Get Mystery Box with random crypto!

Ethio University

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiouniversty1 — Ethio University E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiouniversty1 — Ethio University
የሰርጥ አድራሻ: @ethiouniversty1
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 4.85K
የሰርጥ መግለጫ

ለማንኛውም አይነት የማስታወቂያ ስራ እና ክሮስ(Cross)
💰💰 @Cozboy0 💰💰
ያናግሩን🎫🎟🎪🎪🎪🎪

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 33

2022-08-30 13:26:27 ለወሎ ዩንቨርሲቲ ተማሪዎች ከግቢው ተማሪዎች ህብረት የተላለፈ መልዕክት

★በአሁኑ ሰዓት በግቢያችን ውስጥ ትምህርታችሁን እየተከታተላችሁ የምትገኙ ተማሪዎች በሙሉ

ሃገራዊ ችግሩን ምክንያት በማድረግ ውስጣችሁ እየተረበሸ እንደሆነ አስተውለናል፥ ዩኒቨርሲቲው በአሁኑ ሰዓት ስለጉዳዩ ውይይት እያደረገ በመሆኑ ከተለያዩ ውዝግቦች ራሳችሁን በማግለል ተረጋግታችሁ ትምህርታችሁን እንድትከታተሉና በዩንቨርሲቲው በኩል የሚወሰኑ ውሳኔዎችን እንድትጠብቁ እናሳውቃለን።


፨ማሳሰቢያ ትምህርታችሁን አጠናቃችሁ እየወጣችሁ ያላችሁ የአንደኛ አመት መደበኛ ተማሪዎች ካለአግባብ ወጪና እንግልት ተቆጥባችሁ በተረጋጋ መንፈስ ጉዞ ታደርጉ ዘንድ የግቢው ተማሪዎች ህብረት ያሳስባል።
381 views10:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 21:27:19 #Update

የወልድያ ዩኒቨርሲቲ ባደረባቸው በስጋት ምክንያት ግቢያቸውን ለቀው የወጡ ተማሪዎችን በሚመለከት ውሳኔ ወሳለፈ።

ዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች በ22/12/2014 ዓ.ም ባደረባቸው ስጋት ምክንያት የተነሳ ግቢውን ለቀው መውጣታቸውን ገልጿል።

በዚህ የሚከተሉትን ውሳኔዎች አስተላልፏል፡፡

1ኛ. የመደበኛ መርሀ ግብር ተማሪዎች በሙሉ ወደ ዩኒቨርሲቲው መመለሻ ጊዜ #በቀጣይ_ዓመት ጥሪ በሚደረግበት ጊዜ ይሆናል።

2ኛ. የክረምት መርሀ ግብር ተማሪዎች በሙሉ የተጀመረውን ትምህርትና ፈተና ለማጠናቀቅ ወደ ዩኒቨርሲቲው መመለሻ ጊዜ መስከረም 03/2015 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።
421 views18:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 00:10:01 Woldia University

በጦርነቱ ምክንያት የወልዲያ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ግቢውን ለቀው እየወጡ መሆኑን ከቤተቦቻችን የደረሰን መረጃ ያሳያል ።

"የወልደያ ዩንቨርሲቲ ተማሪዎች ውጡ ተብለው ግቢውን ለቀው በእግራቸው እየሄዱ ነው።
ሮቢት እና ገንደመዩ ላይ ውጊያው እንደቀጠለ ነው።"

ፈጣሪ ከናንተ ጋር ይሁን
491 views21:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 20:03:38 በአማራ ክልል የ2015 የትምህርት ዘመን የተማሪዎች ምዝገባ ከነሐሴ 23 - ጳጉሜ 04 ይካሄዳል።

የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የ2015 የትምህርት ዘመን የተማሪዎች ምዝገባን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል። በዚህም በ2015 የትምህርት ዘመን ከ6 ነጥብ 2 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎችን ለመመዝገብ ቢሮው ቅድመ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ገልጿል።

ከነሐሴ 23/2014 ዓ.ም እስከ ጷጉሜን 04/2014 ዓ.ም ድረስ ተማሪዎችን ለመመዝገብ መታቀዱን የጠቆሙት የቢሮው የሕዝብ ግንኙነት ኀላፊ ጌታቸው ቢያዝን፤ በዚኽም 895 ሺህ 404 የቅድመ መደበኛ ተማሪዎች እንደሚመዘገቡ ገልጸዋል።

