Get Mystery Box with random crypto!

Ewnet Media

የቴሌግራም ቻናል አርማ ewnetmedia1 — Ewnet Media E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ewnetmedia1 — Ewnet Media
የሰርጥ አድራሻ: @ewnetmedia1
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.06K

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 7

2023-04-13 12:14:02 #ENDF

የሰሜን ምስራቅ ዕዝ ም/አዛዥ ሜጄር ጄነራል ብርሃኑ ጥላሁን በሰሜን ወሎ ስለተደረሰው የሰላም ስምምነት ምን አሉ ?

"  ይሄ ችግር መረገብ አለበት። ለማንም ለምንም አይጠቅምም ፤ አሁን ደግሞ ችግር በውይይት ነው መፍታት የምትችለው ወይስ በጠብመንጃ ነው በጠብመንጃ የፈቱ  ሀገሮች የትም የሉም። ህይወት ጠፋ ስለዚህ ሌሎችም ቢሆን ረጋ ብለው ይዩ ሁኔታውን ትክክል አይደለም ፤ በስተጀርባ ያለውን በትክክል ማየት አለባቸው።

ይሄ ግጭት ፤ ይሄ ንትርክ፣ ይሄ በየመንገዱ የነበረውን ሁከት ያቆመው ማንም አይደለም የሀገር ሽማግሌ መሃል እየገባ ነው ያቆመው ነፍሥ እንዳይጠፋ፣ ህፃናት እንዳይጎዱ ፣ የመንግስት እና የግል ንብረት እንዳይወድም ፣ ቤት እንዳይቃጠል ፣ ወንጀለኛ ያለአግባብ ተፈቶ እንዳይወጣ ከፍተኛ ስራ የሰራው የሀገር ሽማግሌ ነው።

ሌላው እዛ ያለው የፀጥታ ኃይልም ከሀገር ሽማግሌ ጋር ሆኖ መስራት አለበት ፣ ችግሩን ማስረዳት አለበት።

ሀገርን የሚጠቅም፣ ህዝብን የሚጠቅም መመሪያ ነው የወረደው ስለዚህ ያልተረዱና በጀርባ ሌላ መልክ የሚሰጡ ሰዎች ግፊት የተፈጠረ ችግር አሁን ህብረተሰቡ በከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ ነው ያለው   ስለዚህ ይሄንን ለመፍታት የመንግስትን መመሪያ ለማክብረ ተስማምተናል ከነሱ ጋር።

ሌላው በእነሱ ላይ ሲደርስ የነበረው ችግር፣ በእኛ ላይ አንዳንድ ነገሮች ይስተካከልልን የተባለው በሙሉ መንግሥት / የክልሉ መንግሥት ያደርጋል።

ስለዚህ ይሄን በተለየና በተጣመመ መንገድ የሚረዱ ሰዎች ትክክለኛ ባልሆነ መንገድ ነው እየቃኙ ያሉት ይሄ እንዲስተካከል ነው ጥረት ያደረግነው  ፤ ችግሩን ለመፍታት በትዕግስት መከላከያ እየሞተም ቢሆን ለማስተካከል ጥረት አድርጓል ፣ ዛሬ ተሳክቶልናል። "
242 views09:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-12 21:37:20 በሰሜን ወሎ ዞን አካባቢ ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ የፋኖ አባላት ይፋዊ ይቅርታ በማቅረብ ወደ መደበኛ ሕይወታቸው ለመመለስ ተስማሙ

በሰሜን ወሎ ዞን አካባቢ ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ የፋኖ አባላት የመንግሥትን የሰላም ጥሪ በመቀበልና ይፋዊ ይቅርታ በማቅረብ ወደ መደበኛ ሕይወታቸው ለመመለስ መስማማታቸው ተገለጸ።

