Get Mystery Box with random crypto!

Ewnet Media

የቴሌግራም ቻናል አርማ ewnetmedia1 — Ewnet Media E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ewnetmedia1 — Ewnet Media
የሰርጥ አድራሻ: @ewnetmedia1
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.06K

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 9

2023-04-06 00:59:32 የጀማ ድልድይ ባልታወቀ ምክንያት መደርመሱ ተሰማ

በሰሜን ሸዋ ዞን እንሳሮ ወረዳ እንሳሮ እና መራሐቤቴን የሚያገናኘው አገር አቋራጭ የጀማ ድልድይ በቀን 27/7/2015 ዓ.ም ሁለት ሲኖ ትራክ ተከታትለው ሲሆዱ አንዱ ሲኖ ትራክ የውሃ መያዣ ቦቴ የጫነ ሲሆን አደኛ በዶውን ሲጓዝ ባልታወቀ ምክንያት ድልድዩ ሊደረመስ ችሏል።

ከአዲስ አበባ - ሙከጡሪ አለም ከተማ - ደጎሎ መስመር ከሙከጡሪ 72.3 ኪ.ሜ. እርቀት ላይ የሚገኘው የጀማ ወንዝ ድልድይ ከተወሰነላቸው የክብደት መጠን በላይ በጫኑ ከባድ ተሽከርካሪዎች ሳቢያ ጉዳት ደርሶበታል ሲል የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር አስታዉቋል።

በመሆኑም ይህ ድልድይ በአሁኑ ወቅት ለተሽከርካሪዎች አገልግሎት መስጠት የማይችልበት ደረጃ ላይ መሆኑን ብስራት ከአስተዳድሩ ካገኘዉ መረጃ ተመልክቶታል።

ይህንን ድልድይ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለአገልግሎት ለማብቃት እንዲያስችል አስፈላጊውን የጥገና ሰራ በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የሚከናወን መሆኑንም ገልጿል ። በመሆኑም የዚህ መስመር ተጠቃሚዎች ለድልድዩ አስፈላጊውን የጥገና ስራ ተከናውኖ ለአገልግሎት እስኪበቃ ድረስ ሌሎች አማራጮችን እንድትጠቀሙ አስተዳድሩ አሳስቧል።
67 views21:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-05 17:01:30 በአዲስ አበባ የጎዳና ላይ ኢፍጣር ለ3ኛ ጊዜ እንደሚካሄድ ተገለጸ

የጎዳና ላይ ኢፍጣር የፊታችን ቅዳሜ መጋቢት 30 ቀን ለ3ኛ ጊዜ እንደሚካሄድ ተገለጸ።

የጎዳና ላይ ኢፍጣሩ “ኢፍጣራችን ለወገናችን” በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ እንደሚካሄድም ተጠቁሟል፡፡
150 views14:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-05 12:13:05
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር 27 አባላት ያሉትን ካቢኔ ይፋ አደረገ

በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው አዲሱ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር 27 አባላት ያሉትን ካቢኔ ይፋ አደረገ። በአዲሱ ካቢኔ ሌተናል ጄነራል ታደሰ ወረደ የክልሉ ምክትል ፕሬዝዳንት እንዲሁም የሰላም እና ጸጥታ ካቢኔ ሴክሬተሪያት ኃላፊን ሆነው የተሾሙ ሲሆን፤ ሌተናል ጄነራል ጻድቃን ገብረትንሳኤ ደግሞ በምክትል ፕሬዝዳንት ማዕረግ ያልተማከለ አስተዳደር እና ዴሞክራታይዜሽን ካቢኔ ሴክሬተሪያት ኃላፊ ሆነዋል።

ከተቋቋመ ሁለት ሳምንት ያስቆጠረው የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የካቢኔ አባላቱን በይፋ ያስተዋወቀው ዛሬ ረቡዕ መጋቢት 27፤ 2015 በመቐለ ከተማ ባካሄደው ስነስርዓት ነው። በዚህ ስነ ስርዓት ላይ የክልሉን መንግስት ሲመራ የነበረው የቀድሞ ካቢኔ፤ የአስፈጻሚነት ስልጣኑን በጊዜያዊ አስተዳደሩ ለተቋቋመው አዲሱ ካቢኔ አስረክቧል።

አዲሱ ካቢኔ የተዋቀረው ከህወሓት፣ ከትግራይ ኃይሎች፣ ከምሁራን እና ከብሔራዊ ባይቶ አባይ ትግራይ (ባይቶና) ፖለቲካ ፓርቲ የተውጣጡ አባላትን በማካተተት ነው። የካቢኔው 51 በመቶ ቦታ የተያዘው በህወሓት ሲሆን፤ ተቃዋሚው ባይቶና ፓርቲ ሁለት ቢሮዎችን በኃላፊነት የመምራት ዕድል አግኝቷል። ከትግራይ ኃይሎች በካቢኔው ውስጥ የኃላፊነት ቦታ ያገኙት ሌተናል ጄነራል ታደሰ ወረደ፣ ብርጋዴር ጄነራል ተኽላይ አሸብር፣ ሌተናን ጄነራል ፍሰሃ ኪዳኑ እና ሜጀር ጄነራል ዘውዱ ኪሮስ ናቸው።
178 viewsedited  09:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-04 10:30:01
#NewsAlert

