Get Mystery Box with random crypto!

#MoH የጤና ሚኒስቴር በነሐሴ 2014 ዓ.ም ለሚሰጠው የጤና ባለሙያዎች የብቃት ምዘና ፈተና ምዝ | Ethio University

#MoH

የጤና ሚኒስቴር በነሐሴ 2014 ዓ.ም ለሚሰጠው የጤና ባለሙያዎች የብቃት ምዘና ፈተና ምዝገባ ጀምሯል።

ምዝገባው ከሐምሌ 06 እስከ 17/2014 ዓ.ም እንደሚከናወን ሚኒስቴሩ አሳውቋል።

በመሆኑም አዲስና ነባር የመንግስት እና የግል ተቋማት ተመዛኞች በኦንላይን hple.moh.gov.et ላይ በመግባት እስከ ሐምሌ 17/2014 ዓ.ም ብቻ መመዝገብ ይችላሉ ተብሏል።

የግል ትምህርት ተቋማት ተመዛኞች ከምዝገባ በፊት የትምህርት ማስረጃዎቻቸውን በትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ማረጋገጥና ስማችሁን ወደ ጤና ሚኒስቴር ማስላክ ይጠበቅባቸዋል፡፡

ማንኛውም ተመዛኝ ወደ ፈተና ጣቢያ ሲሄድ ከምዝገባ በኋላ ሲስተሙ የሚሰጠውን የፈተና መለያ ቁጥር/Registration No የሚያሳይ ስሊፕ መያዝ ይጠበቅበታል።