Get Mystery Box with random crypto!

#MoE የትምህት ሚኒስቴር ፤ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከመጪው ዓመት ጀምሮ ከመንግስት ጣልቃ ገብነ | Ethio University

#MoE

የትምህት ሚኒስቴር ፤ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከመጪው ዓመት ጀምሮ ከመንግስት ጣልቃ ገብነት ነጻ ሆኖ ራሱን የሚያስተዳድር ዩኒቨርሲቲ እንደሚሆን አስታወቀ፡፡

በኢትዮጵያ የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ነጻ ሆኖ የመመራት መብት የሚሰጥበት የውይይት መድረክ በዛሬው ዕለት ተካሄዷል።

የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ÷ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሰቲን ተከትሎ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ከሁለት እስከ አምስት ዓመት ባለው ጊዜ ውስጥ በሂደት ወደ ነጻ ዩኒቨርሰቲነት እንደሚቀየሩ ተናግረዋል።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከመንግስት ጣልቃ ገብነት ውጪ በመሆን ነጻ ተቋም እንዲሆን የተወሰነውም መንግስት ዩኒቨርሲቲዎችን በራስ ገዝ አስተዳደር እንዲተዳደሩ የሚያስችል ውሳኔ ማሳለፉን ተከትሎ መሆኑን መግለፃቸውን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።