Get Mystery Box with random crypto!

ከትግራይ ክልል ዩኒቨርሲቲዎች ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የተመደቡ ተማሪዎች ትምህርታቸውን አጠናቀቁ | Ethio University

ከትግራይ ክልል ዩኒቨርሲቲዎች ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የተመደቡ ተማሪዎች ትምህርታቸውን አጠናቀቁ

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በጦርነት ምክንያት በትግራይ ክልል ካሉ ዩኒቨርሲቲዎች የተመደቡ ተማሪዎች የሚቀራቸውን የትምህርት ኮርስ እንዲያጠናቅቁ አደረገ።


መንግሥት በጦርነቱ ምክንያት በየዩኒቨርሲቲዎች የነበሩ ተማሪዎች ከትግራይ ክልል በማስወጣት በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ሲመድብ ለባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ የደረሱትን ተማሪዎች በሰባት የትምህርት የአካዳሚክ ክፍሎች ውስጥ በማስገባት ቀሪ ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ በማድረግ ለመጀመሪያ ዲግሪ የሚያበቃቸውን ትምህርት እንዲያጠናቅቁ ነው ያደርገው።

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ፍሬው ተገኝ (ዶ/ር) ዛሬ ለመጀመሪያ ዲግሪ የሚያበቃችሁን የትምህርት ኮርስ እንድታጠናቅቁ እንደ ድል አድራጊ ወታደር በችግር ተፈትናችሁ ያለፋች በመሆናችሁ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።

ተማሪዎች ትምህርትና እውቀት ላይ ለተመሰረተ ለውጥ በእልህና በፅናት ለመስራት መዘጋጀት አለባችሁ ሲሉም ገልጸዋል። #ዋልታ

የኢትዮጵያ መንግስት ፊያዝን አስጠነቀቀ ለተጨማሪ መረጃ @vemoonli