Get Mystery Box with random crypto!

Ewnet Media

የቴሌግራም ቻናል አርማ ewnetmedia1 — Ewnet Media E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ewnetmedia1 — Ewnet Media
የሰርጥ አድራሻ: @ewnetmedia1
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.06K

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 68

2022-07-07 10:56:23 ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች የሰጡት ማብራሪያ ዋና ዋና ነጥቦች

በግፍ ህይወታቸውን ላጡ ለተገደሉ ንፁሀን ዜጎች የሚሰማኝን ጥልቅ ኃዘን መግለፅ እፈልጋለሁ፤ ባልሰሩት ወንጀል በማይመለከታቸው ጉዳይ ባልተገባ መንገድ ህይወታቸውን ከሚቀጥፉ ገዳዮች አጥፊ ስብስቦች በእጅጉ ዜጎቻችንን ህይወታቸውን መታደግ ባመቻላችን ጥልቅ ሃዘን ይሰማናል፤

የንጹሀንን ደም በከንቱ የሚያፈሱ የትኛውንም ስብስብ ለማጥፋት በጀመርነው እንቀጥላለን፤ የጥፋት ሃይሎች ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊያን መግፋት ማጎሳቆል ይችሉ እንደሆነ እንጂ ከዋናው ዓላማ አያሰናክሉንም፤ መንግስት 24 ሰአት የዜጎቹን ህይወት ለመታደግ ከፍተኛ ጥረት ያደርጋል፤

በሚፈጠሩ ችግሮች ሁሉ ህይወታቸውን የሚገብሩ የጸታ አካላት እንዳሉ ማወቅ ያስፈልጋል፤ ይሄንን ዋጋ የሚከፍለው የተለየ ጥቅም አግኝቶ ክፍያ ተሰጥቶት አይደለም፣ በማይመች ሁኔታ ውስጥ ሆነው ነው የጸጥታ ሃይሎቻችን ዋጋ እየከፈሉ ያሉት፤ ለእነሱ ክብር መስጠት ይገባል፤

ሽብር የዓለም ሁሉ ፈተና ነው፤ በኢትዮጵ ውስጥ ብቻ የሚፈጸም አድርገን ማሰብ የለብንም፤ ሽብር መልኩ ብዙ ነው፤ በዓለም ላይ እንድ አሜሪካ ጠንካራ የደህንነት ተቋመ ያለው አገር የለም፤ ነገር ግን ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ ብቻ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ተገድለውባታል፤

አሸባሪዎችን ከዘር ጋር ብቻ ማያያዝ ተገቢ አይደለም፤ የአልሸባብ አብዛኛው ታጣቂ ሶማሌ ነው፤ በቡድኑ የሚገደለውም ሶማሌ ነው፤ ተጨማሪ ይዘን እንመለሳለን
236 views07:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 08:41:07 ጠ/ሚ ዐቢይ ዛሬ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው በ2015 ዓ፣ም ረቂቅ በጀት እና በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ምላሽ እና ማብራሪያ እንደሚሰጡ ምክር ቤቱ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል።

ምክር ቤቱ በረቂቅ በጀቱ ላይ የሚቀርብለትን ሪፖርት እና የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ ያጸድቃል። በተጨማሪም ምክር ቤቱ የመረጃና ደኅንነት አገልግሎትን መልሶ ለማቋቋም የቀረበለትን ረቂቅ አዋጅ መርምሮ ያጸድቃል ተብሏል።
232 views05:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 20:18:06 #AddisAbaba

የቤት ኪራይ መጨመር አይቻልም !

" ለቤት ኪራይ የወጣው ደንብ እስከሚሻሻል ድረስ የኪራይ ዋጋ መጨመር አይቻልም- ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ለቤት ኪራይ የወጣው ደንብ እስከሚሻሻል ድረስ የኪራይ ዋጋ መጨመር የማይቻል መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለፁ።

ከንቲባዋ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ በሰጡት መግለጫ ለቤት ኪራይ የወጣው ደንብ እስከሚሻሻል የቤት ኪራይ መጨመር አይቻልም ብለዋል።

