Get Mystery Box with random crypto!

Ewnet Media

የቴሌግራም ቻናል አርማ ewnetmedia1 — Ewnet Media E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ewnetmedia1 — Ewnet Media
የሰርጥ አድራሻ: @ewnetmedia1
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.06K

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2023-04-28 09:55:58 ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከሱዳን ተቀናቃኝ ኃይሎች መሪዎች ጋር በስልክ ተወያዩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከሱዳን ጦር ኃይሎች መሪ ጄኔራል አብደልፈታህ አልቡርሃን እና ከሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች መሪ ጄኔራል ሞሐመድ ሐምዳን ደጋሎ ጋር በስልክ መወያየታቸውን ገለጹ።

ታላቁ የሱዳን ሕዝብ ሰላም ያስፈልገዋል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ሁለቱ መሪዎች ልዩነቶቻቸውን በመግባባት እንዲፈቱ እና ለሀገራቸው መረጋጋትን ማምጣት በሚችሉበት ሁኔታ ላይ መወያየታቸውን ገልጸዋል።
269 views06:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-27 20:54:48
የአማራ ብልጽግና ጽሕፈት ቤት ኃላፊው ግርማ የሽጥላ ተገደሉ

አቶ ግርማ የሺጥላ ከመሃልሜዳ ሲመጡ ጓሳ በተባለ አካባቢ በተተኮሰባቸው ጥይት መገደላቸውን ምንጮች ገልፀዋል።

መሃልሜዳ ሆስፒታል ለህክምና ቢገቡም ህይወታቸውን ማትረፍ እንዳልተቻለ ከቅርብ ሰዎች ለማወቅ ተችሏል።

ይህንንም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ አረጋግጠዋል።

"ሐሳብን በሐሳብ ማሸነፍ ያቃታቸው አካላት የወንድማችንን የግርማ የሺጥላን ነፍስ ነጥቀዋል።  ልዩነትን በሠለጠነ መንገድ መፍታት ባህል በሆነበት ክፍለ ዘመን፣ በሐሳብ የተለየንን ሁሉ በጠመንጃ ለማሳመን መነሣት የጽንፈኝነት የመጨረሻው ጥግ ነው። ተወልዶ ባደገበት አካባቢ ፣ ከእኛ የተለየ ሐሳብ ማሰብ አልነበረበትም ብለው የሚያምኑ ነውጠኛ ጽንፈኞች የፈጸሙት አስነዋሪና አሰቃቂ ተግባር፣ ጽንፈኝነትን በጊዜ ታግለን ካላስወገድነው ወደ መጨራረስ እንደሚወስደን ጉልሕ ማሳያ ነው።
ነፍስህ በሰላም ትረፍ" -

  ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ
282 viewsedited  17:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-27 13:48:14 የአማራ ክልል ፕሬዝደንት ጨምሮ የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች መቀሌ ገቡ !!

አቶ አደም ፋራህ የተመራና የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮችና ሌሎች ባለስልጣናት የተካተቱበት ቡድን ወደ መቀሌ ተጓዘ።

በቡድኑ ውስጥ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ፣ የአፋር ክልል፣ የኦሮሚያ ክልል፣ የደቡብ ክልል፣ የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ የጋምቤላ ክልል፣ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል፣ የሶማሌ ክልል፣ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድሮች ይገኙበታል።

በተጨማሪም የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የድሬዳዋ ከተማ ከንቲባ ከድር ጁሀርና ሚኒስትሮች እና ሌሎች የሥራ ኃላፊዎች አብረው ተጉዘዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ለሰሜኑ ጦርነት የሠላም ስምምነት አስተዋጽኦ  ላበረከቱ አካላት የዕውቅና መርሀ-ግብር ሲከናወን  የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች ወደመቀሌ በማቅናት መቀራረቡን እንዲያጠናክሩ ተናግረው እንደነበር የሚታወስ ነው።
268 views10:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-27 13:20:14 #Update

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ምዝገባ ነገ ሚያዚያ. 20/2015 ዓም ከቀኑ 11:30 ላይ እንደሚያበቃ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

አገልግሎቱ እስካሁን ያልተመዘገቡ ተፈታኞች እስከ ነገ እንዲመዘገቡ አሳስቧል።

በማንኛውም ምክኒያት ያልተመዘገቡ ተፈታኞችን " ከነገ በኋላ አላስተናግድም " ሲል አሳውቋል።

የ2015 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የሚሰጥ ሲሆን ፈተናው የሚሰጥበት ጊዜ ከምዝገባው መጠናቀቅ በኃላ ይፋ ይደረጋል።

የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት የሆናችሁ ተፈታኞች እስካሁን ድረስ የመፈተኛው ቀን ይፋ #አለመደሩግን በማወቅ ከሀሰተኛ መረጃዎች በመራቅ በተጋጋ መንፈስ ዝግጅታቸሁን አድርጉ።
245 views10:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-26 20:57:56 የሱዳን ስደተኞች በመተማ በኩል እየገቡ ነው

በሀገረ ሱዳን የእርስ በእርስ ግጭት ምክንያት የተለያዩ ሀገር ዜጎች በመሸሽ በምእራብ ጎንደር ዞን መተማ ዮኋንስ ከተማ በኩል እየገቡ ነው።

በሀገረ ሱዳን የእርስ በእርስ ግጭት ምክንያት የተለያዩ ሀገር ዜጎች ከግጭቱ በመሸሽ በምእራብ ጎንደር ዞን መተማ ዮኋንስ ከተማ በኩል እየገቡ ነው። የተፈጠረውን አለመረጋጋት ሸሽተው የሚመጡ የተለያዩ የውጭ ሀገር ዜጎችን የምእራብ ጎንደር ዞን መተማ ዮኋንስ ከተማ በሰላም እያስተናገደች ነው።

ሱዳን ላይ በተፈጠረው የውስጥ አለመረጋጋት ምክኒያት ጦርነቱን ሸሽተው ከካርቱም ወደ ጎረቤት ሀገር ኢትዩጵያ የሱዳን ዜጎችን ጨምሮ የ23 ሀገራት የተለያዪ ሃገራት ዜጎች እንደገቡና ወደ ሚፈልጉት አካባቢ እየሄዱ ይገኛሉ።

በዚህም የምዕራብ ጎንደሯ የፍቅር ከተማ መተማ ዮሃንስ ከተማ እንግዶቿን እያስተናገደች ሲሆን በቀን ከ15-20 የሚሆኑ መኪናዎች ወደ ጎንደር እየሄዱ ይገኛሉ ። በዚህ የጦርነት ስጋት ሺሽትም ህፃናት፣ ሴቶች እና አቅመ ደካሞች ይገኙበታል። የመተማ ዮሃንስ ከተማ አስተዳደር፣ የዞን ከፍተኛ አመራሮች፣ የሚመለከታቸው የፀጥታ አካላትም ዜጎች ያለምንም እንግልት ወደ ሚፈልጉት አካባቢ እንዲደርሱ ሰብአዊ ተግባራትን እያከናወኑ እንደሆነ በቦታው ተገኝተን አረጋግጠናል ሲል የምዕራብ ጎንደር ዞን ኮምኒኬሽን ዘግቧል።
247 views17:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-26 14:17:27 20ኛ መደበኛ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ ውሳኔዎች

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 20ኛ መደበኛ ስብሰባው በመካከለኛ ዘመን (2016 - 2020) የማክሮ ኢኮኖሚ እና ፊሲካል ማዕቀፍ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ፡፡

ምክር ቤቱ በዛሬው መደበኛ ስብሰባው የተወያየው በመካከለኛ ዘመን /2016-2020/ የማክሮ ኢኮኖሚ እና ፊሲካል ማዕቀፍ ላይ ሲሆን ማዕቀፉ በዋናነት የመንግስት በጀት ከማክሮ ኢኮኖሚ ዓላማዎችና ታሳቢዎች ጋር ተጣጥሞ የተዘጋጀ መሆኑን፣ የመካከለኛ ዘመን የመንግስት ገቢና ወጪ እንዲሁም የፊሲካል ሚዛን የፖሊሲ አቅጣጫዎችን ለመለየትና ለማመላከት የሚያገለግል የበጀት ዕቅድ መሳሪያ ሆኖ የ2016 የፌዴራል መንግስት ዝርዝር በጀት የሚዘጋጅበትን ጥቅል የገቢ ትንበያ፣ የወጪ ጣሪያ፣ የክልላዊ መንግስታት የበጀት ድጋፍ ጣሪያ እና የፊሲካል ጉድለት መጠንን የሚያመላክት ሆኖ መዘጋጀቱን ምክር ቤቱ አረጋግጧል፡፡