እድሜያቸው 7 ዓመት የሞላቸው ተማሪዎች 714 ሺህ 518 ተማሪዎች እንደሚመዘገቡም አስረድተዋል። በአጠቃላይ 745 ሺህ 708 የአንደኛ ክፍል ተማሪዎች እንደሚመዘገቡ የሕዝብ ግንኙነት ኀላፊው አንስተዋል።

በአጠቃላይ 4 ሚሊዮን 144 ሺህ 845 ተማሪዎች በ1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እንዲኹም 1 ሚሊዮን 219 ሺህ 301 ተማሪዎች በ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በተያዘላቸው ጊዜ እንደሚመዘገቡ አቶ ጌታቸው ገልጸዋል።

ምዝገባው አዲስ ተማሪዎችን ብቻ ሳይኾን በተለያየ ጊዜ ትምህርታቸውን ያቋረጡ ተማሪዎችን የሚያካትት እንደኾነ አቶ ጌታቸው አስረድተዋል። በ2014 ዓ.ም 5 ነጥብ 3 ሚሊዮን ተማሪዎች ተመዝግበው ትምህርታቸውን ሲከታተሉ ቆይተዋልም ነው የተባለው። (አሚኮ)
256 views17:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 20:00:22 የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ለመስጠት የቅድመ ዝግጅት ስራው ሙሉ በሙሉ በመጠናቀቅ ላይ እንደሚገኝ ተገለፀ፡፡
------------------------------------------------------------------------

የ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ቅድመ ዝግጅት ስራ ሙሉ በሙሉ በመጠናቅ ላይ መሆኑን የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ከበደ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

የፈተና ዝግጅቱም የተማሪዎችን ልፋት ሊለካ በሚችል ከደህንነት ስጋት ነፃ እንዲሆን በቴክኖሎጂ በመታገዝ በከፍተኛ ጥንቃቄ እየተሰራ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

ለፈተና አሰጣጡ ውጤታማነት ከመፈተኛ ቦታ መረጣ ጀምሮ የፈተና ኮዶችን ብዛት ከፍ የማድረግ ስራ የተሰራ መሆኑም ተገልጿል።

ይህንንም ተከትሎ ተማሪዎች አስፈላጊውን ዝግጅት በማድረግ የራሳቸው ጥረት ውጤት ለማግኘት መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡

የተሳሳቱ መረጃዎችን በመልቀቅ ተማሪዎች የስነ ልቦና ጫና እንዲደርስባቸው የሚያደርጉ አካላትም ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ዋና ዳይሬክተሩ ያሳሰቡ ሲሆን ለዚህም የህግ ተጠያቂነት እንዲኖር እየተሰራ እንደሚገኝም ገልፀዋል፡፡

ተማሪዎችና ወላጆችም መረጃዎችን ከተቋሙ እና ከታማኝ የመረጃ ምንጮች ብቻ እንዲከታተሉም ጠይቀዋል።

ትምህርት ሚኒስቴር የ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን ከ መስከረም 30,2015ዓ.ም ጀምሮ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ለመስጠት ዝግጅት እያደረገ እንዳለ ይታወቃል፡፡
408 views17:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 23:16:27 #Update

የ2014 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ከመስከረም 30 እስከ ጥቅምት 11 ቀን 2015 ድረስ በሁለት ዙር እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

ለዚህም ተማሪዎች እራሳቸውን እንዲያዘጋጁ ጥሪ አቅርቧል።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ረዲ ሽፋ #ለኦቢኤን በሰጡት ቃል ፤ በአጠቃላይ በሁለት ዙር በሚሰጠው ፈተና ከ984,000 በላይ ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚወስዱ ገልፀዋል።

ፈተናውን ከሚወስዱት ውስጥ የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ቁጥር 622,739 መሆኑን አመልክተዋል።

የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ብዛት ያላቸው በመሆኑ በመጀመሪያው ዙር ከመስከረም 30 እስከ ጥቅምት 3 /2015 አስቀድሞ ፈተናው እንደሚሰጣቸው አቶ ረዲ ተናግረዋል።

የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ቁጥር ደግሞ 361,279 ሲሆን በሁለተኛው ዙር ከጥቅምት 8 እስከ 11/2015 ፈተናውን እንደሚወስዱ አስረድተዋል።

ከዚህ ቀደም የነበሩ የፈተና ችግሮችን ለመፍታት ፈተናው በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እንደሚሰጥ አረጋግጠዋል ፤ ፈታኞቹ ደግሞ የዩኒቨርሲቲ መምህራን መሆናቸውን አሳውቀዋል።

በተጨማሪም ፤ ፈተናው ከዚህ ቀደም ከነበረው ከ4 ኮድ ከፍ ማለቱን ገልፀዋል።

ፈተናው ተዘጋጅቶ እየታተመ ሲሆን ፈተናው እስከሚሰጥበት ቀን ድረስ ተፈታኞች እራሳቸውን ማዘጋጀት እንዳለባቸውም አሳስበዋል።
468 views20:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-20 09:35:00 #ExitExam

የትምህርት ጥራት #ፈተና_በመስጠት ብቻ ይረጋገጣል ?