የአማራ ክልል መንግሥት ከዚህ በፊት በግላቸው ታጥቀው ሲንቀሳቀሱ የቆዩ ግለሰቦችን እና ቡድኖችን በማወያየት ወደ መደበኛ የፀጥታ አደረጃጀት እንዲገቡ ወይም ደግሞ ወደ መደበኛ ሕይወታቸው እንዲመለሱ ጥረት ሲያደርግ መቆየቱ ይታወሳል።

በዚህ ጥረቱም በርካታዎች ጥሪውን ተቀብለው ተግባራዊ አድርገዋል። ነገር ግን በቅርቡ በሰሜን ወሎ ዞን አካባቢ የሚንቀሳቀሱ ግለሰቦች የመንግሥትን ጥሪ ባለመቀበል ከመከላከያ ጋር ወደ ግጭት የገቡ መሆኑም ይታወሳል።

ሆኖም በቅርቡ የፋኖ አባላቱ ይፋዊ ይቅርታ በመጠየቅ የመንግሥትን የሰላም ጥሪ መቀበላቸውን በማሳወቅ ከክልሉ መንግሥት እና ከመከላከያ ሠራዊት አመራሮች ጋር ውይይት አድርገው ወደ መደበኛ ሕይወት ለመመለስ መስማማታቸውን የክልሉ መንግሥት አስታውቋል ሲል አሚኮ ዘግቧል።
269 views18:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-12 11:21:13 በተቃውሞ ሳቢያ ተዘግቶ የነበረው የደጀን መንገድ፤ ትናንት ለሀገር አቋራጭ ትራንስፖርት አገልግሎት ክፍት ሆነ

በአማራ ክልል በተቀሰቀሰው ተቃውሞ ምክንያት ለሶስት ቀናት ተዘግቶ የነበረው የደጀን መንገድ፤ ትናንት ጠዋት ላይ መከፈቱን አንድ የከተማይቱ አስተዳደር ኃላፊ እና ነዋሪዎች ተናገሩ። ሀገር አቋራጭ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች፤ ከአዲስ አበባ በደጀን ከተማ በኩል ወደ ባህር ዳር ለሚደረግ ጉዞ ገና ትኬት መቁረጥ አለመጀመራቸውን ገልጸዋል።

ከአዲስ አበባ ወደ ባህር ዳር ከተማ የሚወስደው አውራ ጎዳና፤ በአማራ ክልል ምስራቅ ጎጃም ዞን በምትገኘው ደጀን ከተማ የተዘጋው፤ ባለፈው ሳምንት አርብ መጋቢት 29፤ 2015 ዓ.ም ነበር። የአማራ ክልል “ልዩ ኃይል መበተንን የሚቃወሙ” የተባሉ ነዋሪዎች፤ በከተማዋ መግቢያ እና ውስጥ ባሉ ቦታዎች መንገዱን ከዘጉ በኋላ በደጀን በኩል የሚያልፉ የህዝብ እና የጭነት ሀገር አቋራጭ ተሽከርካሪዎች መተላለፍ አቁመው ቆይተዋል።

ትናንት ማክሰኞ ሚያዝያ 3፤ 2015 ጠዋት ከሁለት ሰዓት ገደማ ጀምሮ ግን፤ ለቀናት ተዘግቶ የነበረው መንገድ ተከፍቶ ቆመው የነበሩ ተሽከርካሪዎች መንቀሳቀስ እንደጀመሩ የከተማዋ ኮሚዩኒኬሽን ቡድን መሪ አቶ ሞኙ ሆዴ አሳየ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል።
288 views08:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-11 19:14:31
በወልድያ ከተማ የሰዓት እላፊ ታወጀ  ጥብቅ የሆኑ ክልከላዎችም ተጥለዋል

ወልድያ ከተማ አስተዳደር የጸጥታ ኮማንድ ፖስት ላልተወሰነ ጊዜ የሚቆይ የሰዓት እላፊ ገደብ እና ክልከላ ማስቀመጡ ተገልጿል።

ክልከላዎቹ፦

- ጭፈራ ቤቶች ካፍቴሪያዎች ሬስቶራንቶች እና የመሳሰሉት ማንኛውም መጠጥ ቤቶች ከምሽቱ 2:00 ሰዓት በኋላ አገልግሎት መስጠት አይችሉም።

