Get Mystery Box with random crypto!

Ethio University

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiouniversty1 — Ethio University E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiouniversty1 — Ethio University
የሰርጥ አድራሻ: @ethiouniversty1
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 4.85K
የሰርጥ መግለጫ

ለማንኛውም አይነት የማስታወቂያ ስራ እና ክሮስ(Cross)
💰💰 @Cozboy0 💰💰
ያናግሩን🎫🎟🎪🎪🎪🎪

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 32

2022-10-04 21:19:13 የትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የሚፈትኑ መምህራንን ምደባ አካሄድ

መምህራኑ ወደ ተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ወዳሉ የመፈተኛ ማዕከላት የተመደቡ ሲሆን ከዚህ ጋር በተያያዘ ሚቀርቡ ማንኛውም አይነት ጥያቄዎችን እንደማያስተናግዱ ዩኒቨርሲቲዎች እያሳወቁ ይገኛሉ።

በሚኒስተሮች ም/ቤት ደንብ ቁጥር 260/2004 አንቀፅ 9(2) በተሰጠው ሥልጣንና እንዲሁም በሀገር አቀፍ የፈተና አስተዳደር መመሪያ ቁጥር 1/2012 መሰረት ፈተና ለመፈተን ወደ ሌላ መፈተኛ ማዕከል የተመደበ መምህር በተዘጋጀው የፈተና አሰጣጥ እና አፋጻጸም ማንዋል 01/2014 መሰረት የፌደራል ት/ሚ/ር እና ፈተናዎች አገልግሎት ኤጄንሲ ወደ ተመደበበት ቦታ የመገኘት ኃላፊነት ያለበት መሆኑን ይገልጻል፡፡

በመመሪያው መሰረት የዩኒቨርሲቲ መምህራን ወደ ተመደቡበት አካባቢ ሄደው የተጣለባቸው #ሀገራዊ_ኃላፊነት የመወጣት ግዴታ ያለባቸው መሆኑ የተገለፀ ሲሆን ከጉዞ ጋር ተያይዞ የሚመጣ ማንኛውንም ጥያቄ እንደማያስተናግዱ ከወዲሁ እያሳወቁ ይገኛሉ።

ትላንት የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በሰጡት መግለጫ ፤ " ከዚህ በፊት የነበረውን የኔ አካባቢ ሰው ፣ የኔ ዘመድ የሚለውን ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት ማንኛውም የአንድ አካባቢ ተወላጅ እዛው አካባቢ ያሉ ተማሪዎችን አይፈትንም። ማንኛውም የአንድ ዩኒቨርሲቲ አስተማሪ እራሱ የሚያስተምርበት ዩኒቨርሲቲ ውስጥ አይፈትንም " ሲሉ አሳውቀዋል።
92 views18:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-03 14:49:34 በ12ኛ ክፍል ፈተና አሰጣጥ ዙሪያ ለጋዜጠኞች መግለጫ ተሰጠ

ትምህርት ሚኒስቴር የ2014ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና አሰጣጥ ዙሪያ ማብራሪያና መግለጫ ሰጥቷል።የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ ፈተናውን በተሳካ ሁኔታ ለመስጠት አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉን የገለጹ ሲሆን ሂደቱ ተማሪዎች በራስ ጥረት ብቻ ውጤታማ የሚሆኑበት ነው ብለዋል።

ከዚህም መካከል የፈተናው ዝግጅትና ህትመት በቴክኖሎጂ ታግዞ በከፍተኛ ጥንቃቄና ከደህንነት ስጋት ነፃ በሆነ መልኩ መከናወኑን በመግለጫቸው ተናግረዋል።እስከ አሁን በነበረው የቅድመ ዝግጅት ሂደትም ከሚመለከታቸው የፌደራል እና የክልል መንግስታት የስራ ሃላፊዎች ጋር በቅንጅት እየተሰራ እንደሆነም ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

በመግለጫው ሀገር አቀፍ ፈተናው በሁለት ዙር የሚሰጥ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን በዚህም በመጀመሪያው ዙር የሶሻል ሳይንስ ተማሪዎች ከመስከረም 30,2015 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 02,2015 ዓ.ም ፈተናውን ሲወስዱ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ከ ጥቅምት 8,2015 ዓ.ም እስከ 11,2015 ዓ.ም ፈተናውን ይወስዳሉ ተብሏል።

