Get Mystery Box with random crypto!

Ethio University

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiouniversty1 — Ethio University E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiouniversty1 — Ethio University
የሰርጥ አድራሻ: @ethiouniversty1
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 4.85K
የሰርጥ መግለጫ

ለማንኛውም አይነት የማስታወቂያ ስራ እና ክሮስ(Cross)
💰💰 @Cozboy0 💰💰
ያናግሩን🎫🎟🎪🎪🎪🎪

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 37

2022-06-11 11:40:15 ከትግራይ ክልል ዩኒቨርሲቲዎች ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የተመደቡ ተማሪዎች ትምህርታቸውን አጠናቀቁ

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በጦርነት ምክንያት በትግራይ ክልል ካሉ ዩኒቨርሲቲዎች የተመደቡ ተማሪዎች የሚቀራቸውን የትምህርት ኮርስ እንዲያጠናቅቁ አደረገ።


መንግሥት በጦርነቱ ምክንያት በየዩኒቨርሲቲዎች የነበሩ ተማሪዎች ከትግራይ ክልል በማስወጣት በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ሲመድብ ለባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ የደረሱትን ተማሪዎች በሰባት የትምህርት የአካዳሚክ ክፍሎች ውስጥ በማስገባት ቀሪ ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ በማድረግ ለመጀመሪያ ዲግሪ የሚያበቃቸውን ትምህርት እንዲያጠናቅቁ ነው ያደርገው።

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ፍሬው ተገኝ (ዶ/ር) ዛሬ ለመጀመሪያ ዲግሪ የሚያበቃችሁን የትምህርት ኮርስ እንድታጠናቅቁ እንደ ድል አድራጊ ወታደር በችግር ተፈትናችሁ ያለፋች በመሆናችሁ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።

ተማሪዎች ትምህርትና እውቀት ላይ ለተመሰረተ ለውጥ በእልህና በፅናት ለመስራት መዘጋጀት አለባችሁ ሲሉም ገልጸዋል። #ዋልታ

የኢትዮጵያ መንግስት ፊያዝን አስጠነቀቀ ለተጨማሪ መረጃ @vemoonli
1.0K views08:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-09 23:48:32 ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የኦንላይን (Online) ሙከራ ፈተና የሰጠው ት/ቤት

በሀገር ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የኦንላይን (Online) ሙከራ ፈተና መስጠቱን የአረካ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አስታዉቋል። ይህም ሀገራዊ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች በፈተና ጊዜ የቴክኖሎጂ ችግር እንዳይገጥማቸው ያግዛል ነው የተባለው።

ፈተናው በሙክራ እየተሰጠ የሚገኘው ትምህርት ቤቱ በራሱ መምህር አማካኝነት በበለጸገው ሥርዓት አማካኝነት ነው። ትምህርት ቤቱ የዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ በተገኙበት በይፋ በዛሬው ዕለት ሲስተሙን አስተዋዉቋል።

የወላይታ ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ታደሰ ኩማ ይህ ተግባር እጅግ ተስፋ የሚሰጥ ተግባር መሆኑን በመግለፅ የዚህን ትምህርት ቤት ተሞክሮ ወደ ሌሎች በዞን ወደሚገኙ ትምህርት ቤቶች በአጭር ጊዜ ለማስፋፋት እንደሚሰራ ጠቁመዋል።

ይህ የኦንላይን (Online) ፈተና ዝግጅት ከማዳበር ባሻገር ለተማሪዎች የቴክኖሎጂ ክህሎታቸውን እንዲያዳብሩና እንድያጎለብቱ መልካም እድል እንደሆነ የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር አቶ አለማየሁ ተናግረዋል።

ትምህርት ቤቱ በዚህ ዘርፍ ላይ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን የጠቀሱት አቶ አለማየሁ በረካታ በጀቶችን ወደዚህ መስክ በማሰማራት ዉጤታማ ለመሆን እየተሰራ እንደሚገኝ ጭምር ጠቁመዋል።
972 views20:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-04 14:18:30
#DebarkUniversity

በ2014 ዓ/ም ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ከሰኔ 8-9 ቀን 2014 ዓ/ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።
1.2K views11:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-01 23:26:28 #woldia university

የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች ጥሪ ከ ግንቦት30 አና ሰኔ 1 ነዉ

በምዝገባ ወቅት ፦
የ8ኛ ክፍል ሚንስትሪ ካርድ ዋናውና ፎቶኮፒ
ከ9-12 ክፍል ትራንስክሪብት ኦርጅናል እና ፎቶ ኮፒ
የ10ኛ እና የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ሰረተፍኬት ኦርጅናል ፎቶ ኮፒ
3×4 ጉርድ ፎቶ ግራፍ በዛት 4
አንሶላ፣ብርድልብስ፣ትራስጨረቅ እና የስፖርት ትጥቅ አሟልታቹ እድትገኙ
1.2K views20:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-30 18:36:10 #ማስታወሻ
#ScholarshipTip

የህንድ መንግስት በ2022/23 ለ55 ኢትዮጵያዊያን ነፃ የትምህርት ዕድል እንደሚሰጥ አሳውቋል።

በህንድ ባህላዊ ግንኙነት ም/ቤት (ICCR) የቀረበው ነፃ የትምህርት ዕድሉ፤ ከመጀመሪያ ዲግሪ እስከ ድህረ ዶክትሬት የትምህርት ፕሮግራሞች የተካተቱበት ነው።

በህንድ በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች/ተቋማት የሚሰጠው ዕድሉ፤ ከክፍያ ነፃ የትምህርት አገልግሎቶች እና ነፃ የአየር በረራ ትኬት ለአሸናፊዎች ያቀርባል።