- ለባለ 3 እግር ተሽከርካሪዎች ከምሽቱ 1:00 ሰዓት እስከ ንጋቱ 12:00  ሰዓት ባለው ጊዜ መንቀሳቀስ የተከለከለ ሲሆን ፤ ከተሽከርካሪ እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ ለጸጥታ ሥራ ከተመደቡ ተሽከርካሪዎች ውጭ በዚህ ምደባ ስምሪት ያልታቀፉ የመንግሥት ተሽከርካሪዎች ከምሽቱ 2:00 እስከ ጧቱ 12:00  ብቻ እንዲሆን ተወስኗል።

- የሰው እንቅስቃሴ ለጸጥታ ሥራ ከተመደበው ሰው ውጭ ከምሽቱ 3:00 እስከ ጧቱ 12:00 ሰዓት ባለው ጊዜ መንቀሳቀስ ተከልክሏል።

- በማንኛውም ቦታና ጊዜ ለጸጥታ ሥራ ስምሪት ከተመደበ አካል ውጭ የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ በጥብቅ ተከልክሏል።

- አድማ መቀስቀስ፣ ማድረግና ማስተባበር እንዲሁም መደበኛ ሥራን ማስተጓጎል በጥብቅ ተከልክሏል።

- የመንግሥትን የታጠቀ ኀይል ያስከዳ፣ በተለያየ መንገድ አማሎ የጦር መሳሪያ የገዛ፣ የለወጠ ባልተገባ መንገድ መታወቂያ የሰጠ መንገድ የመራ ማንኛውም አካል በሕግ ተጠያቂ ይሆናል ተብሏል።

- የመንግሥት የጸጥታ ኀይል ሕግና ስርዓትን ለማስከበር በሚያከናውናቸው ተግባሮች ዙሪያ ማንኛውም ሰው የመተባበር ግዴታ ተጥሎበታል የማይተባበር በሕግ ይጠየቃል ተብሏል።

የኮማንድ ፖስቱ በአብዛኛውን በሌሎች ከተማዎች የተጣሉ ክልከላዎችን አይነት ይዘት ያለው ክልከላ ነው የጣለው።

(የወልድያ ከተማ አስተዳደር የጸጥታ ኮማንድ ፖስት ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል)
310 viewsedited  16:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-11 16:16:56 በዶ/ር ሊያ ታደሰ የተመራ ልዑክ መቐለ ገባ

በጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ የተመራው የጤና ሚኒስቴር ልዑካን ቡድን ዛሬ መቐለ ገብቷል።ልዑኩ ከክልሉ አስተዳደር ጋር በተለያዩ የጤና ጉዳዮች ዙሪያ እንደሚነጋገር ይጠበቃል።
272 views13:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-10 20:09:59 #Update

ልክ ጎንደር እንደተደረገው በደብረብርሃን ከተማም ክልከላዎች ተጣሉ።

ደብረ ብርሃን ውስጥ ህጋዊ መታወቂያ ሳይዙ መንቀሳቀስ በጥብቅ የተከለከለ ሲሆን ህጋዊ መታወቂያ ሳይዝ የተንቀሳቀሰ ግለሰብም ሆነ ቡድን በህግ ቁጥጥር ስር ይውላል ተብሏል።

የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ኮማንድ ፖስት " የከተማዉን ሰላምና የህግ የበላይነት ለማረጋገጥ " እንዲቻል በሚል ክልከላዎችን መጣሉን አሳውቋል።

ክልከላዎቹ ምንድናቸው ?

