Get Mystery Box with random crypto!

Ethio University

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiouniversty1 — Ethio University E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiouniversty1 — Ethio University
የሰርጥ አድራሻ: @ethiouniversty1
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 4.85K
የሰርጥ መግለጫ

ለማንኛውም አይነት የማስታወቂያ ስራ እና ክሮስ(Cross)
💰💰 @Cozboy0 💰💰
ያናግሩን🎫🎟🎪🎪🎪🎪

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 9

2023-03-08 08:42:18
#ማስታወቂያ

የአቅም ማሻሻያ (REMEDIAL) ትምህርት ለመማር ወደ ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ ተማሪዎች የማደሪያ ክፍል ድልደላ በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች የመኝታ ክፍል ድልደላ ቦት {WKU Dormitory Placement(@WKUDormitoryBot)} ማግኘት የምትችሉ ሲሆን የብሄራዊ ፈተና የመለያ ቁጥር (Admission Number) በማስገባት የተመደባችሁበትን ዶርም ቁጥር እና ህንፃ ቁጥር ማወቅ የምትችሉ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ማስታወሻ፦
➭ የብሄራዊ ፈተና የመለያ ቁጥራችሁ (Admission Number) ከዜሮ(0) የሚጀምር ካለ ዜሮን በማስወገድ በመቁጠሪያ ቁጥር ብቻ ጀምራችሁ እንድትጠቀሙ እንጠይቃለን።
ለምሳሌ 067801 => 67801


የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት

ለተጨማሪ መረጃ

@EthioUniversty1 @EthioUniversty1
539 viewsedited  05:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-07 17:41:09
የምዝገባ ጥሪ ማስታወቂያ ለሬሚድያል ፕሮግራም ጂንካ ዩኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ ተማሪዎች በሙሉ:

በ2015ዓ/ም ለሬሚዲያል ፕሮግራም ጂንካ ዩኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ ተማሪዎች ምዝገባ የሚካሄደው ከመጋቢት 2-3/2015 ዓ/ም ስለሆነ በአካል ቀርባችሁ ሪፖርት እንድታደርጉ በጥብቅ እናሳስባለን።

ከተጠቀሰው ቀን ቀድሞም ይሁን ዘግይቶ የሚመጣን ተማሪ የማናስተናግድ መሆኑን እየገለፅን ማንኛዉም ተማሪ ሲመጣ የትራስ ጨርቅ እና አንሶላ ይዞ መምጣት እንዳለበት እናሳስባለን።

የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራር ዳይሬክቶሬት

ለበለጠ መረጃ ከዛሬ ጀምሮ ምሽት ሁለት ሰዐት ዜና በኋላ በኢቲቪ ዜና ቻናል ለተከታታይ ቀናት የሚተላለፈውን የጥሪ ማስታወቂያ እንድትከታተሉ እናሳውቃለን!!

ለተጨማሪ መረጃ

@EthioUniversty1 @EthioUniversty1
654 viewsedited  14:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-06 22:38:56 #MoE

" የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በቅድሚያ የመዘገቧቸውን ተማሪዎች ለትምህርት እና ስልጠና ባለስልጣን ማሳወቅ ይኖርባቸዋል " - ትምህርት ሚኒስቴር

የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የ12ኛ ክፍል የአቅም ማሻሻያ ትምህርት መስጠት እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር መግለፁን አሀዱ ዘግቧል።

በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መግቢያ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል ከ95 በመቶ በላይ የሚሆኑት ተማሪዎች ከ50 በመቶ በታች ውጤት ማምጣታቸው ይታወቃል፡፡

ከሀምሳ በመቶ በታች ካመጡት ተማሪዎች መካከል በልዩ ሁኔታ ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ገብተው ለአንድ አመት የአቅም ማሻሻያ ትምህርት ሪሜዲያል እንዲወስዱ የተወሰነ ሲሆን ከመንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በተጨማሪ በግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትም የአቅም ማሻሻያ ትምህርት መውሰድ እንደሚችሉ የትምህርት ሚንስቴር የህዝብ ግንኙት ሃላፊ ወ/ሮ አመለወርቅ ህዝቅኤል ገልፀዋል፡፡