በመሆኑም ማዕቀፉ ባለፉት ዓመታት በሀገሪቱ በተከሰቱ ችግሮች ምክንያት የተጋረጠውን የፊሲካል ስጋት ለመቅረፍ እና የፊሲካል ጤናማነትን ለማረጋገጥ የሚያስችል የፋይናንስ አጠቃቀም ስልት ተግባራዊ እንዲደረግ የሚያስችል መሆኑን በማመን፣ የመንግስት ገቢና ወጪ እንዲመጣጠን ማድረግን ታሳቢ ያደረገ መሆኑም ግምት ውስጥ በማስገባት ምክር ቤቱ በማዕቀፉ ላይ ከተወያየ በኋላ ግብዓቶችን በማከል በስራ ላይ እንዲውል በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡
246 views11:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-26 13:41:58 ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ከኢትዮ ቴሌኮም ለተከራየው የቴሌኮም መሠረተ ልማት 743.6 ሚሊዮን ብር ክፍያ ፈጽሟል።

በኢትዮጵያ ለሚሰማሩ የውጭ የቴሌኮም መሠረተ ልማት አልሚዎች የቴሌኮም መሠረተ ልማትን ከሀገር ውስጥ ኦፕሬተሮች የመከራየት አስገዳጅ አሠራር ተግባራዊ መደረጉ ይታወሳል። ይኽም የኢትዮ ቴሌኮም የገበያ አቅምን ፈጥሯል። 

በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የውጭ የግል የቴሌኮም አገልግሎት ፈቃድ ያገኘው ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በዚሁ አስገዳጅ ሕግ መሠረት የራሱን የቴሌኮም መሠረተ ልማት መገንባት ስለማይችል የኢትዮ ቴሌኮምን መሠረተ ልማት በኪራይ የመጠቀም ግዴታ ውስጥ ገብቷል።

በዚህም መሠረት ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የኢትዮ ቴሌኮምን መሠረተ ልማት መጠቀም የጀመረ ሲሆን፣ በ2015 ዓ.ም. የመጀመሪያ ስድስት ወራት ውስጥም ከኢትዮ ቴሌኮም ለሚያገኘው የመሠረተ ልማት መጋራት አገልግሎት 743.6 ሚሊዮን ብር ክፍያ ፈጽሟል። (ሪፖርተር)

#Telecom
239 views10:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-26 09:33:01 ሰበር ዜና

በታንዛኒያ ዛንዚባር ደሴት በኢትዮጵያ መንግስት እና በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት መካከል የሰላም ውይይት ዛሬ ተጀመረ።

በታንዛኒያ የሰላም ድርድር ዛሬ ማለዳ መጀመሩን በስፍራው የነበሩ ምንጮች ለቢቢሲ ተናግረዋል። በውይይቱ ላይ የሁለቱም ወገኖች ተወካዮች ስድስት ሰዎች እየተሳተፉ መሆናቸውን ምንጮች ለቢቢሲ ተናግረዋል።

በመንግስት በኩል ወደ ታንዛኒያ የተጓዘው የልዑካን ቡድን አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን እና ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ እንደሚገኙበት ቢቢሲ ዘግበዋል።

በኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት በኩል አንጋፋው የታሪክ ምሁር ፕሮፌሰር መሃመድ ሃሰን እና የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ዋና አዛዥ አማካሪ ሚስተር ጂሬኛ ጉዳታ እና አቶ አብዲ ጠሃ እና ሌሎችም መገኘታቸውን ፋስት መረጃ ከቢቢሲ የተገኘው መረጃ ያመለክታል። ሁለቱም ተደራዳሪ አካላት ንግግር ስለመጀመሩ ማረጋገጫ ቢሰጡም ዝርዝር መረጃ ይፋ አላደረጉም ፤ የታንዛኒያ ባለስልጣናትም ስለድርድሩ የተለየ መረጃ ከመስጠት ተቆጥበዋል።
258 views06:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-25 17:39:30 #Ethiopia

'' መከላከያ ሚኒስቴር ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ተማሪዎች የውትድርና ስልጠና ወስደው ብሔራዊ አገልግሎት እንዲሰጡ ማድረግ ይችላል " - ዲማ ኖጎ ( ዶ/ር)

መከላከያ ሚኒስቴር ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ተማሪዎች  በፈቃዳቸው ወታደራዊ ስልጠና ወስደው ብሔራዊ አገልግሎት እንዲሰጡ ሊያደርግ እንደሚችል በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነት እና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዲማ ኖጎ (ዶ/ር) አሳውቀዋል።

ሰብሳቢው ይህንን ያሳወቁት ዛሬ የሕዝብ ተወካዮቸ ምክር ቤት የመከላከያ ሠራዊት አዋጅን ለማሻሻል  የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ  ባጸደቀበት ወቅት ነው፡፡

ዶ/ር ዲማ  ናጎ ምን አሉ ?

" ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ዕድሜያቸው 15 ዓመት የሞላቸው እና የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ወይም የዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ተማሪዎችን በፈቃዳቸው ወታደራዊ ስልጠና ወስደው ለሁለት ዓመት ብሔራዊ አገልግሎት እንዲሰጡ ሊያደርግ ይችላል።

ተማሪዎች በፈቃዳቸው በመደበኛ የመከላከያ ሠራዊት ወይም የብሔራዊ ተጠባባቂ ኃይል አባላት የሚሆኑ ከሆነ፤ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ተያያዥ መብቶችንና ጥቅሞች እንዲጠበቁላቸው ያደርጋል። "

የተሻሻለው የመከላከያ ሠራዊት አዋጅ የሀገር መከላከያ ሠራዊት ከማንኛውም የፖለቲካ ወገንተኝነት ነጻ ሆኖ የተጣለበትን ሀገር የመጠበቅ ተልዕኮ በአስተማማኝ ሁኔታ እንዲወጣ የሚያስችል ነው ተብሏል።

የተሻለ ሠራዊት ለመገንባት ማነቆ የሆኑ ሕግ ማዕቀፎችን እና ተቋማዊ አስተሳሰቦችን በመፈተሽ ለሀገር እና ሕዝብ ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው ነው የተገለፀው።

ምክር ቤቱ በተሻሻለው ረቂቅ አዋጅ ላይ ከተወያየ በኋላ ረቂቅ አዋጁን አዋጅ ቁጥር 1286/2015 አድርጎ   በስድስት ድምጸ-ተኣቅቦ እና በአብላጫ ድምጽ አጽድቆታል፡፡

Via HoPR
263 views14:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-25 17:30:03 የተሻሻለው የመከላከያ ሰራዊት አዋጅ ጸደቀ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 2ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 14ኛ መደበኛ ጉባዔውን ዛሬ አካሂዷል፡፡

አዋጁ÷ የመከላከያ ሰራዊት ከፖለቲካ ወገንተኝነት ነፃ ሆኖ ሀገርን የመጠበቅ ተልዕኮውን በአግባቡ እንዲወጣ ማድረግ የሚያስችሉ  የሕግ ማዕቀፎች እንደተካተቱበት ተጠቁሟል፡፡

በተጨማሪም አዋጁ ኅብረ ብሔራዊ ተዋፅኦውን የጠበቀ የዘመነ ሰራዊት ለመገንባት ማነቆ የሆኑ የሕግ ማዕቀፎችን ማሻሻል እንደሚያስችል ተገልጿል፡፡

ተሻሽሎ የቀረበው አዋጅ ያሉትን ችግሮችና ክፍተቶች በመሙላት ሊያሠራ የሚችል የሕግ ማዕቀፍ፣ አደረጃጀት እና አሠራር ለመዘርጋት የሚያስችል መሆኑን በማመን ምክር ቤቱ በአብላጫ ድምጽ አጽድቆታል፡፡

የመከላከያ ሠራዊቱን የሚመጥን ራሱን የቻለ የመከላከያ አዋጅ ሊወጣ እንደሚገባ ቀደም ሲል በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ሲጠየቅ መቆየቱ ይታወሳል፡፡

ለመከላከያ ሠራዊት ክብር የሚመጥን የደመወዝና የካሳ ክፍያ እንዲሁም ሌሎች ጥቅማ ጥቅሞች በሚገባ እንዲከበሩ ራሱን ችሎ የመከላከያ አዋጅ ቢወጣ የጎላ ፋይዳ እንደሚኖረውም ሲገለጽ ቆይቷል፡፡

ከጡረታ መውጫ ዕድሜ ጣሪያ አወሳሰንና የጡረታ ዕድሜ ከማራዘም ጋር በተገናኘ፣ ከሠራዊት መብትና ጥቅማ ጥቅሞች አንጻር መታየት ያለባቸውን ጉዳዮች በአዋጅ ማሻሻያው እንዲካተቱ ትኩረት ከተሰጠባቸው ጉዳዮች መካከል ናቸው፡፡
229 views14:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