1. በከተማው ያሉ ማንኛውም መጠጥ ቤቶችና ጭፈራ ቤቶች እስከ ምሽቱ 2:00 ሰዓት ዉጭ አገልግሎት መስጠት ተከልክለዋል።

2. በከተማው የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ባለ 3 እግር ባጃጆች ከንጋቱ 12:00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 2:00  ሰዓት ዉጭ መንቀሳቀስ ተከልክሏል።

3. በከተማ አስተዳደሩ ለጸጥታ ማስከበር ተልዕኮ ከተሠጠው   የፀጥታ ኃይል ውጭ የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ ተከልክሏል።

4. ድምፅ አልባ መሳሪያዎችን ስለታማ የሆኑ እንደ ጩቤ ፣ ገጀራ ፣ አንካሴ ፣ ጦርና ፌሮ ብረት ወዘተ የመሳሰሉትን ይዞ መንቀሳቀስ ተከልክሏል።

5. በህግ የሚፈለጉ ወይም ተጠርጣሪዎችን ሽፋን የሰጠ ፣ የደበቀ ፣ የሀሰተኛ መረጃ ሰጥቶ ያሰመለጠ ፣ የፀጥታ ሀይሎችን የህግ ማስከበር ተልዕኮ ማደናቀፍ ማወክ በህግ ተከልክሏል።

6. በማንኛውም ቦታና ስዓት ጥይትም ሆነ ሮኬት ርችት መተኮስ በጥብቅ ተከልክሏል።

7. በተከለከሉ ቦታዎች በእምነት ተቋማት፣ በገቢያዎች፣ ህዝብ በብዛት በሚሰበሰብባቸው ቦታዎች ፣ በሆቴሎች፣ መጠጥ ቤቶችና ግሮሰሪዎች፣ ልዩ ልዩ መዝናኛ ቦታዎች ጦር መሳሪያ ይዞ መገኘትና መንቀሳቀስ ተከልክሏል።

8. የሠራዊቱን ሚሊተሪ (አልባሳት) ከሰራዊቱ አባላት ውጭ መልበስ ተከልክሏል የልዩ ኋይል ፣ የፓሊስ ፣ የመከላከያ ሠራዊት ፣ የፌዴራል ፓሊስ ልብስ መልበስ ተከልክሏል።

9 . ያልተፈቀደ ስብሰባዎችን ያለ መንግስት እውቅና ውጭ ስብሰባ ማድረግ ፣ ያልተፈቀደ ሰልፍ ማድረግ ፣ መንገድ መዝጋት  ተከልክሏል።

10. አድማ መቀስቀስ፣ ማድረግና ማስተባበር እንዲሁም መደበኛ ስራን ማስተጓጎል በጥብቅ ተከልክሏል።

11. የአማራን ህዝብ ከጥቃትና ከውርደት ለመታደግ መስዋትነት የከፈሉ የአማራ የቁርጥ ቀን ልጆች ፣ የአማራ ልዩ ኃይል አባላት በተፈጠረው የመረጃ ክፍተት ከተለያየ አካባቢ ተነስተው ወደ ከተማው የገቡ በከተማው በተዘጋጀው ማረፊያዎች እንዲሰባሰቡ ማሳሰቢያ ተላልፏል። ከዚህ ውጭ በተናጠልም ሆነ በቡድን መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ እና ጥይት መተኮስ ተከልክሏል።

12. ፀጉረ ልዉጥ/አጠራጣሪ ሰው ከቤቱ ያሳደረ ፣ያከራየ፣ በሆቴሉ አልጋ ያስያዙ  እንዲሁም ለሚመለከተዉ የፀጥታ አካል ጥቆማ ያልሰጠ በህግ የሚጠይቅ ይሆናል ተብሏል።

13. በከተማው ውስጥ ህጋዊ መታወቂያ ሳይዙ መንቀሳቀስ በጥብቅ የተከለከለ ነው ህጋዊ መታወቂያ ሳይዝ የተንቀሳቀሰ ግለሰብም ሆነ ቡድን በህግ ቁጥጥር ስር ይውላል።