ተፈታኞችም ፈተናው ከሚሰጥበት ቀን በፊት ባሉት ሶስት ቀናት በሚፈተኑበት ዩኒቨርስቲዎች መገኘት እና ኦረንቴሽን መውሰድ እንደሚጠበቅባቸውም ተነግሯል።ከፈተናው ቀን በፊት ባሉት ቀናት ተማሪዎችን ወደ ፈተና ቦታ የማምጣት እና ፈተናው እንዳለቀም ተማሪዎችን ወደየመጡበት አካባቢ የመመለስ ስራ እንደሚሰራም ተገልጿል።

በተጨማሪም በመግለጫው ተፈታኞች ወደ ፈተና ቦታ ሲመጡ ይዘዋቸው እንዲመጡ የተፈቀዱ እና የተከለከሉ ቁሳቁሶች የተገለፁ ሲሆን ከነዚህም መካከል የዲጅታል ቴክኖሎጂ ውጤቶች( ስልክ፣ ላፕቶፕ፣ ፍላሽ.. ወ.ዘ.ተ)፣ ስለታማ ቁሳቁሶች እና ሌሎችም በፈተና ቦታ የተከለከሉ ቁሳቁሶች መሆናቸው ተገልጿል።

ተማሪዎች እና ወላጆች ከተሳሳቱ መረጃዎች እራሳቸውን በማራቅ ለፈተናው አሰጣጡ ስኬት የበኩላቸውን እንዲወጡም በመግለጫው ተጠይቋል።የ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን ከመስከረም 30,2015 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 11,2015 ዓ.ም በዩኒቨርስቲዎች ውስጥ ይሰጣል።
258 views11:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-03 14:09:32 የ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን በተሳካ ሁኔታ ለመስጠት ዝግጅት መደረጉ ተገለጸ

የትምህርት ሚኒስቴር የ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በዩኒቨርሲቲዎች ለመስጠት ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን ገልጿል፡፡

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ፈተናውን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል።

በመግለጫውም ፈተናው በዩኒቨርሲቲ ቅጥር ግቢ የሚሰጠው፥ ባለፉት አመታት የፈተና አሰጣጡን ሲያውክ የነበረውን የፈተና ስርቆትና የሃሰተኛ መልስ ስርጭትን ለመከላከል በማሰብ መሆኑን አስታውቋል።

ለዚህም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሙሉ ዝግጅት ማድረጉን ነው የገለጸው።

ተፈታኞች በአካባቢያቸው በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ፈተናውን የሚወስዱ ሲሆን በተቀመጡ መመሪያዎች መሰረት የፈተናውን ደህንነት ለማስጠበቅ የተወሰነውን ውሳኔ አክብረው እንዲፈተኑ፤ ወላጆችም ለዚህ አላማ መሳካት አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ ተጠይቋል።

(ኤፍ ቢ ሲ)
263 views11:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-29 19:54:32 የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎችን የሚያጓጉዙ ተሽከርካሪዎች እየተዘጋጁ እንደሚገኝ ተገለፀ

ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ፈተና ለሚወስዱ 12ኛ ክፍል ተማሪዎች የትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠት እየተሰራ እንደሚገኝ የምስራቅ ጎጃም ዞን አስታውቋል ።

በምስራቅ ጎጃም ዞን ለሚፈተኑ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ተሽከርካሪዎች እንዲሁም የመፈተኛ ተቋማት በማዘጋጀት በኩል ግብረሃይል ተቋቁሞ እየተሰራ እንደሚገኝ የምስራቅ ጎጃም ዞን ትምህርት መመሪያ ሀላፊ አ/ቶ ጌታሁን ፈንቴ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል ። በዞኑ ተማሪዎች የሚፈተኑባቸው አምስት ተቋማት እየተዘጋጁ እንደሚገኝ ተገልጿል ።

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከመስከረም 30 ጀምሮ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እንደሚሰጥ ቀደም ብሎ በትምህርት ሚኒስቴር መገለፁ ይታወቃል ።


#ዳጉ_ጆርናል
555 views16:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-29 19:01:46
በዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ላይ ከአንድ ሚልዬን በላይ ተፈታኞቹ ፈተናውን የሚወስዱ ሲሆን ከ200,000 የማይበልጡት ተማሪዎች ብቻ ወደ ዩንቨርስቲ ይገባሉ ምክንያቱም የኢትዮጵያ ዩኒቨርስቲዎች የመቀበል አቅማቸው ከ200,000 የማይበልጥ በመሆኑ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ የዩቲውብ ቻናላችንን ይጎብኙ

https://youtube.com/channel/UCgmzpzIOElQB2v1JZtkjKQg?sub_confirmation=13
508 views16:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-27 17:07:11 #ዪኒፎርም ግዴታ ነው