ከ2015 ዓ/ም ጀምሮ የመውጫ ፈተና መሰጠት እንደሚጀመር ይታወቃል።

ለመሆኑ ፈተና በመፈተን ብቻ የትምህርት ጥራት ማምጣት ይቻላል ? ትምህርት ሚኒስቴር በዚህ ጉዳይ ምላሽ አለው።

ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) ለብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ (ኢቲቪ) የተናገሩት ፦

" የትምህርት ጥራት ፈተና ብቻ በመስጠት የሚሳካ ፤ የሚረጋገጥ ነገር አይደለም።

በአጠቃላይ ግን በትምህርት እና ስልጠና ዘርፉ በተለይም በትምህርቱ ዋና ችግር አለ ተብሎ የተለየው ዋና የትምህርት ሴክተሩ ስብራት ነው ተብሎ የተለየው ትምህርታችን ጥራትም ተገቢነትም ጎሎታል።

ስለዚህ አስመርቀን የምናስወጣው በሙሉ ባይባልም የጥራት ፣ የብቃት ችግር አለበት ይሄንን መፍታት ያስፈልጋል።

ለዚህ የሚሆን በሁሉም ደረጃ ከግብዓትም ጋር ከሂደቱም ጋር የሚያያዝ እንደዚሁም ውጤቱን ከማረጋገጥ ጋር የሚያያዝ ስራዎች መሰራት አለባቸው ተብሎ በመንግስት ቁልፍ የሪፎርሞች ተጀምረዋል አንደኛው ከመውጫ ፈተና ጋር የሚያያዝ ነው።

ይሄ የመውጫ ፈተና በዋናነት የሚመለከተው የመጀመሪያ ዲግሪ ምሩቃንን ነው ሁለተኛ ዲግሪ እና ሌሎችን አይመለከትም የሚጀምረው በ2015 ሰፋ ብሎ ነው እንጂ ከዚህ በፊትም የተጀማመሩ ስራዎች አሉ የተጀመሩ ፕሮግራሞች አሉ።

ዋናው ቁም ነገሩ በግብአት ደረጃ ጥራቱን ማረጋገጥ ያስፈልጋል የምሩቁን ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገባውን የመማር ማስተማር ሂደቱ ጥራትን በሚያረጋግጥ መልኩ መምራት እና መስጠት ያስፈልጋል።

           
201 views06:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-19 18:29:27 በአዲስ አበባ ትምህርት መስከረም 9 ይጀምራል

በ2015 የትምህርት ዘመን 8ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ሆኖ ይሰጣል ተባለ

የ6ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ የሚኒስትሪ ፈተና እና የ8ኛ ክፍል ፈተና ሀገር አቀፍ ሆኖ ይሰጣል።

የ2015 ዓመት መደበኛ የትምህርት ዘመን መስከረም 9 ቀን እንደሚጀመር የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ አስታውቋል።

በ2015 የትምህርት ዘመን አዲሱ ስርዓተ ትምህርት ወደ ሙሉ ትግበራ እንደሚገባ የቢሮው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አበበ ቸርነት ተናግረዋል።
በአንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ተቋማት ላይ በተመረጡ ትምህርት ቤቶች የሙከራ ትግበራ በ2014 የትምህርት ዘመን ላይ የተከናወነ ሲሆን አዲሱ ስረዓተ ትምህርት በ2015 የትምህርት ዘመን ሙሉ በሙሉ በሁሉም የመንግስትም ሆነ የግል ትምህርት ቤቶች ተግበራዊ ይሆናል።

በሌላ በኩል በቅድመ አንደኛ ደረጃ እና በአጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ እንዲሁም በከፊል በተወሰኑ ትምህርት ቤቶች ላይ በ2015 የትምህርት ዘመን የሙከራ ትግበራ ከተከናወነ በኃላ በ2016 ዓ.ም ወደ ሙሉ ትግበራ እንዲገባ ይደረገል።