14. በከተማው በተፈናቃይ ካምፕ የምትገኙ ተፈናቃይዎች በማንኛውም ሰአት ወቅታዊ ሁኔታው እስከሚስተካከለ ድረስ ከካምፕ ውጭ መገኘት ፈጽሞ ተከልክለዋል።

መረጃው ደብረብርሃን ከተማ አስተዳደር የጸጥታው ምክር ቤት ኮማንድ ፖስት ነው።
159 views17:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-10 13:40:58
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 19ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ
213 viewsedited  10:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-10 12:39:06 #GONDAR

በጎንደር ክልከላዎች ተጣሉ።

የጎንደር ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ኮማንድ ፖስት ክልከላዎችን አስቀመጠ።

ኮማንድ ፖስቱ ፤ ክልከላው " የከተማዉን ሰላምና የህግ የበላይነት ለማረጋገጥ እንዲቻል " የተቀመጠ መሆኑን ገልጿል።

የተቀመጡ ክልከላዎች ምንድናቸው ?

1. በከተማው ያሉ ማንኛውም መጠጥ ቤቶችና ጭፈራ ቤቶች እስከ ምሽቱ 3:00 ሰዓት ዉጭ አገልግሎት መስጠት ተከልክለዋል።

2. በከተማው የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ባለ 3 እግር ባጃጆች ከንጋቱ 12:00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 2:00 ሰዓት ዉጭ መንቀሳቀስ ተከልክለዋል።

3. ከተፈቀደለት የመንግስት የፀጥታ ኃይል ውጭ የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ ተከልክሏል።

4. ድምፅ አልባ መሳሪያዎችን ስለታማ የሆኑ እንደ ጩቤ ፣ ገጀራ ፣ አንካሴ ፣ ጦርና ፌሮ ብረት ወዘተ የመሳሰሉትን ይዞ መንቀሳቀስ ተከልክሏል።

5. በህግ የሚፈለጉ ወይም ተጠርጣሪዎችን ሽፋን የሰጠ ፣ የደበቀ ፣ የሀሰተኛ መረጃ ሰጥቶ ያሰመለጠ ፣ የፀጥታ ሀይሎችን የህግ ማስከበር ተልዕኮ ማደናቀፍ ማወክ በህግ ተከልክሏል።

6. በማንኛውም ቦታና ስዓት ጥይትም ሆነ ሮኬት ርችት መተኮስ በጥብቅ ተከልክሏል።

7. በተከለከሉ ቦታዎች በእምነት ተቋማት፣ በገቢያዎች፣ ህዝብ በብዛት በሚሰበሰብባቸው ቦታዎች ፣ በሆቴሎች፣ መጠጥ ቤቶችና ግሮሰሪዎች፣ ልዩ ልዩ መዝናኛ ቦታዎች ጦር መሳሪያ ይዞ መገኘትና መንቀሳቀስ ተከልክሏል።

8. የሠራዊቱን ሚሊተሪ (አልባሳት) ከሰራዊቱ አባላት ውጭ መልበስ የተከለከለ ነው ፦
- የልዩ ኃይል ፣
- የፓሊስ ፣
- የመከላከያ ሠራዊት ፣
- የፌዴራል ፓሊስ ልብስ መልበስ በጥብቅ ተከልክሏል።

9. ያልተፈቀዱ ስብሰባዎችን ማለትም ያለ መንግስት እውቅና ውጭ ስብሰባ ማድረግ ፣ ወታደራዊ ስልጠና መስጠት ተከልክሏል።

10. አድማ መቀስቀስ፣ ማድረግና ማስተባበር እንዲሁም መደበኛ ስራን ማስተጓጎል በጥብቅ ተከልክሏል።

11. የአማራን ህዝብ ከጥቃትና ከውርደት ለመታደግ መስዋትነት የከፈሉ የአማራ የቁርጥ ቀን ልጆች ፣ የአማራ ልዩ ኃይል አባላት በተፈጠረው የመረጃ ክፍተት ከተለያየ አካባቢ ተነስተው ወደ ከተማው የመጡ በከተማው በተዘጋጀው ማረፊያዎች እንዲሰባሰቡ ማሳሰቢያ ተለልፏል። ከዚህ ውጭ በተናጠልም ሆነ በቡድን መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ እና ጥይት መተኮስ ተከልክሏል።

