Get Mystery Box with random crypto!

Ewnet Media

የቴሌግራም ቻናል አርማ ewnetmedia1 — Ewnet Media E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ewnetmedia1 — Ewnet Media
የሰርጥ አድራሻ: @ewnetmedia1
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.06K

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2023-04-25 17:26:51
የኩላሊት ታማሚ የተኛ በማስመሰል ገንዘብ ሲሰበስቡ የተገኙ 4 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ።

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ሲኒማ ራስ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሚኒባስ ተሽከርካሪ ውስጥ ባዶ ፍራሽ አንጥፈው፤ የኩላሊት ታማሚ የተኛ በማስመሰል በህክምና ሰበብ ገንዘብ ሲሰበስቡ የተገኙ 4 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።

እንደ ፖሊስ መረጃ 4 ተጠርጣሪዎች የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3- 43018 አ.አ በሆነ ሚኒባስ ውስጥ ባዶ ፍራሽ በማንጠፍ ፣ በፍራሹ ላይ የኩላሊት በሽታ ታማሚ የተኛ በማስመሰልና የግለሰብ ፎቶ በባነር አሳትመው በመስቀል ገንዘብ ሲሰበስቡ እንደነበር ገልጿል።

በዚህም የፖሊስ አባላት በጥርጣሬ ባከናወኑት የማረጋገጥ ስራ በቁጥጥር ስር ሊውሉ መቻላቸውን ከአዲስ አበባ ፒሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
218 viewsedited  14:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-25 11:14:53 “የሱዳንን ህዝብ ይቅርታ መጠየቅ እፈልጋለሁ”- ጄነራል ዳጋሎ

ራፒድ ሰፖርት ፎርስ (አር.ኤስ.ኤፍ) ተብሎ በሚጠራው ፈጥኖ ደራሽ ኃይል ዋና አዛዥ ጄነራል መሃመድ ሃምዳን ዳጋሎ “የሱዳንን ህዝብ ይቅርታ መጠየቅ እፈልጋለሁ” አሉ።

ጄነራል መሃመድ ሃምዳን ዳጋሎ በሱዳን እየተካሄደ ባለው ጦርነት ዙሪያ ከስካይ ኒውስ ጋር በነበራቸው ቆይታ “አሁን ላይ እየተዋጋን ያለነው ከሱዳን ጦር ጋር ሳይሆን ከቅጥረኛ ኃይሎች ጋር ነው፤ ምክንያቱም 90 በመቶ የሱዳን ጦር ከጥቅም ውጪ ሆኗል” ብለዋል። ዳጋሎ አክለውም፤ “ከዚህ በኋላ ከሱዳን ጦር ዋና አዛዣ አብዱል ፈታህ አል ቡርሃን ጋር ተቀምጦ መነጋገር ምንም ዋጋ እንደሌለውና አልቡርሃን ከዚህ በኋላ ያለው አማራጭ እጅ መስጠት ብቻ ነው” ሲሉ ተናግረዋል።

“ጦርነት አልፈልግም ነበር፣ ከጦርነት ይልቅ ሰላም እና መረጋጋትን ነው የምመርጠው” ያሉት ዳጋሎ፤ “ወደ ጦርነት እንድንገባ የገፋፋን አልቡርሃን ነው፤ አሁን ግን እጁ ላይ ምንም አልቀረለትም” ሲሉም ተናግረዋል። በአሁኑ ወቅት የት እንዳሉ የተጠየቁት ሃሜቲ፤ “እኔ የሱዳን ህዝብ አንድ አካል ነኝ፤ ካርቱምን ለቀቄ ወደየትም መሄድ አልችልም፤ እዛው ጦር ግንባር ላይ ነኝ” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

የሱዳን መከላከያ ሰራዊት በበኩሉ በዛሬው እለት በቃል አቀባይ ጽህፈት ቤቱ በኩል ጦርነቱን አስመልክቶ መግለጫ የሰጠ ሲሆን፤ በአሁኑ ወቅት በሱዳን ያለው ሁኔታ እየተረጋጋ መሆኑን እና የሱዳን ጦር የካርቱም የመኖሪያ አካባቢዎችን ደህንነት ለማስጠበቅ እየሰራ እንደሆነ ገልጸዋል።

የተለያዩ ሀገራት ዜጎችን ከሱዳን ከማስወጣት ጋር በተያያዘ ከሀገራት መሪዎች ጋር ግንኙነት እየተደረገ መሆኑን እና የማስወጣት ሂደቱ አሁን ባለበት ሂደት እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።
254 views08:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-24 13:43:18
በአዲስ አበባ በሚገኙ 153ቱም ነዳጅ ማደያዎች የነዳጅ ሽያጭ በዲጂታል ክፍያ ሥርዓት እየተከናወነ ነው

