Get Mystery Box with random crypto!

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲታወጅ የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) ጠየቀ የአማራ ብሄራዊ ንቅና | Ewnet Media

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲታወጅ የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) ጠየቀ

የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) በወቅታዊ ጉዳይ እና በድርጅቱ ቀጣይ የትግል አቅጣጫ መግለጫ ሰጥቷል።በምእራብ እና ምስራቅ ወለጋ በአማራ ብሄር ተወላጆች ላይ ተደጋጋሚ አሰቃቂ ጥቃት ተፈፅማል ብሏል ንቅናቄው።ይህ ጥቃት በአማራ ሕዝብ ላይ ሲፈፀም አዲስ አይደለም ይልቁንስ የተሳሳተው ትርክት አንዱ ቅርንጫፍ መኾኑንም አብን አስታውቋል።አማራ ጠል ትርክት ከውጭም ከውስጥም ጠላት አፍርቶልናል እናም በዚህ ደግሞ እየተጎዳ ያለው ምስኪን ራሱን መከላከል የማይችል ሕዝብ ነው፤ የአሁኑን ጨምሮ ተከታታይ ችግሮችን ለማስቆም የሚመለከታቸው ሁሉ ሊያስቆሙት ይገባል ሲሉ የንቅናቄው ሊቀመንበር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) አሳስበዋል።

በአማራ ሕዝብ ላይ እየተደረገ ያለውን ዘር የማጥፋት ጥቃት የሚመለከታቸው ሁሉ ሊያስቆሙት ይገባል ሲሉ ዶክተር በለጠ አሳስበዋል።ንቅናቄው በአማራ ሕዝብ ላይ አየተፈፀመ ያለው ስልታዊ ዘር ማጥፋት ነው ብሎ አብን ያምናል ብለዋል ዶክተር በለጠ በመግለጫቸው።የአማራ ሕዝብ ተከታታይ ግድያ ግድ ሊለው የሚገባው የመንግስት መዋቅር ችላ ማለቱን እንዲያቆም እና ባስቸኳይ ሕዝብን እንዲጠብቅ ሲል አብን አሳስቧል።

ጥቃቱን እየተከታተለ እርምጃ ያልወሰደው መንግስት ይህንን ጥቃት እየሸፈኑ ያሉ እንዲሁም ሕዝብን መጠበቅ ያለባቸው ከክልል እስከ ፌደራል ቢሮዎች ተጠያቂ ናቸው ሲልም አብን አስታውቋል።ጥቃቱን ለማስቆም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲታወጅና የአካባቢው ነዋሪዎች በፀጥታ አካልነት ተካትተው ራሳቸውን እንዲጠብቁ የሚያስችል ሥራ እንዲሰራ አብን ጠይቋል።አጥቂዎች በግልፅ ፍርድ እንዲበየንባቸው፤ ይህን ችላ ያሉ፣ እንዲባባሱ ያደረጉ ሚዲያዎች፣ ፓለቲከኞች እና ግለሰቦችን መንግስት ተጠያቂ እንዲያደርግ አብን ጠይቋል።

ብሄራዊ የሀዘን ቀን እንዲታወጅም አብን ጠይቋል።አማራ የመጣበትን ችግር ለመመከት እንደ ሕዝብ በአንድነት ለመመከት አንድነቱን ጠብቆ የመጣውን የዘር ማጥፋት ጥቃት ለመመከት እንዲሠራ አብን ጥሪ አቅርቧል።በቀጣይ ሀሙስ የሀዘን ቀንን ለማሰብ የሻማ ማብራት፣ የፓናል ውይይት እና ሌሎች ዝግጅትን ለማከናወን ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን አብን ገልጿል።