Get Mystery Box with random crypto!

Ethio University

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiouniversty1 — Ethio University E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiouniversty1 — Ethio University
የሰርጥ አድራሻ: @ethiouniversty1
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 4.85K
የሰርጥ መግለጫ

ለማንኛውም አይነት የማስታወቂያ ስራ እና ክሮስ(Cross)
💰💰 @Cozboy0 💰💰
ያናግሩን🎫🎟🎪🎪🎪🎪

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 35

2022-07-26 19:39:56
የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርስቲ በክረምት ፕሮግራም በህግ ት/ት ቤት የሰብአዊ መብቶች ህግ የት/ት ዘርፍ የግል አመልካቾችን ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል። ስለሆነም በዘርፉ መማር የምትፈልጉ የግል አመልካቾች እስከ ሐምሌ 22/2014 ዓ.ም ዋናው ግቢ ሬጅስትራር ህንፃ ቁጥር 29 ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

ዝርዝር መረጃውን ከፎቶው ያንብቡ
249 views16:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-25 18:57:52 የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2014 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ውጤትን ይፋ አድርጓል።

ፈተናውን ከወሰዱ ተማሪዎች 63.9 በመቶ የሚሆኑት 50 እና ከዚያ በላይ ውጤት ማስመዝገባቸውን የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ ገልጿል፡፡

ይህም ባለፉት ዓመታት በከተማዋ ከተመዘገቡ የ8ኛ ክፍል ውጤቶች አንጻር ከፍተኛ ውጤት መሆኑ ተመላክቷል፡፡

ቢሮው ከዛሬ ጀምሮ ተማሪዎች ውጤታቸውን በቀጣይ በሚያሳውቀው አድራሻ አማካይነት በኦላይን መመልከት ይችላሉ ብሏል፡፡

ውጤታችሁን ኦንላይን የምትመለከቱበትን አድራሻ ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ በቀጣይ ያደርሳችኋል።

በአዲስ አበባ ከ71 ሺህ በላይ ተማሪዎች የ8ኛ ክፍል ፈተናን መውሰዳቸው አይዘነጋም።
330 views15:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-23 20:32:38 የ2015 ዓ.ም ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተናን ዲጂታላይዝ ለማድረግ/በኦንላይን ለመስጠት እየተሠራ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ገልጸዋል።

የፈተና አሰጣጡን ሙሉ ለሙሉ አውቶሜት ለማድረግ ከቻይና መንግስት ጋር እየተሠራ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሰጡት ማብራሪያ ጠቁመዋል።

ለፈተናው የሚቀመጡ ተማሪዎች ቁጥር ከፍተኛ መሆኑን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በርካታ ታብሌት ኮምፒዩተሮች እንደሚያስፈልጉ ተናግረዋል።

ይሁን እንጂ በኮቪድ-19 ምክንያት አምራች ድርጅቱ ኮምፒዩተሮቹን በተያዘለት ጊዜ ማምረት አለመቻሉን ገልጸዋል።

ኮምፒዩተሮቹ በተያዘላቸው ጊዜ ከደረሱ በቂ ዝግጅት ስለተደረገ የቀጣይ ዓመት ፈተና ኦንላይን እንደሚሰጥ አረጋግጠዋል።

ታብሌቶቹ በሚጠበቀው ጊዜ ካልደረሱ፥ መንግስት የፈተና ስርቆት የሚቀነስበት የተሻለ አሰራር በመከተል ፈተናው ይሰጣል ብለዋል።
243 views17:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-23 13:59:27 የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2014 የትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ ፡፡

ለፈተና ከተቀመጡ ተማሪዎች መካከል 64.9 ፐርሰንት ተማሪዎች 50 እና በላይ ውጤት ማስመዝገብ ችለዋል፡፡ ይህም ካለፉት አመታት ከተመዘገቡት ከተማ አቀፍ የ8ኛ ክፍል ውጤቶች አንጻር ሲታይ ከፍተኛ ውጤት ሆናል፡፡

ለውጤቱ መመዝገብም የሁሉም ባለድርሻ አካላት ሚና የላቀ በመሆኑ ቢሮው ይህ ውጤት እንዲመዘገብ ኃላፊነታቸውን ለተወጡ አካላት በሙሉ ምስጋናውን እያቀረበ ከሰኞ ማለትም ከ18/11/2014 ዓ.ም ጀምሮ ተማሪዎች ውጤታችሁን በቀጣይ በምናሳውቃችሁ አድራሻ አማካኝነት ኦላይን መመልከት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
86 views10:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-21 22:46:45 #የትምህርትና_ስልጠና_ባለሥልጣን

የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በሀገር አቀፍ ደረጃ በ2014 ዓ.ም ብቻ እርምጃ የወሰደባቸው የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ካምፓሶችና ቅርንጫፎች ብዛት #357 ደርሷል።

ባለሥልጣኑ በ5ኛ ዙር የስነ ስርዓት ጥሰት ፈጽመው በመገኘታቸው የማስተካከያ እርምጃ የወሰደባቸውን 25 ካምፓሶችና ቅርንጫፎችን ይፋ አድርጓል።

ባለስልጣኑ በ2014 ዓ.ም ብቻ በአዲስ አበባ ከተማ እና በክልል ከተሞች በሚገኙ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ ባደረገው ድንገተኛ ፍተሻ የመመሪያ ጥሰት ፈጽመው የተገኙ ካምፓሶች እና ቅርንጫፎቻቸውን በአምስት ዙር አሳውቋል።

በ1ኛ ዙር በአዲስ አበባ (106) እንዲሁም በክልል ከተሞች በ2ኛ ዙር (95)፣ በ3ኛ ዙር (104)፣ በ4ኛ ዙር (27) እና በ5ኛ ዙር (25) በድምሩ #357 የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ የማስተካከያ እርምጃ መወሰዱን ባለስልጣኑ ገልጿል።

ተቋማቱ የእርምት እርምጃ የተወሰደባቸው የእውቅና ፈቃድ ባልተሰጠባቸው ካምፓሶች፣ ቅርንጫፎች እና የትምህርት መስኮች ተማሪ ተቀብለው ሲያስተምሩ፣ የእውቅና ፈቃድ እድሳት ባልተሰጠባቸው የትምህርት መስኮች መዝገበው ሲያስተምሩ በመገኘታቸው መሆኑ ተመላክቷል፡፡
44 views19:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-20 22:33:44 #DebreTaborUniversity

ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ የነባር እና አዲስ ገቢ የ2014 ዓ.ም #የክረምት መርሃ ግብር ተማሪዎች ምዝገባ ከሐምሌ 20 እስከ 22/2014 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል።

ጥሪው ለመጀመሪያ ዲግሪ፣ ለሁለተኛ ዲግሪ እና ለPHDT የክረምት ተማሪዎች የተደረገ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

 Share share
195 views19:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-20 22:23:55 በሰሜኑ ጦርነት ሳቢያ በትግራይ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች በመዘጋታቸው የተፈናቀሉ ወደ 4,000 የሚደርሱ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን በሌሎች ክልሎች በሚገኙ ዩንቨርስቲዎች መመደባቸው ዋዜማ ያሰባሰበችው መረጃ ያመለክታል፡፡

በትግራይ ክልል ከሚገኙ የመንግስት ዩኒቨርሰቲዎች በተለይም መቀሌ፣ አዲግራት፣አክሱም እና ራያ ዩንቨርስቲዎች ዋና ካምፓሶችና ኮሌጆች ውስጥ ሲሰሩ የነበሩት መመህራን ጦርነትቱን ተከትሎ በተደረገ ጊዜዊ ድልዳላ በሌሎች የአገሪቱ ክፍሎች በሚገኙ ዩንቨርስዎች በጊዜዊነት ዝውውር መመዳባቸውን ለዋዜማ የገለጹት የኢትዮጵያ መመህራን ማህበር ፕሬዚዳንት ዮሐንስ በንቲ (ዶ/ር) ናቸው፡፡

በተመሳሳይ ከዚሁ ክልል በመቀሌና አላማጣ ከተማ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ሲሰሩ የነበሩ መምምራን ሸሽተውና ተፈናቅለው ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ቅጥር እንዲፈጸምላቸው ጥያቄ ያቀረቡ 25 መምህራን እንዳሉ ዮሐንስ ተናግረዋል፡፡

ይሁን እንጅ የሁለተኛ ደራጃ ትምህርት ቤቶችን ጉዳይ የሚመለከተው የየክልሎቹ ትምህርት ቢሮ በመሆኑ በትምህርት ሚንስቴር በኩል መልስ ባለማገኘታቸው መምራኑ ከመምህራን ማህበሩ ጋር መነጋገራቸውን አክለው ገልጸዋል፡፡

ጦርነቱ ከተጀምረ ጊዜ ጀምሮ ተፈናቅለው አዲስ አበባ የገቡት የሁለተኛ ደረጃ መምሀራን ከትግራይ ክልል ጋር ያለው ችግር እስኪፈታ ቦታ እንዲፈለግላቸው ለኢትዮጵያ መምራን ማህበሩ ያቀረቡትን ጥያቄ መሰረት በማድረግ ማህበሩ ‹‹ አቅም በፈቀድ መጠን ትብብር እንዲደረግላቸው›› መረጃ እየሰነዱ እንደሆነ ፕሬዚዳንቱ ገልፀዋል፡፡

