የዒድ አልፈጥር በዓል መቼ ነው ? የፌዴራል ጠቅላይ ሼሪዓ ፍርድ ቤት ፥ የዒድ አልፈጥር በዓል ጨ | Ewnet Media
የዒድ አልፈጥር በዓል መቼ ነው ?
የፌዴራል ጠቅላይ ሼሪዓ ፍርድ ቤት ፥ የዒድ አልፈጥር በዓል ጨረቃ ዛሬ ሀሙስ ማታ ከታየች ነገ፣ ካልታየች ደግሞ ቅዳሜ ይከበራል ሲል አሳውቋል።
ይህ ያለው ዛሬ በሰጠው መግለጫ ነው።
1 ሺህ 444ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል ፤ ለኢትዮጵያና ለመላው ዓለም ህብረተሰብ የሰላም፣ የደስታና የፍቅር እንዲሆን መልካም ምኞቱን የገለፀው ሼሪዓ ፍርድ ቤቱ ሙስሊሙ ህብረተሰብ በዓሉን ሲያከብር ያጡና የተቸገሩ ወገኖችን በማሰብና በመርዳት እንዲሆን ጥሪ አቅርቧል።
#ኤፍቢሲ