ከንቲባዋ በመግለጫቸው የከተማ አስተዳደሩ በየ3 ወሩ የሚታደስ መመሪያ እንደነበረው አስታውሰዋል።

በከተማዋ ከፍተኛ የኑሮ ውድነት በመኖሩ በዜጎች ላይ ጫና እያስከተለ በመሆኑ የቤት ኪራይ መጨመር መከልከሉን አስረድተዋል።

በመሆኑም የከተማ አስተዳደሩ በልዩ ሁኔታ አይቶ ደንቡ እስካልተሻሻለ ድረስ ምንም አይነተ የቤት ኪራይ ጭማሪ ማድረግ አይቻልም ብለዋል።

አከራዮችም ሆኑ ተከራዮች ይህንኑ ማወቅ እንዳለባቸው ጠቁመው ክልከላውን ተላልፈው በሚገኙ ላይ ህጋዊ እርምጃ ይወሰዳል ሲሉ አሳስበዋል።

በዚህ ዙሪያ ዜጎች መብትና ግዴታቸውን በቅጡ ተገንዝበው እንዲሰሩ አስገንዝበዋል።

#ENA
265 views17:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 20:06:33 የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲታወጅ የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) ጠየቀ

የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) በወቅታዊ ጉዳይ እና በድርጅቱ ቀጣይ የትግል አቅጣጫ መግለጫ ሰጥቷል።በምእራብ እና ምስራቅ ወለጋ በአማራ ብሄር ተወላጆች ላይ ተደጋጋሚ አሰቃቂ ጥቃት ተፈፅማል ብሏል ንቅናቄው።ይህ ጥቃት በአማራ ሕዝብ ላይ ሲፈፀም አዲስ አይደለም ይልቁንስ የተሳሳተው ትርክት አንዱ ቅርንጫፍ መኾኑንም አብን አስታውቋል።አማራ ጠል ትርክት ከውጭም ከውስጥም ጠላት አፍርቶልናል እናም በዚህ ደግሞ እየተጎዳ ያለው ምስኪን ራሱን መከላከል የማይችል ሕዝብ ነው፤ የአሁኑን ጨምሮ ተከታታይ ችግሮችን ለማስቆም የሚመለከታቸው ሁሉ ሊያስቆሙት ይገባል ሲሉ የንቅናቄው ሊቀመንበር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) አሳስበዋል።

በአማራ ሕዝብ ላይ እየተደረገ ያለውን ዘር የማጥፋት ጥቃት የሚመለከታቸው ሁሉ ሊያስቆሙት ይገባል ሲሉ ዶክተር በለጠ አሳስበዋል።ንቅናቄው በአማራ ሕዝብ ላይ አየተፈፀመ ያለው ስልታዊ ዘር ማጥፋት ነው ብሎ አብን ያምናል ብለዋል ዶክተር በለጠ በመግለጫቸው።የአማራ ሕዝብ ተከታታይ ግድያ ግድ ሊለው የሚገባው የመንግስት መዋቅር ችላ ማለቱን እንዲያቆም እና ባስቸኳይ ሕዝብን እንዲጠብቅ ሲል አብን አሳስቧል።

ጥቃቱን እየተከታተለ እርምጃ ያልወሰደው መንግስት ይህንን ጥቃት እየሸፈኑ ያሉ እንዲሁም ሕዝብን መጠበቅ ያለባቸው ከክልል እስከ ፌደራል ቢሮዎች ተጠያቂ ናቸው ሲልም አብን አስታውቋል።ጥቃቱን ለማስቆም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲታወጅና የአካባቢው ነዋሪዎች በፀጥታ አካልነት ተካትተው ራሳቸውን እንዲጠብቁ የሚያስችል ሥራ እንዲሰራ አብን ጠይቋል።አጥቂዎች በግልፅ ፍርድ እንዲበየንባቸው፤ ይህን ችላ ያሉ፣ እንዲባባሱ ያደረጉ ሚዲያዎች፣ ፓለቲከኞች እና ግለሰቦችን መንግስት ተጠያቂ እንዲያደርግ አብን ጠይቋል።

ብሄራዊ የሀዘን ቀን እንዲታወጅም አብን ጠይቋል።አማራ የመጣበትን ችግር ለመመከት እንደ ሕዝብ በአንድነት ለመመከት አንድነቱን ጠብቆ የመጣውን የዘር ማጥፋት ጥቃት ለመመከት እንዲሠራ አብን ጥሪ አቅርቧል።በቀጣይ ሀሙስ የሀዘን ቀንን ለማሰብ የሻማ ማብራት፣ የፓናል ውይይት እና ሌሎች ዝግጅትን ለማከናወን ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን አብን ገልጿል።
261 views17:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 20:29:31 #የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ!

በነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ጭማሬ ተደረገ!!

ከነገ ሰኔ 29 ቀን 2014 ዓ.ም እስከ ሀምሌ 30 ቀን 2014 ዓ.ም የነዳጅ ምርቶች የመሸጫ ዋጋ ጭማሬ መደረጉን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በዚህም መሠረት ከነገ ጀምሮ

ቤንዚን----47 ነጥብ 83 በሊትር

ነጭ ናፍጣ ….49 ነጥብ 02 በሊትር

ኬሮሲን…49 ነጥብ 02 በሊትር

ቀላል ጥቁር ናፍጣ…53 ነጥብ 10 በሊትር

ከባድ ጥቁር ናፍጣ…52 ነጥብ 37 በሊትር

የአውሮፕላን ነዳጅ…98 ነጥብ 83 በሊትር እንደሚሸጥ ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡

ምንጭ ፣ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚንስቴር
311 views17:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 19:33:23 አብን ትናንት በኦሮሚያ ክልል ቄለም ወለጋ ዞን ሐዋ ገላን ወረዳ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጭፍጨፋ ከ400 በላይ አማራዎች በግፍ እንደተጨፈጨፉ ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።ፌደራል እና ክልል መንግሥታት ጭፍጨፋውን ባለማስቆም የዘር ማጥፋት ወንጀሉ ተባባሪ ሆነዋል ሲል የከሰሰው አብን፣ መንግሥት ለጭፍጨፋ ተጋላጭ የሆኑ ነዋሪዎችን አደራጅቶ እንዲያስታጥቅ እና ከጭፍጨፋው ለተረፉ ወገኖች አስቸካይ ዕርዳታ እንዲሰጥ ጠይቋል። ፌደሬሽን ምክር ቤት ፌደራል መንግሥቱ ጭፍጨፋ እየተፈጽመባቸው ያሉትን የወለጋ ዞኖችን በቀጥታ እንዲያስተዳድር እንዲወስንም አብን ጨምሮ ጠይቋል።
295 views16:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 09:07:11 ምክር ቤቱ አሸባሪው የሸኔ ቡድን በምእራብ ወለጋ በንጹሀን ዜጎች ላይ ያደረሰውን ጥቃት በፅኑ አወገዘ

አሸባሪው የሸኔ ቡድን በጸጥታ ሀይሎች በከፍተኛ ሁኔታ ጥቃት እየደረሰበት መሆኑን ተከትሎ ከጥቃቱ በመሸሽም በምእራብ ወለጋ ንጹሀን ዜጎች ላይ ያደረሰውን ጉዳት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ኮንኗል።ቡድኑ በቄለም ወለጋ ዞን ውስጥ የሚገኙ ንጹሀን ዜጎች ላይ የፈጸመውን ጭፍጨፋም በእጅጉ የሚወገዝ መሆኑን አስታውቋል።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በማህበራዊ ትስስር ገጹ ማምሻውን ባወጣው መግለጫ "በዜጎቻችን ላይ በደረሰው ስቃይ እና መከራ እያዘን ይህንን አሸባሪ ቡድን ለማስወገድ መላው ህዝባችን በተለይም የአካባቢው ማህበረሰብ ከጸጥታ ሀይላችን ጋር በመተባበር እስከመጨረሻው እንድናስወግደው" ሲልም ጥሪውን አቅርቧል።
322 views06:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 23:13:21
" በትንሹ 150 ሰዎች ተገድለዋል "

ቢቢሲ አፍሪካ ዛሬ ማምሻውን ይዞት በወጣው ዘገባ በኦሮሚያ ክልል፣ ሀዋ ገለን ወረዳ በተፈፀመው ጥቃት በትንሹ 150 ሰዎች መገደላቸውን ገልጿል።

ቢቢሲ አፍሪካ ፤ የአይን እማኞች ጥቃቱ በሀዋ ገላን ወረዳ መፈፀሙን እንደገለፁለትና በአካባቢው ላይ በሚኖሩ የአማራ ተወላጆች ላይ ያነጣጠረ እንደነበር አክሏል።
316 viewsedited  20:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