ጉዳዩ ምንም እንኳ አስቸጋሪ ቢሆንም፣ አሁን ያለው ሁኔታ እስኪረጋጋ ድረስ ሪፖርት ያቀረቡትን መምህራን ቢያንስ እንኳ በጊዜዊት ክልሎች ላይ ተመድበው የሚሰሩበት መፍትሄ እንዲያገኙ ማህበሩ ለጠቅላይ ሚንስቴሩ፣ ለትምህርት ሚንስቴር፣ለገንዘብ ሚንስቴርና ለክልሎች እንደ አማራጭ ጥያቄ እያቀረቡ መሆኑን ዮሃንስ ተናግረዋል፡፡

ዩኒቨርስቲዎችን በበላይ ሲመራ የነበረው የቀድሞው የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በመስከረም 2014 ዓ.ም አዲስ በተቋቋመው አደረጃጀት መሰረት ወደ ትምህርት ሚኒስቴር የተጠቃለለ ሲሆን የመምህራኖቹ ጉዳይ ለዚሁ ለሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ መዘዋወሩ የሚታወስ ነው።

[ዋዜማ ራዲዮ]
206 views19:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-19 20:38:24 #WolaitaSodoUniversity

ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የ2014 ዓ.ም #የክረምት መርሃ ግብር ተማሪዎች ምዝገባ ሐምሌ 20 እና 21/2014 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል።

የነባር የክረምት ተማሪዎች ቲቶሪያል ከሐምሌ 22 እስከ 25/2014 ዓ.ም እንደሚሰጥ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

ጥሪው የቅድመ እና ድኅረ ምረቃ የክረምት መርሃ ግብር ተማሪዎችን ይመለከታል የተባለ ሲሆን በግብርና፣ በእንስሳት ጤና እና በኅብረት ሥራ ትምህርት ፕሮግራሞች የክረምት ተማሪዎችን አይመለከትም ተብሏል።
117 views17:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-19 18:45:52 #MoH

የጤና ሚኒስቴር በነሐሴ 2014 ዓ.ም ለሚሰጠው የጤና ባለሙያዎች የብቃት ምዘና ፈተና ምዝገባ ጀምሯል።

ምዝገባው ከሐምሌ 06 እስከ 17/2014 ዓ.ም እንደሚከናወን ሚኒስቴሩ አሳውቋል።

በመሆኑም አዲስና ነባር የመንግስት እና የግል ተቋማት ተመዛኞች በኦንላይን hple.moh.gov.et ላይ በመግባት እስከ ሐምሌ 17/2014 ዓ.ም ብቻ መመዝገብ ይችላሉ ተብሏል።

የግል ትምህርት ተቋማት ተመዛኞች ከምዝገባ በፊት የትምህርት ማስረጃዎቻቸውን በትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ማረጋገጥና ስማችሁን ወደ ጤና ሚኒስቴር ማስላክ ይጠበቅባቸዋል፡፡

ማንኛውም ተመዛኝ ወደ ፈተና ጣቢያ ሲሄድ ከምዝገባ በኋላ ሲስተሙ የሚሰጠውን የፈተና መለያ ቁጥር/Registration No የሚያሳይ ስሊፕ መያዝ ይጠበቅበታል።
167 views15:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-16 10:32:23 እንኳን ደስ አላችሁ!!!

የአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን 5 ሺሕ 58 ተማሪዎች እያስመረቀ ይገኛል፡፡

ዩኒቨርሲቲው መደበኛ ፣በርቀት በማታ እና በክረምት ያስተማራቸውን ተማሪዎች ነው እያስመረቀ ያለው፡፡ከአጠቃላይ ተመራቂ ተማሪዎች ውስጥ 1 ሺሕ 654 ሴቶች ሲሆኑ 3 ሺሕ 404 ደግሞ ወንድ መሆናቸው ታውቋል።ዩኒቨርሲቲው በዛሬው እለት ያስመረቀው ለ73ኛ ጊዜ መሆኑ ተገልጿል።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት ጣሰው ወልደሀና (ፕ/ር) ለተመራቂ ተማሪዎች እና ቤተሰቦች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ተመራቂዎች በተመረቁበት የሙያ መስክ ሀገራቸውን በቅንነት እና በታማኝነት እንዲያገለግሉም ጥሪ አቅርበዋል።በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የኢፌዴሪ ፕሬዝደንት ሳህለወርቅ ዘውዴን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች እና የተመራቂ ቤተሰቦች ተገኝተዋል፡፡
33 views07:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