ኢትዮ ቴሌኮም

በአዲስ አበባ በሚገኙ 153ቱም ነዳጅ ማደያዎች የነዳጅ ሽያጭ በዲጂታል ክፍያ ሥርዓት እየተከናወነ መሆኑን ኢትዮ ቴሌኮም አስታወቀ።

በአዲስ አበባ በሚገኙ ሁሉም ነዳጅ ማደያዎች ባለሙያዎች እና የቴሌብር ወኪሎች ተሰማርተው አስፈላጊውን እገዛ በማድረግ ላይ እንደሚገኙ ኢትዮ ቴሌኮም ገልጿል።

በአዲስ አበባ ነዳጅ ማደያዎች ዛሬ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ በሆነው የዲጂታል ክፍያ ሥርዓት ደንበኞች በቀላሉ ክፍያቸውን በቴሌብር እየፈጸሙ እንደሆነም ተገልጿል።

ደንበኞች ነዳጅ ለመቅዳት ሲሄዱ በቅድሚያ የቴሌብር አካውንት ከሌላቸው ቴሌብር ሱፐርአፕን http://xn--onelink-om4a.to/75zfa5 በማውረድ ወይም *127# በመደወል በቀላሉ ሂደቱን በመከተል እንዲመዘገቡ ከቴሌብር ጋር በተሳሰሩ 20 ባንኮች፣ በአገልግሎት ማዕከሎች ወይም በቴሌብር ወኪሎች በኩል በቂ ገንዘብ ወደ ቴሌብር አካውንት እንዲያስተለልፉ እና በየነዳጅ ማደያዎቹም በሚገኙ ወኪሎች በኩል ገንዘብ ገቢ በማድረግ የነዳጅ ክፍያን በቀላሉ በቴሌብር መፈጸምም እንደሚችሉ ኢትዮ ቴሌኮም በማኅበራዊ ሚዲያ ገጹ አስታውቋል።
310 viewsedited  10:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-23 20:37:56
ታዋቂው የአፋን ኦሮሞ ድምፃዊ ዘሪሁን ወዳጆ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

ታዋቂው የአፋን ኦሮሞ ድምፃዊ ዘሪሁን ወዳጆ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።ድምፃዊው ለረዥም ጊዜ ባደረበት ህመም በህክምና ሲረዳ ቆይቷል።የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በድምፃዊው ሞት የተሰማውን ሀዘን ገልጿል።
97 viewsedited  17:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-22 16:01:21 በርካታ ኢትዮጵያውያን የሚገኙበት የሱዳን አል-ሁዳ ወህኒ ቤት ተሰበረ 

ከካርቱም በስተምስራቅ የሚገኙ አካባቢዎች በጀነራል አህመድ ሃምዳን ዳጋሎ ቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ ትልቁ የአል-ሁዳ ወህኒ ቤት መሰበሩ ተሰምቷል።

እስር ቤቱ ብዙ ኢትየጵየዊያን በሱዳን የፀጥታ ኃይሎች የሚታሰሩበት ሲሆን የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ እስረኞቹ እንዲለቀቁ ማድረጉን የአዲስ ዘይቤ ምንጮች ተናግረዋል።

ከካርቱም 15 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በኦምዱሩማን መንገድ የሚገኝና የወንጀለኛ ቡድን መሪዎች፣ አደንዛዥ እፅ አዘዋዋሪዎች እና ከመኖሪያ ፈቃድ ጋር በተገናኘ ብዙ ኢትዮጵያውያን የሚታሰሩበት እንደነበረ ምንጮቻችን ተናግረዋል።

የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ እስረኞቹን ማስለቀቁን ተከትሎ ሃሳባቸውን የሰጡ ምንጮች ታስረው ለነበሩት ኢትዮጵያውያን መፈታት በጎ ቢሆንም በከባድ ወንጀል የታሰሩ ሰዎችም መፈታታቸው ስጋት ፈጥሯል።