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ቅድመ ዝግጅት ላይ ፈተናዉን ለማስተግበር ከተቋቋመዉ ኮማንድ ፖስት አባላት ጋር ውይይት አካሄደ፡፡ በውይይቱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ማኔጅመንት አባላት ፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፣ የኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ ፣ የኢትዮጵያ የሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ፣ የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና የፌደራል ቴክኒክና እልጠና ኢንስቲትዩት ሀላፊዎች እና የክፍለ ከተማ የትምህርት ጽፈት ቤት ሀላፊዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

ዘንድሮ ፈተናው በሀገር አቀፍ ደረጃ ከመስከረም 30/2015 ዓ.ም ጀምሮ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እንደሚሰጥ ቀደም ብሎ በትምህርት ሚኒስቴር የተገለጸ ሲሆን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርም ፈተናውን አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፤ ኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ ፤ ኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ፣ አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና ፌደራል ቴክኒክና እልጠና ኢንስቲትዩት ለመስጠት የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተሰሩ መሆኑ ተገልጻል፡፡

በአዲስ አበባ 49,203 ተማሪዎች ፈተናውን ለመውሰድ መመዝገባቸውን ተገልጿል ።

      
246 views14:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-25 18:44:17 " የምንሄድበት የለም፤ መፍትሄ ይፈለግልን " - ተማሪዎች

የ12ኛ ክፍል ፈተና በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ መሰጠቱን ተከትሎ ፈተና የሚሰጥባቸው ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ማንኛውም ተማሪ እንዳይገኝ ተብሏል።

ይህ ሁኔታ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የሚገኙ የፀጥታ ችግር ካለባቸው አካባቢዎች የመጡ ተማሪዎችን ጭንቀት ውስጥ የከተተ ሲሆን ተማሪዎቹ መፍትሄ ይፈለግላቸው ዘንድ ጠይቀዋል።

አንድ የቲክቫህ ቤተሰብ አባልና ቤተሰቦቹ በሰሜን ኢትዮጵያ የጦርነት ቀጠና ውስጥ ያሉ የዩኒቨርሲቲ ተማሪ፤ "ወደ መጡበት ቦታ መመለስ የማይችሉ ተማሪዎች ምን ሊደረጉ ነው ? ጦርነት ካለበት ቦታ የመጣን ተማሪዎች አለን ድምፃችን ተሰምቶ መፍትሄ ይፈለግልን፤ ወደ ቤታችን መሄድ አንችልም፤ መሄጃም የለንም" ብሏል።

ሌሎችም ተማሪዎች በተመሳሳይ መሄጃቸው እንደጨነቃቸው ገልፀዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በአንድ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ብቻ 50 የፀጥታ ችግር ካለባቸው አካባቢዎች የመጡ ተማሪዎች መኖራቸው ለማወቅ የቻለ ሲሆን ዩኒቨርሲቲው ለእነዚህ መሄጃ ለጠፋቸው ተማሪዎች ምን አሰቧል በሚል ለዩኒቨርሲቲው አስተዳደር የቅርብ ሰው ጥያቄ አቅርቦ ነበር።

እኚሁ ሰው ዩኒቨርሲቲው ለትምርህት ሚኒስቴር ጥያቄ አቅርቦ ከግቢ ይውጡ እንደተባለና ምናልባት ከፈተና መለስ እንደሚመለሱ አስረድተዋል።

መሄጃ የሌላቸው ተማሪዎች እስከዛ የት እንዲያርፉ ታስቧል ለሚለው ጥያቄ፤ ከግቢ ወጥተው ወደየ መጡበት/ቤተሰብ ጋር ይሂዱ መባሉን ገልፀዋል። በዚህ ጉዳይ ሚኒስቴሩ አቅጣጫ ቢያስቀምጡ ጥሩ እንደሆነ ጠቁመዋል።
379 views15:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-22 11:45:29 ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በሙሉ

የሁለተኛ ደረጃ ማጠናቀቂያና ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ተፈታኞች በሙሉ:-

