2023-03-09 23:55:59
የሬሚዳል ፕሮግራምን ለመከታተል የመመዝገቢያ ነጥብ በመንግስት እና በግል ዩኒቨርሲቲዎች ይለያያል?
ትምህርት ሚኒስቴር ከ50 በመቶ በታች ያመጡ የ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች የሬሚዳል ፕሮግራምን በተለያዩ አማራጮች እንዲከታተሉ የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ማድረጉ አይዘነጋም።
የመቁረጫ ነጥቡ በሁሉም አማራጮች (በግል እና በመንግስት ተቋማት) የ Remedial ፕሮግራም ለመከታተል ተማሪዎች እንደተፈተኑት የትምህርት አይነት ብዛት 30% ከመቶ እና ከዚያ በላይ ማለትም (210 ከ 700፣ 180 ከ 600 እና 150 ከ 500) መሆኑን ማሳወቁም የሚታወስ ነው።
በዚህ የሬሚዳል መቁረጫ ነጥብ መሰረት ባደረግነው ምልከታ ከተቀመጠው ነጥብ #በታች ያመጡ ተማሪዎችን የሚመዘግቡ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መሆራቸውን አይተናል።
ምዝገባውን እያከናወነ ላለው ዩኒቨርሲቲ እና ኮሎጁ ትምህርት ሚኒስቴር ካስቀመጠው ነጥብ በታች ያመጡ ተማሪዎችን ለምን መዘገባችሁ? በሚል ላቀረብንላቸው ጥያቄ መንግሥት ይፋ ያደረገው ለመንግሥት ዩኒቨርስቲዎች እንጂ ለግል ተቋማት አይደለም ሲሉ ምላሽ ሰጥተውናል።
አል ዓይን ይህን ጥያቄ ይዞ ትምህርት ሚኒስቴርን የጠየቀ ሲሆን የሚኒስቴሩ የህዝብ ግንኙነት እና ኮሙንኬሽን ሀላፊ ወይዘሮ አመለወርቅ እዝቅኤል፥ "ለሬሚዳል ፕሮግራምም ይሁን ከ50 በመቶ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች መመዝገቢያ ነጥብ ለመንግሥትም ይሁን ለግል ዩኒቨርሲቲ ተመሳሳይ ነው" ሲሉ ተናግረዋል ።
ከዚህ በፊት የነበረው ለግል እና ለመንግሥት ዩኒቨርስቲዎች የተማሪዎች መመዝገቢያ ነጥብ ይለያይ ነበር ያሉት ሀላፊዋ፥ ከ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና በኋላ ተመሳሳይ እንዲሆን መወሰኑን አክለዋል።
በዚህም መሰረት ትምህርት ሚኒስቴር ካስቀመጠው የሬሚዳል ፕሮግራም መመዝገቢያ ነጥብ ውጪ የሚመዘግቡ ዩኒቨርስቲዎች እና ኮሌጆች ህግ እየጣሱ መሆኑንና እርምጃም እንደሚወሰድባቸው ነው ያብራሩት።
ምንጭ፡አልዓይን
ለተጨማሪ መረጃ
@EthioUniversty1 @EthioUniversty1
120 viewsedited 20:55