን ከ365 በላይ ሰዎች መቁሰላቸው ተነግሯል።

በሱዳን ጦር እና በፈጥኖ ደራሽ ኃል መካከል የተቀሰቀሰው ጦርነት ለ3ኛ ቀን ተባብሶ መቀጠሉ ታውቋል።
259 views11:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-16 22:14:34 የሱዳን ጦር እና ፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ አስቸኳይ የተኩስ አቁም ሊያደርጉ ይገባል

የአፍሪካ ኅብረት

ጦርነት ውስጥ የገቡት የሱዳን ጦር እና ፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች /ልዩ ኃይሎች/ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ አስቸኳይ የተኩስ አቁም እንዲያደርጉ የአፍሪካ ኅብረት የሰላም እና ፀጥታ ምክር ቤት አሳሰበ።

ምክር ቤቱ በሱዳን ወቅታዊ ጉዳይ ላይ በዛሬው ዕለት መክሯል፤ በዚህም የሱዳን ሕዝብ ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱ ወደ ነበረበት እንዲመለስ እና በሲቪል መራሽ መንግሥት ለመተዳደር ያቀረበውን ጥያቄ እና ለዚሁ የሚደረግን ጥረት እንደሚደግፍ ገልጿል።

ለሱዳን ሕዝብ ሉዓላዊነት እና ፖለቲካዊ አመለካከት ነፃነት እንዲሁም የሀገሪቱ የግዛት አንድነት መከበር እና ቀጣይነት ድጋፉን ዳግም አረጋግጧል። በሱዳን ጦር እና በፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች መካከል የተቀሰቀሰው ጦርነት በእጅጉ አሳሳቢ መሆኑን የገለጸው ምክር ቤቱ፣ ነገሩ ወደ ከፍተኛ ቀውስ ሊሸጋገር እንደሚችልም አሳስቧል።

በሁለቱ ኃይሎች መካከል የተጀመረው ጦርነት በሀገሪቱ ዴሞክራሲያዊ እና ሰላማዊ ሽግግር ለማድረግ የተጀመረውን ጥረት ሊያደናቅፍ ይችላል ሲልም ስጋቱን ገልጿል። በጦርነቱ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ ዕርዳታ ሠራተኞችን ጨምሮ በሰላማዊ ሰዎች ላይ ሞት እና የአካል ጉዳት እንዲሁም የንብረት ውድመት ማስከተሉን ገልጾ ድርጊቱን በጥብቅ እንደሚያወግዘው አስታውቋል።
288 views19:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-16 16:57:22 በካርቱም የሞቱ ሰዎች ቁጥር ወደ 56 ከፍ ማለቱ ተገለጸ

ትናንት በሱዳን በሀገሪቱ ጦር እና አርሴስኤፍ ሀይሎች መካከል የተጀመረው ውጊያ አዳሩንም ቀጥሏል።

ይህን ተከትሎም የሀገሪቱ ዶክተሮች ኮሚቴ እንደገለጸው በጦርነቱ ምክንያት እስካሁን በካርቱም የሟቾች ቁጥር ወደ 56 ከፍ ብሏል።

የሱዳን ጦር እና የፈጥኖ ደራሽ ኃይል መካከል በትናትናው እለት የተከሰተውን ግጭት ትክተሎ በሁለቱም ወገኖች በርካታ የሰራዊት አባላትም ሞተዋ የተባለ ሲሆን፤ ከ600 ገደማ ሰዎች መቁሰላቸውን የሱዳን ዶክተሮች ማእከላዊ ኮሚቴን አስታውቋል።
282 views13:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-15 20:29:20 የፈጥኖ ደራሽ ሃይሉ ከካርቱም ካልወጣ ተጨማሪ ጦር ከክልሎች እናስገባለን

ጀነራል አልቡርሃን

የሱዳን ጦር መሪው አብዱልፈታህ አልቡርሃን ጀነራል ሃምዳን ዳጋሎ የሚመሩት ሀይል ከካርቱም እንዲወጣ አሳስበዋል።

ጀነራል አልቡርሃን የፈጥኖ ደራሽ ሃይሉ በፍጥነት ከካርቱም እንዲወጣ ነው ያስጠነቀቁት።

የዳጋሎ (ሄሜቲ) ሃይል በጥፋት መንገዱ ከቀጠለ ግን ተጨማሪ ወታደሮችን ከክልሎች አስገብተን እርምጃ ለመውሰድ እንገደዳለን ብለዋል።

ጀነራል ሃምዳን ዳጋሎ በበኩላቸው “ቀድመን የተወጋነው እኛ ነን፤ አልቡርሃንን ለፍትህ ሳናቀርብ ትግላችን አናቆምም” ማለታቸው በአር ኤስ ኤፍ የትዊተር ገጽ ላይ ሰፍሯል።
110 views17:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