በ2015 ዓመት የትምህርት ዘመን 6ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፣የ8ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ እንዲሁም 12ኛ ክፍል የሁለተኛ ደረጃ የማጠቃለያ ፈተና ይሰጣል ፡፡በ2015 የትምህርት ዘመን ላይ ወደ ሙሉ ትግበራ የሚገባው አዲሱ ስርዓተ ትምህርት የጥራት ደረጃውን ጠብቆ እንዲተገበር በተለይ የግል እና መንግስታዊ ያልሆኑ ትምህርት ተቋማት ትኩረት ሰጥተው እንዲሰሩ ለማድረግ እና ከዚህ ቀደም በስርዓተ ትምህርት ትግበራ ላይ የነበሩ ጉድለቶችን ለማረም በጋራ መሰራት እንደሚያስፈልግ ተገልጿል።

የመጽሀፍ ስርጭትን በተመለከተ ትምህርት ከመጀመሩ በፊት በተማሪዎች እጅ እንዲደርስ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን አቶ አበበ ቸርነት ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
277 views15:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 23:56:02 ኤሌክትሪካል እና ኮንፒተር ምንድስና ምንድነው ?

ኤሌክትሪካል ምንድስና ሰለ ትንሿ ቅጣት ወይም ኤልክትሮን እንቅስቃሴ የሚያጠና ዲፓርትመንት ሲሆን ማንኛውም መብራትን የሚጠቀሙ ማሽኖች ይሁን ኤሌክትሮኒክሶዎችን የሚያጠና ወይም ዲዛይን የሚያደረግ ዲፓርትመንት ነው።

መብራት ማለት ምንድነው ?

መብራት ማለት ኤሌክትሮኖች ከቦታ ቦታ ሲንቀሳቀሱ የሚፈጠረ ክስተት ሲሆን በአንድ ገመድ ውስጥ መብራት አለ ማለት ኤሌክትሮን በዛ ገመድ ውስጥ እየተንቀሳቀሱ ነው እንደማለት ነው።

ኤሌክትሮን እራሷ ምንድናት ?

ኤልክትሮን ማለት ዩንቨረስ የተፈጠረበት ትንሿ ቅንጣት ናት ይሄ ማለት የሰው ልጆችን ጨምሮ ሁሉም ነገሮች የተፈጠሩት ኤልክትሮን እና ፕሮቶን ከተባሉ ሁለት ቅንጣቶች ነው ወይም የሆንን ነገረ ዝንብላቹ እየከፈላቹት ብትሄዱ መጨረሻ ላይ የምታገኙት እና መከፈል የማይችለው ነገረ ነው ይሄም በሰው ልጅ የማይታይ ነገረ ሲሆን መኖሯም የታወቀው በምትፈጥረው ተፅኖ ነው።

ኤሌክትሮን ብዙ ነገሯ ሚስጥር ቢሆንም ኤሌክትሪካል ምንድስና ሰለዚች ትንሽ ነገር የሚያጠና የትምህርት ክፍል ነው።

ምንም እንኳን የኤልክትሪክ ምንድስናን ብዙ ሰዎች ከመብራት ጋር ብቻ ቢያገናኙትም በዚህ ስር የሰለጠነ አንድ ተማሪ ትላልቅ ማሽኖችን መቆጣጠር በቴሌዎች በቲቪ እና የራዲዮ ኤጀንሲዎች እንዲውም አየረ መንገድ ውስጥ ሲግናል የመቆጣጠር ስራ ይሰራሉ በተጨማሪ የኤሌክትሮኒክስ ፣ እንደ ፕሌን እና ባቡር ላሉ ትላልቅ መጓጓዣዎች የጥገና ስራን መስራት ይችላሉ።

ኢትዮጵያ ውስጥ ተምራቹት ከሆነ ደግሞ ውሃ በላቹ ምንም አታቁም

ለተጨማሪ መረጃ የዩቲውብ ቻናላችንን ይጎብኙ

https://youtube.com/channel/UCgmzpzIOElQB2v1JZtkjKQg?sub_confirmation=13
333 views20:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 19:26:54 #WolloUniversity

ለኮምቦልቻ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት መደበኛ ተመራቂ ተማሪዎች በሙሉ

የወሎ ዩንቨርሲቲ ቴክኖ ግቢ ተመራቂ ተማሪዎች እስከ መስከረም 15/2015 ድረስ የመመረቂያ ጽሁፋቸውን በማጠናቀቅ ግቢውን ለቀው እንዲወጡ እና የመመረቂያ ቀናቸው ጥቅምት 26 እና 27/2015 እንዲሆን መወሰኑን ከግቢው ተማሪዎች ህብረት የቴሌግራም ቻናል ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
335 views16:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