አመልካቾች ዕድሚያቸው ከ18 እስከ 30 መሆን ያለበት ሲሆን እስከ አምስት ዩኒቨርሲቲዎች/ተቋማት ማልከት እንደሚችሉም ተገልጿል።

የማመልከቻ ጊዜው ነገ ግንቦት 23/2014 ዓ.ም ያበቃል።

ለማመልከት የሚከተለውን ሊንክ ይጠቀሙ፦

https://a2ascholarships.iccr.gov.in
1.3K views15:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-29 17:26:06 የቴክኒክና ሙያ ምዘናን ወደ ዓለም ዐቀፍ ደረጃ የሚያሸጋግር ስምምነት ተፈረመ።

በኢትዮጵያ፣ ኬንያ እና ታንዛኒያ መካከል ሲደረግ የነበረው የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ምዘናን ወደ ዓለም አቀፍ ደረጃ ያሳድጋል የተባለው ፕሮጀክት በሦሥቱ አገሮች ተፈርሞ ጸድቋል።

በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና የሚመረቁ ተማሪዎችና መምህራን በሦሥቱ አገሮች ተንቀሳቅሰው የመስራት ዕድል ይፈጠርላቸዋል ተብሏል፡፡

ስምምነቱ በዘርፉ ቀጠናዊ፣ አህጉራዊና ዓለም ዐቀፋዊ ተወዳዳሪነት ያላቸው ምሁራንን ለማፍራት ያስችላል መባሉን ሪፖርተር ዘግቧል፡፡

የሦሥቱ አገሮችን የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ለማሳደግ በዓለም ባንክ የሚደገፍ "የምስራቅ አፍሪካ አገሮች የክህሎት ሽግግር (EASTRIP)" የተባለ ፕሮጀክት ወደ ሥራ መገባቱ ይታወቃል፡፡

የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር በአዲስ አበባ ባዘጋጀው ዓውደ ጥናት ላይ እንደተገለጸው፤ ሦሥቱ አገሮች የተስማሙበት ወጥ የሆነ የጋራ የምዘና ሥርዓት ሲሠራ ቆይቶ የኬንያ እና ታንዛኒያ ሚኒስትሮች በተገኙበት ስምምነት ሆኖ ጸድቋል፡፡

በስምምነቱ መሠረት ኢትዮጵያ በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ቀጠናዊ የምዘና መስጫ ማዕከል እንደምትሆን የሥራ እና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ አሰግድ ጌታቸው ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ እስካሁን በቴክኒክና ሙያ እስከ ደረጃ ስምንት ሥልጠና ትሰጥ የነበረ ሲሆን ስምምነቱ እስከ 10 እና 11 ደረጃዎች ከሚሰጡ አገሮች ጋር መደረጉ በኢትዮጵያ የሚሰጠውን ደረጃ እንደሚያሳድገው ሪፖርተር ዘግቧል።
1.1K viewsedited  14:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-28 17:25:35
#WollegaUniversity

ወለጋ ዩኒቨርሲቲ የተቋሙ አርማ በአፋን ኦሮሞ የዩኒቨርሲቲውን ስያሜ ተጨማሪ አድርጎ አካቷል።

የተሻሻለው የዩኒቨርስቲው አርማ የተወሰኑ የቀለም ለውጥም ተደርጎበታል።

ዩኒቨርሲቲው የተሻሻለውን አርማ ከትላንት ግንቦት 19/2014 ዓ.ም ጀምሮ በይፋ መጠቀም ጀምሯል።

ውሳኔው ተቋሙ የሚገኝበት የአካባቢውን ቋንቋ በአርማው ላይ ለማካተት በማሰብ የተደረሰ እንደሚሆን ይገመታል።
977 views14:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-26 20:08:51 #DillaUniversity

ዲላ ዩኒቨርሲቲ በ2014 ዓ.ም ለተመደቡለት አዲስ ገቢ የመጀመሪያ ዲግሪ መደበኛ ተማሪዎች ጥሪ ለማድረግ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እያከናወነ መሆኑን አሳውቋል።

በሁለት ሳምንት ጊዜ ውስጥ ለተማሪዎቹ ጥሪ እንደሚደረግ የዩኒቨርሲቲው ሬጅስትራር ለ #ቲክቫህዩኒቨርሲቲ ገልጿል።

ዲላ ዩኒቨርሲቲ በ2014 የትምህርት ዘመን 5 ሺህ 780 አዲስ ገቢ ተማሪዎች በትምህርት ሚኒስቴር ተመድበውለታል።
1.1K views17:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-26 20:08:26 #ማስታወቂያ

የ2014 ዓ.ም የህግ ትምህርት መውጫ ፈተና (Exit Exam) ፈተናው የሚሰጥበት ቀናት ከሰኔ 21 - 24 ቀን 2014 ዓ.ም ባሉት ተከታታይ አራት የስራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 - 6፡00 ሰዓት ብቻ መሆኑን አውቃችሁ ተፈታኞች ከወዲሁ አስፈላጊውን ዝግጅት እንድታደርጉ እናሳስባለን ።
969 views17:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-25 19:06:30 #OdaBultumUniversity

ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ ''ምንም አይነት የጸጥታ ችግር በዩኒቨርሲቲው አለመኖሩን" አረጋግጧል።

በአንዳንድ የማኅበራዊ ሚዲያዎች ስለተቋሙ የሚሰራጩ መረጃዎች ፍጹም የተሳሳቱ እና ሀሰተኛ መሆናቸውን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ዩኒቨርሲቲው ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሥራውን እያከናወነ መሆኑን በፎቶ አስደግፎ ገልጿል።
908 views16:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