2014/15 የኢትዮ ዩኒቨርሲቲ መግቢያና
የሁለተኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ ፈተና ተፈታኞች ወደ ተመደቡበት ካምፖስ ጉዞ ሲያደርጉ #መያዝ #የተፈቀደላቸው፣#መያዝ #የተከለከሉ እና #የጊዜ #ሠሌዳ እንደሚከተለው ያለው ሲሆን ተማሪዎች ከወዲሁ ራሣችሁን እንድታዘጋጁ ይሁን።

❶#መያዝ #የተፈቀደላቸው
አንሶላ፣
ትራስ ጨርቅ፣
የማታ ልብስ፣
ደረቅ ምግብ፣
ልብስ፣ቦርሳ፣
የመፈተኛ ካርድ፣እርሳስ፣ላጲስ፣የማስታወሻ ደብተር፣ባዶ ወረቀት፤መጽሐፍ

❷፣#መያዝ #የተከለከሉ
ማንኛውም ድምፅ የሚቀዳ፤ቪዲዮ የሚቀዳ ወይም ፎቶግራፍ የሚያነሳ፤
ካሜራ
ማንኛውም ከቴሌ መስመርም ይሁን ከቴሌ ውጭ መልዕክት በድጂታል ቴክኖሎጂ መቀበያ ወይም ማስተላለፊያ ውጤቶች(ታብሌት፣ኮሚፕዩተር፣ላብቶፕ፣ ስልክ፣አይፓድ፥ሃርድ ዲስክ፣ፍላሽ)

❸ #የጊዜ #ሠሌዳ
ማህበራዊ ሳይንስ $social science dep't
➤26_28/1/2015 ዩኒቨርስቲ መግቢያ
➤29/01/2015 ኦሬንተሽን
➤30/01/2015_02/02/2015 ፈተናው የሚሰጥበት ጊዜ ይሆናል።

የተፈጥሮ ሳይንስ Natural Science dep't
➤05_06/2/2015 ዩኒቨርስቲ መግቢያ
➤07/02/2015 ኦሬንተሽን
➤08/02/2015_11/02/2015 ፈተናው
የሚሰጥበት ጊዜ ይሆናል።

ትምህርት ሚኒስቴር
መልካም እድል!
574 views08:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-15 08:46:07 በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በዩኒቨርሲቲዎች መሰጠቱ በርካታ ጠቀሜታዎች እንደሚኖሩት  የፈተናዎች አገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር እሸቱ ከበደ ገልፀዋል፡፡

የፈተና ስርቆትና ኩረጃ  ላይ ከፍተኛ ቁጥጥር በማድረግ ተማሪዎች የራሳቸውን ብቻ እንዲሰሩ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ ፈተናውን በማጓጓዝ ወቅት የሚያጋጥሙ ችግሮችንም ለመፍታት ትልቅ እገዛ እንዲሚኖረውም አብራርተዋል፡፡

ተማሪዎችን በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ መፈተኑ የፈተናውን ሂደት ለማበላሸት ጥረት ከሚያደርጉ ሰዎችም ለመጠበቅ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንደሚኖረው ገልፀዋል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ መፈተናቸው ቀድመው ዩኒቨርሲቲዎቹን በአካል እንዲያውቋቸው ያደርጋልም ብለዋል።

ለፈተናው ተማሪዎች ተገቢውን ዝግጅት እንዲያደርጉና ወላጆችም አስፈላጊውን ድጋፍ ለልጆቻቸው እንዲያደርጉ ዋና ዳይሬክተሩ ጠይቀዋል።

የ2014ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሁለት ዙር በዩኒቨርሲቲዎች ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ እንዳለ ይታወቃል፡፡
761 views05:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-12 21:38:33 ከመስከረም 2015 ዓ.ም. መጨረሻ አንስቶ በሁለት ዙር የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የሚወስዱ አንድ ሚሊዮን ገደማ ተፈታኝ ተማሪዎች፣ ወደ ዩኒቨርሲቲዎች የሚጓጓዙበትን የትራንስፖርትና ሌሎች ወጪዎች በመንግሥት እንደሚሸፈኑ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታወቀ፡፡

ዩኒቨርሲቲዎች ለተፈታኝ ተማሪዎች የሚያስፈልጉ የምገባና መኝታ አገልግሎቶችን ለመስጠት ቁሳቁሶችን እያሟሉ መሆኑን አስታውቆ፣ ፈተናውን በዩኒቨርሲቲዎች ለማከናወን የሚያስችለውን ወጪ ለመሸፈን ተጨማሪ በጀት እንዲፈቀድለት ንግግር ላይ መሆኑን ገልጿል፡፡