ዶ/ር ጫላ ዋታ ያለመከሰስ መብታቸው ተነሳ።

የቡሌሆራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዜዳንት የነበሩት ዶ/ር ጫላ ዋታ የመንግስት ግዥ ህግ ከሚፈቅደው አሰራር ውጭ በሰሩት ስራ ያለመከሰስ መብታቸው ተነስቷል።

ምክር ቤቱ በአንድ ድምፀ ተአቅቦ በአብላጫ ድምፅ ነው ያለመከሰስ መብታቸው የማንሳት ውሳኔን ያፀደቀው።

አንድ ድምፀ ተአቅቦ ያደረጉት እራሳቸው ዶ/ር ጫላ ዋታ ናቸው።

(ዝርዝር ይኖረናል)
211 viewsedited  07:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-04 09:44:46
#NewsAlert

ወ/ሮ ሌሊሴ ደሳለኝ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዜዳንት ሆነው ተሾሙ።

የህ/ተ/ም/ቤት የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሹመትን በሁለት ድምፀ ተአቅቦ በአብላጫ ድምፅ አፅድቋል።
199 viewsedited  06:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-04 09:22:21
የአድማስ ሎተሪ እጣ መደብ ቁጥር 009 አሸናፊ እጣ ቁጥሮች ይፋ ሆነዋል!!

9ኛው ዙር የአድማስ ሎተሪ የሽልማት መጠን ወደ 3 ሚሊየን ከፍ ብሎ በትናንትናው እለት እጣው ወጥቷል።

1ኛ እጣ ሶስት ሚሊየን ብር የሚያስገኘው እጣ ቁጥር 0091844739

2ኛ እጣ 1 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር የሚያስገኘው እጣ ቁጥር 0090540530

3ኛ እጣ 8 መቶ ሺሕ ብር አሸናፊ እጣ ቁጥር 0092021699

4ኛ እጣ 4 መቶ ሺሕ ብር አሸናፊ እጣ ቁጥር 0090412316

5ኛ እጣ 2 መቶ 50 ሺሕ ብር አሸናፊ ቁጥር 0092260801

6ኛ እጣ 1 መቶ 50 ሺሕ ብር አሸናፊ እጣ ቁጥር 0090567816

7ኛ እጣ 1 መቶ ሺሕ ብር አሸናፊ እጣ ቁጥር 0091588711

8ኛ እጣ 50 ሺሕ ብር አሸናፊ እጣ ቁጥር 0090361764

9ኛ እጣ 30 ሺሕ ብር አሸናፊ እጣ ቁጥር 0090947970

10ኛ እጣ 25 ሺሕ ብር አሸናፊ ቁጥር 0090876951 በመሆን ወጥቷል፡፡
182 viewsedited  06:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-03 20:31:42 የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ ዋጋ እስከ ሚያዚያ 30 ቀን 2015 ድረስ ባለበት ይቀጥላል

የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ ዋጋ እስከ ሚያዚያ 30 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ በመጋቢት ወር ሲሸጥበት በነበረው ዋጋ እንዲቀጥል ተወሰነ።

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ለኢቢሲ በላከው መግለጫ፣ እስከ ሚያዚያ 30 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ የሁሉም የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ የመሸጫ ዋጋ በመጋቢት ወር ሲሸጥበት በነበረው ዋጋ እንዲቀጥል ተወስኗል።
192 views17:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-03 12:19:39 ነዳጅ ላኪ ሀገራት አቅርቦት ለመቀነስ መወሰናቸውን ተከትሎ የነዳጅ ዋጋ ጨምሯል!

የዓለማችን ግዙፍ ነዳጅ ላኪ ሀገራት ያልተጠበቀ የምርት ቅነሳን ይፋ ካደረጉ በኋላ የነዳጅ ዋጋ ጨምሯል። ያልተጣራ ድፍድፍ ነዳጅ በበርሚል ከ5 ዶላር ወይም ከ7 በመቶ በላይ ጭማሪ አሳይቷል። ይህንኑ ተከትሎ ያልተጣራ ድፍድፍ ነዳጅ በበርሜል ከ80 ዶላር ወደ 85 ዶላር ከፍ ብሏል።