ግጭቱ ከተጀመረ ጀምሮ 15 የሚደርሱ ኢትዮጵያዊያን በጦርነቱ መገደላቸው የተገለፀ ሲሆንሲሆን በካርቱም የኢትዮጵያ ኤምባሲ በቂ መረጃ እየሰጠ ባለመሆኑና ስለተገደሉት ዜጎች ጉዳይ መንግስት ያለው ነገር አለመኖሩ በኢትዮጵያውያኑ ዘንድ ትችቶች እንዲሰነዘሩ አድርጓል።በግጭቱ መባባስ ምክንያት ሀገራት ዜጎቻቸውን ከሀገሪቱ አእያስወጡ ሲሆንአሁን የኢትዮጵያ መንግስትም ዜጎቹን ለመታደግ ሀገራዊ ግብረ ሀይል ማቋቋሙን ይፋ አድርጓል።
201 views13:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-22 13:42:41
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለጀኔራል ሰዓረ መኮንን ያስገነባውን ሐውልት እና በስማቸው የሰየመውን ፓርክ አስመረቀ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለቀድሞው የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀኔራል ሰዓረ መኮንን ያስገነባውን የመታሰቢያ ሐውልት እና በስማቸው የሰየመውን ፓርክ ዛሬ አስመርቋል፡፡የመታሰቢያ ሐውልቱ እና ፓርኩ ግንባታ የተከናወነው በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ርዋንዳ አካባቢ ነው፡፡
203 viewsedited  10:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-22 12:11:28 የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ በአዲስ አበባ ከተማ ለሚገኙ የነዳጅ ማደያ ድርጅቶች በሙሉ ጥብቅ ትዕዛዝ አስተላልፏል፡፡

ከሚያዝያ 16 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ የነዳጅ ተጠቃሚ ለሆኑ አካላት በሙሉ የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ሥርዓት ብቻ እንደሚካሄድ ያሳወቀዉ ንግድ ቢሮዉ በጥሬ ገንዘብ ክፍያ መፈጸም የተከለከለ መሆኑን አሳዉቋል፡፡

ከኤሌክትሮኒክስ ክፍያ ውጪ በተለይ በጥሬ ገንዘብ ክፍያ መፈፀም የተከለከለ በመሆኑ ቢሮው በዕለቱ ጥብቅ ክትትልና ቁጥጥር ያደርጋል ነዉ ያለዉ፡፡ይህ በመሆኑም ከወዲሁ በቂ ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ለማንኛውም የነዳጅ ተጠቃሚ አካላት የነዳጅ ሽያጭን በኤክትሮኒክስ ሥርዓት ብቻ እንዲያስተናግዱ አሳስቧል።
196 views09:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-21 18:22:37 የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ይቅርታ ጠየቀ
መግለጫው እንደሚከተለው ቀርቧል

የዒድ ሰላት ለመስገድ ከቤታችሁ ወጥታችሁ ላመለጣችሁ የከተማችንና አካባቢው ሙስሊሞች በሙሉ!!

ዛሬ በነበረው የኢድ ሰላት ፕሮግራም ላይ ለመታደም ጥሪያችንን አክብራችሁ በአንድነት  አምራችሁና ደምቃችሁ ግዙፉ የከተማችን ውበት ሆናችሁ በመዋላችሁ የተሰማንን ታላቅ ደስታ እንገልፃለን።

የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት በድጋሚ እንኳን ለ1444 ዓ.ሂ  የኢድ አልፊጥር በዓል  በሰላም አደረሳችሁ እያልን በዛሬው እለት የተሰገደው የኢድ ሰላት በሰላም፣በደስታ መጠናቀቁ ቢያስደስትም የዒድ ሰላት ከዚህ ቀደም ሲሰገድበት ከነበረው ሰአት ቀድሞ በመሰገዱ የዒድ ሰላት ላመለጣችሁ የከተማችን ሙስሊሞች ይቅርታ እንጠይቃለን።

በትናንትናው እለት ከፌደራል መጅሊስ ጋር በጋራ በሰጠነው መግለጫ ሸሪአውን በጠበቀ መልኩ በእለቱ ንግግሮች እንደማይኖሩና በማለዳ ሰግደን እንደምንበተን ለህዝባችን ገልፀን ቢሆንም በእለቱ የተገኙት ሚድያዎች በአብዛኛው በሚባል መልኩ ትኩረት ሰጥተው ባለማስተላለፈቸው እና ከሚዲያዎቹ በተጨማሪ ሌሎች አማራጮችን በሰፊው  ባለመጠቀማችን ችግሩ እንዲፈጠር ምክንያት እንደነበሩ ተረድተናል።