የ12ኛ ክፍል ፈተናን በተመለከተ ከዚህ ቀደም ከነበረው ልምድ የተለየ አሠራር ለመዘርጋት ያቀደው ትምህርት ሚኒስቴር፣ ፈተናው በትምህርት ቤቶች ሳይሆን በዩኒቨርስቲዎች እንደሚሰጥ አስታውቋል፡፡ ለዚህም ሲባል ተፈታኝ ተማሪዎችን በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ መመደቡን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ምክትል ኃላፊ አቶ ይልቃል ወንድሜነህ ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

ምደባው ሲዘጋጅ በተቻለ መጠን ተማሪዎች በአቅራቢያቸው በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እንዲመደቡ መደረጉን ያስረዱት አቶ ይልቃል፣ ‹‹በአቅራቢያቸው ያለው ዩኒቨርሲቲ በመኝታ ወይም በመፈተኛ ክፍሎች ብዛት ውስንነት ካለበት ወደ ሌላ ዞንና ክልል የመሄድ ዕድል ይኖራል፤›› ብለዋል፡፡

በተለይ ገጠር አካባቢዎች ላይ ያሉ ተማሪዎች ወደ ተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ ለመጓዝ አስቸጋሪ ሁኔታ ሊገጥማቸው እንደሚችል ጠቅሰው፣ አገልግሎቱ ከክልል ትምህርት ቢሮዎች ጋር በመሆን ተማሪዎቹን ወደ ዩኒቨርሲቲ እንደሚያጓጉዝ አስረድተዋል፡፡

‹ተማሪዎቹን እንዴት እናጓጉዛቸው?› የሚለው ላይ ውይይት እያደረግን ነው፡፡ ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲዎች በመፈተናቸው ምክንያት ግን ወደ ተማሪዎችም ሆነ ወደ ወላጆች የሚሄድ ወጪ አይኖርም፤›› ብለዋል፡፡

ምክትል ኃላፊው፣ ተማሪዎቹ የተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ አካባቢ እንዲላመዱት ለማድረግ ሲባል ፈተናው ከሚጀመርበት ቀናት ቀደም ብለው ወደ ዩኒቨርሲቲው እንደሚጓዙ አስታውቀዋል፡፡ ወደ ዩኒቨርስቲ ሲገቡ ድምፅም ሆነ ምሥል የሚቀዳና የሚቀርፅ አሊያም ሌላ የኤሌክትሮኒክስ መሣሪያ ይዘው መግባት እንደማይችሉ ተናግረዋል፡፡ የሚኖሩበት ከተማ ውስጥ በሚገኝ ዩኒቨርሲቲ የተመደቡ ተፈታኞችም ቢሆኑ በዩኒቨርስቲው ውስጥ እንዲያድሩ ለማድረግ መታቀዱንም ገልጸዋል፡፡

ከመስከረም 28 እስከ ጥቅምት 17 ቀን 2015 ዓ.ም. ባለው ጊዜ ውስጥ በሁለት ዙር በሚሰጠው የ12ተኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከ984,000 በላይ ተማሪዎች ለፈተና እንደሚቀመጡ ተገልጿል፡፡ መስከረም 30 ቀን በሚጀምረው የመጀመሪያው ዙር ፈተና ለፈተና የሚቀመጡት የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ሲሆኑ፣ ብዛታቸው 623 ሺሕ ገደማ ነው፡፡ ይህም ፈተናው የሚሰጥባቸው 42 ዩኒቨርሲቲዎች በመጀመሪያው ዙር በፈተና በአማካይ 14,827 ሺሕ ገደማ የ12ተኛ ክፍል ተማሪዎች በእያንዳንዱ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ይመደባሉ እንደማለት ነው፡፡

ይሁንና የዩኒቨርሲቲዎች ምደባ የተደረገላቸው ካላቸው ሀብትና አቅም አንፃር እየታየ መሆኑን የተናገሩት አቶ ይልቃል፣ ፈተናው በሁለት ዙር እንዲሰጥ የተወሰነው ዩኒቨርሲቲዎቹ ካላቸው አቅም አንፃር መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲዎቹ ለአንድ ዙር የተመደበላቸውን የተማሪ ብዛት ለማስተማገድ የሚጎድሏቸው ቁሳቁሶችን በመገምገም በግዥ እንዲያሟሉ እየተደረገ መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡

ምንጭ፡ሪፖርተር ጋዜጣ
922 views18:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