ጭማሪው የተከሰተው ሳዑዲ አረቢያ፣ ኢራቅ እና በርካታ የባህረ ሰላጤው ሀገራት በቀን ከአንድ ሚሊዮን በርሜል በላይ ከምርታቸው ላይ እየቀነሱ መሆናቸውን ተከትሎ ነው። ሩሲያ ዩክሬንን በወረረችበት ወቅት የነዳጅ ዋጋ ጨምሮ የነበሩ ቢሆንም አሁን ላይ ግን ግጭቱ ከመቀስቀሱ በፊት ወደነበረበት ተመልሷል። ይሁን እንጂ አሜሪካ የነዳጅ ዋጋን ዝቅ ለማድረግ አምራቾች ምርታቸውን እንዲጨምሩ ስትጠይቅ ቆይታለች።

ባለፈው አመት ከፍተኛ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ መደረጉ በመሰረታዊ ምርቶች ላይ ግሽበት እንዲፈጠር ማድረጉ ይታወሳል።የዩናይትድ ስቴትስ ብሄራዊ የጸጥታ ምክር ቤት ቃል አቀባይ ስለ ቅርብ ጊዜ የምርት ቅነሳ በሰጡት መግለጫ ቅነሳው በአሁኑ ጊዜ ጠቃሚ ነው ብለን አናምንም ይህንንም ግልፅ አድርገናል ብለዋል። የምርት ቅነሳው በኦፔክ የነዳጅ ዘይት አምራቾች አባላት ሀገራት እየተደረገ ይገኛል።

የኦፔክ አባል ሀገራት ከዓለም ድፍድፍ ዘይት ምርት 40 በመቶውን ድርሻ ይይዛሉ። ሳዑዲ አረቢያ በቀን 500,000 ፣ ኢራቅ 211,000 በርሜል ያልተጣራ ድፍድፍ ነዳጅ ምርትን እየቀነሱ ይገኛል። የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ፣ ኩዌት፣ አልጄሪያ እና ኦማን ቅነሳ በማድረግ ላይ ናቸው። የሳውዲ ኢነርጂ ሚኒስቴር ባለስልጣን እርምጃው የነዳጅ ገበያውን መረጋጋት ለመደገፍ የታለመ የጥንቃቄ እርምጃ ማለቱን የሳውዲ ፕሬስ ኤጀንሲ ዘግበል።

[ዳጉ ጆርናል]
240 views09:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-01 13:40:12
የቤት ማፍረስ ዘመቻው ...

በአዲስ አበባ ዙርያ " ሸገር ከተማ " እየተካሄደ ያለውን የቤት ማፍረስ ዘመቻን በተመለከተ ኢሰመኮ የደረሰበትን የክትትል ውጤት በላከልን መግለጫ አሳውቋል።

በመግለጫው፤ በኦሮሚያ ክልል በሸገር ከተማ እየተካሄደ ያለው ቤቶችን የማፍረስ እና በግዳጅ ማስነሳት እርምጃ የመኖሪያ ቤት አልባነትን አባብሷል ብሏል።

ሕገ ወጥ የሆነ ግንባታን የማፍረስ እርምጃ ሕጋዊ ሂደትን መከተልና እርምጃው ሊያስከትል የሚችለውን ማኅበራዊ ቀውስ ከግንዛቤ በማስገባት አማራጭ መፍትሔዎችን ማመቻቸት ያስፈልጋልም ብሏል።

(ከኢስመኮ የተላከልን ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል)
310 viewsedited  10:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-01 09:46:29 የዓለማቀፉ ወንጀል ፍርድ ቤት መመስረቻ ስምምነት ፈራሚዋ ደቡብ አፍሪካ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቱን ለ"ብሪክስ" አገራት የመሪዎች ጉባኤ ሲሄዱ እንደምታስተናግዳቸው ዛሬ በውጭ ጉዳይ ሚንስትሯ ናለዲ ፓንዶር በኩል አስታውቃለች።

የዓለማቀፉ ወንጀል ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ፑቲን በዩክሬን "የጦር ወንጀል ፈጽመዋል" በማለት የእስር ማዘዣ ማውጣቱን ተከትሎ፣ በቀጣዩ ነሐሴ የ"ብሪክስ" አገራት የመሪዎች ጉባኤ አዘጋጇ ደቡብ አፍሪካ አቋሟ ምን እንደሚኾን በጉጉት ሲጠበቅ ነበር። ደቡብ አፍሪካና ሩሲያ በሌሎች አገራት ግፊት በድንገት ጠላት ሊኾኑ አይችሉም ያሉት ፓንዶር፣ ፑቲንን በጉባኤው እንዲገኙ እንደተጋበዙ ተናግረዋል። በዓለማቀፉ ፍርድ ቤት ስምምነት መሠረት፣ ደቡብ አፍሪካ ፑቲን ግዛቷን ከተረገጡ አስራ ለፍርድ ቤቱ የማስረከብ ግዴታ አለባት። "ብሪክስ" በፍጥነት በማደግ ላይ ያሉት ኃያላኑ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ሩሲያ፣ ቻይና፣ ሕንድና ብራዚል የመሠረቱተ ቡድን ነው።
262 views06:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