በተጨማሪም ከዚህ ቀደም ሲሰገድበት የነበረውን ሂደትን ለማሻሻል በሚል መልካም እሳቤ በተፈጠረ ክፍተት ሰላት ላመለጣችሁ ሁሉ ታላቅ ይቅርታ እየጠየቅን በቀጣይ የሚስተካከል መሆኑን ህዝባችን እንዲገነዘብ እያልን፣
በበጎና ገንቢ በሆነ መልኩ አስተያየታችሁን ለለገሳችሁን የከተማችን ነዋሪዎች ምስጋና እያቀረብን በዓሉ የሰላም

የደስታ፣የመተዛዘን፣የመረዳዳት እንዲሆን መልካም ምኞታችንን ለመግለፅ እንወዳለን።
222 views15:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 19:45:15 #AddisAbaba

ከለሊቱ 10 ሰዓት ጀምሮ መንገዶች ይዘጋሉ።

1444ኛው የኢድ አልፈጥር ረመዳን በዓል የኢድ ሶላት ተጀምሮ እሰከሚጠናቀቅ ለተሸከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች የፀጥታ እና ደህንነት የጋራ ግብረኃይል ይፋ አድርጓል።

አሽከርካሪዎች የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር ከዚህ በታች የተዘረዘሩት መንገዶች የሚዘጉ መሆኑን በማወቅ አማራጭ መንገዶችን ተጠቀሙ ብሏል።

የሚዘጉ መንገዶች ፦

- ከቦሌ አየር መንገድ በሚሊኒየም አዳራሽ ወደ ስታዲዮም የሚወስደው መንገድ ደንበል ሲቲ ሴንተር ኦሎምፒያ አደባባይ አከባቢ፤

- ከመገናኛ ፣ በሃያ ሁለት ወደ መስቀል አደባባይ እንዲሁም ከቦሌ መድሃኒያለም፣ በአትላስ ሆቴል ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኡራኤል ቤተ-ክርስቲያን አካባቢ፤

- ከአራት ኪሎ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ባሻ ወልዴ ችሎት ወይም ፓርላማ መብራት፤

- ከፒያሣ አካባቢ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ቸርችል ጎዳና ቴዎድሮስ አደባባይ፤

- ከተክለ ሀይማኖት በሜትሮሎጂ ወደ ስታዲዮም የሚወስደው መንገድ ሜትሮሎጂ መስሪያ ቤት አካባቢ፤

- ከተክለ ሀይማኖት ፣ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የሚወስደው መንገድ ጥቁር አንበሳ የኋላ በር አካባቢ፤

- ከሲኒማ ራስ በጎላ ሚካኤል ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ጎላ ሚካኤል መስቀኛ፤

- ከጌጃ ሰፈር ፣ ጤና ጥበቃ፣ ብሄራዊ ቲያትር የሚወስደው መንገድ ጎማ ቁጠባ፤

- ከባሻ ወልዴ ችሎት በኦርማ ጋራዥ ወደ ፍል ውሃ መስኪድ የሚወስደው መንገድ ንግድ ማተሚያ ቤት ፤

- ከጎፋ በቅዱስ ቂርቆስ ቤ/ክ ወደ ለገሐር አዲሱ መንገድ የሚወስደው መንገድ ቅዱስ ቂርቆስ ቤ/ክ መስቀለኛው ላይ፤

- ከጦር ኃይሎች ፣ ልደታ ፣ ፖሊስ ሆስፒታል ሜክሲኮ አደባባይ ፤

- ከሳሪስ በጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ ለቀላል መኪና የቀድሞ አራተኛ ክፍለ ጦር አካባቢ እንዲሁም ለከባድ መኪና አጎና ሲኒማ አካባቢ #ይለፍ_ለሌላቸው ተሽከርካሪዎች ከለሊቱ 10 ሰዓት ጀምሮ ዝግጅቱ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ዝግ ይሆናሉ።

ህብረተሰቡ የትራፊክ ፖሊስ አባላት በሚጠቁሙት አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀም እና ለትራፊክ ፖሊስ አባላት ትዕዛዝ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግ ግብረኃይሉ ጥሪ አቅርቧል።
123 views16:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 18:41:05 #BREAKING

የዒድ አልፈጥር በዓል #ነገ መሆኑ ታውቋል።

የሸዋል ወር ጨረቃ በሳኡዲ አረቢያ በቱሚናር እና ሱዳይር ዛሬ ሀሙስ በመታየቷ የዒድ አልፈጥር በዓል ነገ ጁምዓ / አርብ ይውላል።

እንኳን ለ1 ሺህ 444ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

ምንጭ፦ Haramain Sharifain
155 views15:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