2023-03-30 22:44:13
ከተማሪዎች የቤት ሥራ እስከ ፕሬዝዳንቶች ንግግር የሚጽፈው ቻትጂፒቲ
***
ምን ዓይነት መረጃ ይፈልጋሉ? ምን ዓይነት መረጃ ለማግኘት ፈልገው ወደ ኢንተርኔት ደጃፍ ብቅስ ይላሉ?
ከዚህ ቀደም ለጥያቄዎ መልስ ፍለጋ በጉግል መረጃ ማሰሻ ላይ ጽፈው ሰዓታትን አባክነው ከሆነ አሁን ብዙ ነገር ተቀይሯል።
ለጥያቄዎ ፈጣን መረጃ በማቀበል ረገድ ቻትጂፒቲ (ChatGPT ) የትንፋሽዎ ያህል ቅርብ ነው።
ከዚህ በፊት በጉግል የመረጃ ማሰሻ ፈልገው ይማሩት የነበረውን በማሻሻል፣ ክህሎት የሚጠይቀውን ጉዳይ በአጭር ጥያቄ መዳፍዎ ላይ ያስገባል።
ሚሊዮኖች መልዕክቶቻቸውን ለማርቀቅ፣ የዘፈን ግጥሞችን፣ አልፎ ተርፎም የኮምፒውተር ኮዶችን ለመቀመር ይጠቀሙበታል።
ይህ የአርተፊሻል ኢንተለጀንስ (ሰው ሰራሽ አስተውሎት) ለሰፊው ተጠቃሚ ክፍት የሆነው ባለፈው ኅዳር ወር ላይ ነው።
ዝናው ግን የዕድሜውን ያህል አጭር አይደለም።
በኅዳር 2015 ዓ.ም. 2022 ወደ ሥራ የገባው ቻትጂፒቲ (ChatGPT ) በአንድ ሳምንት ውስጥ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ተጠቃሚዎችን አግኝቶ እንደነበር የድርጅቱ ባለቤት ኦፕን ኤአይ በወቅቱ ገልጿል።
ጉግል እና ማይክሮሶፍት ይህንን አርተፊሻል ኢንተለጀንስ አበልጽገው አገልግሎት ላይ ለማዋል እየተጣደፉ ነው።
ማይክሮሶፍት ብቻ በቢሊዮኖች ዶላር መድቦ የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ ነው። ይህ የወቅቱ የዓለማችን አነጋጋሪ እና አወዛጋቢ ስለሆነው አዲስ ቴክኖሎጂ በቴሌግራም ማናገር ለምትፈልጉ የፈለጋቹትን ነገረ ጠይቁት እንዲውም የአሳይመንት ጥያቄዎችን ጠይቁት መልሰ አለው
@GPT4Telegrambot
share share
@EthioUniversty1 @EthioUniversty1
687 viewsedited 19:44