12. ፀጉረ ልዉጥ/አጠራጣሪ ሰው ከቤቱ ያሳደረ ፣ያከራየ፣ በሆቴሉ አልጋ ያስያዙ እንዲሁም ለሚመለከተዉ የፀጥታ አካል ጥቆማ ያልሰጠ በህግ  ይጠየቃል።

መረጃው የጎንደር ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ኮማንድ ፖስት ነው።
212 views09:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-10 12:09:05
ደሴ ሰላማዊ ሰልፍ

በደሴ ከተማ በዛሬው እለት ሰላማዊ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።

ደሴ ዛሬ ጠዋት መውጫ እና መግቢያ መንገዶች ዝግ መሆናቸውንም ከስፍራው ተሰምቷል።
196 viewsedited  09:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-10 08:55:11 የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ አብን የሚከተሉትን ጥሪዎች በድጋሜ አስተላልፏል

1. ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ውሳኔያቸውን በይፋ እንዲሰርዙ ፣ ውሳኔው ስለመሰረዙ በአደባባይ እንዲገልጹ እና የአማራ ልዩ ኃይል አባላት እና የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላት ወደ ካምፓቻቸው እና ወደ ግዳጅ ቦታቸው እንዲመለሱ በይፋ ጥሪ እንዲያደርጉ፤

2. በፌዴራል መንግስቱ ውሳኔ እና ትዕዛዝ ከስራ ውጭ የሆኑት የአማራ ልዩ ኃይል ከፍተኛ አመራሮች ፣ የብርጌድ እና የክፍለ ጦር አዛዦች ወደ ኃላፊነታቸው እና ምድብ ቦታቸው እንዲመለሱ እንዲደረግ፤

3. የክልሉ መንግስት ለልዩ ኃይሉ  አስፈላጊ የሆኑ የስንቅ እና ሎጂስቲክ እንዲያቀርብ እና ደሞዝ እንዲከፍል፤

4. በካምፕ እና በግዳጅ ቦታችሁ ላይ የምትገኙ ውድ የአማራ ክልል የልዩ ኃይል ፖሊስ አመራሮች እና አባላት ሠራዊቱ እንዲበተን የሚደረጉ ጥረቶችን እና የፕሮፖጋንዳ ጥቃቶችን በመቋቋም በተለመደው ሥነ-ምግባር ፣ ዲስፕሊን እና ጨዋነት የሠራዊቱን የእዝ ሰንሰለት አክብራችሁ እና ጠብቃችሁ ከህዝባችሁ ጎን እንድትቆሙ፤

5. ለሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላት እና አመራሮች በሙሉ በግፍ እየተጠቃ ካለው የአማራ ክልል ልዩ ኃይል እና ከአማራ ሕዝብ ጎን እንድትቆሙ እና ለግጭት ከሚጋብዙ ማናቸውም ሁኔታዎች እንድትቆጠቡ፤

6. የአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም የዞን እና የወረዳ አመራሮች በሙሉ በዚህ ፈታኝ ወቅት ከልዩ ኃይል ፖሊስ ሰራዊት እና ከሕዝባችሁ ጎን እንድትቆሙ፤ 

7. የአማራ ሕዝብ በየአካባቢው ላሉት የልዩ ኃይል አባላት አስፈላጊውን ስንቅ እና ድጋፍ እንዲያደርግላቸው ድርጅታችን አብን ጥሪውን አቅርቧል።

አብን መላው የአማራ ሕዝብ እና ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን በሙሉ ከሀገር ወዳዱ የአማራ ልዩ ኃይል ጎን እንዲቆሙ ጥሪውን አቅርቧል።
216 views05:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