ትምህርት ሚንስቴር ለአቅም ማሻሻያ ትምህርት የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ያደረገ ሲሆን ይህን የአቅም ማሻሻያ ትምህርት መስጠት የሚፈልጉ የግል ከፍትኛ የትምህርት ተቋማትም በዚሁ መሰረት ተማሪዎች ተቀብለው ማስተማር የሚችሉ ሲሆን በቅድሚያ ግን የመዘገቧቸውን ተማሪዎች ለትምህርት እና ስልጠና ባለስልጣን ማሳወቅ እንደሚኖርባቸው ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም የልህቀት ማእከል ተብለው በተለዩ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በኩል የተዘጋጀ የአቅም ማሻሻያ ሪሜዲያል ትምህርት ማስተማሪያ ተዘጋጅቶ ለሁሉም የመንግስት እና የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መላኩን ጠቁመዋል፡፡

አያይዘውም የማስተማሪያ ሰነዱ ለተማሪዎቹ ከ 9ኛ ክፍል እስከ 12ኛ ክፍል ያለውን ትምህርት አጠቃሎ የያዘ ሲሆን ሁሉም የትምህርት ተቋማት ማስተማር የሚችሉት ይሄንን በመጠቀም መሆን እንዳለበት ለአሀዱ በሰጡት ቃል አመላክተዋል፡፡

ለተጨማሪ መረጃ

@EthioUniversty1 @EthioUniversty1
749 viewsedited  19:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-06 20:14:08
በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል 760 ሺህ 832ቱ ወደ ቴክኒክ እና ሙያ ተቋማት ገብተው እንደሚሰለጥኑ የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር አስታወቀ።

በቴክኒክ እና ሙያ ተቋማት የሚሰጠው ሥልጠና ወደ ደረጃ ስምንት ከፍ እንዲል ተደርጓል።

የሥራ እና ክህሎት ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፣ በሀገር አቀፍ ደረጃ በ2015 ዓ.ም ወደ ቴክኒክ እና ሙያ ተቋማት ሊገቡ የሚችሉ ሠልጣኞች ቁጥር 760 ሺህ 832 ሲሆን፣ 20 በመቶ የሚሆኑት ከቴክኒክ እና ሙያ ውጪ ባሉ ማሠልጠኛ ተቋማት ይገባሉ።

በመሆኑም በአገር አቀፍ ደረጃ ቴክኒክ እና ሙያ የሚገቡት ሠልጣኞች ቀጥር 608 ሺህ 666 መሆናቸውን አስታውቀዋል።

በ2015 ዓ.ም የመቁረጫ ነጥብ የሠልጣኞች ድልድል የኢንዱስትሪውን የሰው ኃይል አሰላለፍ መሠረት በማድረግ የተሰላ በመሆኑ ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች የሥራ ገበያውን፣ የሰው ኃይል ፍላጎት እና የአከባቢውን የልማት ቀጠና መሠረት በማድረግ ቅበላ ማድረግ እንዳለባቸው ገልጸዋል።

መቁረጫ ነጥቡ የ2014 ዓ.ም 12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተናን የወሰዱ ተማሪዎችን ታሳቢ ተደርጎ የተሠራ በመሆኑ ለ2015 ዓ.ም ብቻ የሚያገለግል መሆኑን ያነሡት ሚኒስትሯ፣ መቁረጫ ነጥቡን እስካሟሉ ድረስ በመረጡት የሥልጠና መስክ በመንግሥት እና የግል ማሠልጠኛ ተቋማት ላይ መሠልጠን የሚችሉ መሆናቸውን አብራርተዋል።

ለተጨማሪ መረጃ

@EthioUniversty1 @EthioUniversty1
727 viewsedited  17:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-06 20:13:13
#MaddaWalabuUniversity

በ2015 ዓ.ም በመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የአቅም ማሻሻያ ሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች ምዝገባ መጋቢት 7 እና 8/2015 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሄዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➧ የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ፣
➧ ከ8-12ኛ ክፍል የትምህርት ማስረጃዎች ዋናውና ኮፒው፣
➧ ጉርድ ፎቶግራፍ፣
➧ የሌሊት አልባሳት፣
➧ የስፖርት ትጥቅ፣
➧ የኮቪድ-19 መከላከያ ማስክ፡፡

ከተጠቀሱት ቀናት ውጪ የሚመጡ ተማሪዎችን የማያስተናግድ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል።

ለተጨማሪ መረጃ

@EthioUniversty1 @EthioUniversty1
669 viewsedited  17:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-06 15:51:30
#WolaitasoddoUniversity #ExitExam

➭ለሁሉም የመደበኛ እና ተከታታይ ትምህርት
ተመራቂ ተማሪዎች በሙሉ!!
═════════❁✿❁═════════
በመጪው ሀምሌ ወር በሁሉም የትምህርት መስኮች እና መርሀግብሮች (በመደበኛ እና ተከታታይ) ተመራቂ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና /Exit Exam/ እንደሚሰጥ ይታወቃል።

የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደርም የካቲት 29/2015 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ በዋናው ግቢ በሚገኘው ሁለገብ መሰብሰቢያ አዳራሽ የመውጫ ፈተናን /Exit Exam/ በተመለከተ ከመደበኛ እና ተከታታይ የትምህርት መርሀ ግብር ተመራቂ ተማሪዎች ጋር የጋራ ውይይት መድረክ አዘጋጅቷል።

በመሆኑም የመውጫ ፈተና /Exit Exam/ በተመለከተ እስካሁን በዩኒቨርሲቲው በተሰሩ እና ቀጣይ ትኩረት ተሰጥቷቸው የሚተገበሩ ተግባራትን አስመልክቶ በተዘጋጀ የውይይት መድረክ ላይ ሁሉም የመደበኛና ተከታታይ ትምህርት ተመራቂ ተማሪዎች በተጠቀሰው ሰዓት እንዲገኙ የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር በጥብቅ ያሳስባል።

         ጥያቄ ና አስተያየት ለመስጠት
 

ለተጨማሪ መረጃ

@EthioUniversty1 @EthioUniversty1
716 viewsedited  12:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-06 11:30:14
Mizan-Tepi University
Light of the green Valley!

ለትምህርት ፈላጊዎች የወጣ ማስታወቂያ

፨ዝርዝር መረጃ ከምስሉ ይመልከቱ

ለተጨማሪ መረጃ

@EthioUniversty1 @EthioUniversty1
958 viewsedited  08:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-06 11:23:25 #awolkiteUniversity #Extension

ለሪሚዲያል (REMEDIAL) ትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ በ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የሪሚዲያል (REMEDIAL) ትምህርት ፈላጊዎችን ትምህርት ሚኒስቴር ባወጣው መስፈርት መሰረት ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል። ስለሆነም በሳምንት መጨረሻ መርሃ ግብሮች በማህበራዊ እና ተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፍ ማመልከት የምትፈልጉ አመልካቾች ከየካቲት 22 - 29/2015 ዓ.ም ድረስ ብቻ ዋና ሬጅስትራር ጽ/ቤት በአካል በመቅረብ ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

፨ዝርዝር መረጃ ከምስሉ ይመልከቱ

ለተጨማሪ መረጃ

@EthioUniversty1 @EthioUniversty1
724 viewsedited  08:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-05 17:16:31 #ትውስታዎቻችን

ታድያስ ቤተሰቦች ....ሰላሌ ዩኒቨርስቲ በመጀመሪያ ዓመት የገጠመኝን ገጠመኝ ላጫውታችሁ
አንድ ቀን ምሽት ነው ወደ ዶርም ልገባ ስል 2 ፖሊሶች በር ላይ ነበሩ ያው ተግባቢ ስለሆንኩ ሰላም አልኳቸው ሰላም አሉኝና አንዱ ይሄን ማብሪያ ማጥፊያ(switch) ማነው የሰበረው አለኝ አላቅም አልኩት ለምንድነው ምትሰብሩት ሲለኝ ጥጋበኛ ይሆናል የሰበረው ከቤተሰቦቻችን በተለቀመ ብር ተሰርቶ የሀገረ ሀብት ምናምን ስለው አሪፍ ነው አስተሳሰብህ አለኝ ከዛ ደና ደሩ ብያቸው ገባሁ። ስገባ ጫት እየቃሙ ነበረ የዶርም ልጆች እኔ ዝምብዬ handout ማንበብ ጀመርኩ ትንሽ ቆይቶ ዶርምተሪ መጣ በሩ አልተቆለፈም ነበር በርግዶ ሲገባ ጫቱን አየ ምንም ሳይል ቀጥ ብሎ ሄዶ ፖሊስ ጠራ። እስኪመጣ ግን ጫቱን በመስኮት ወረወሩ። የመጡት ፖሊሶች አጋጣሚ ቅድም ያዋራዋቸው ነበሩ። ብቻ ባጭሩ ወደ ውጪ አስወጥተው ደበደቡን በመሀል አንዱ ፖሊስ አየኝና አንተ ጥሩ ልጅ አልነበርክ እንዴ? አለኝ ከዛ ዶርምተሪው አይ እሱ ና ያ የሉበትም ብሎ ገባን።

ለተጨማሪ መረጃ

@EthioUniversty1 @EthioUniversty1
861 viewsedited  14:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-05 11:41:47 የዩንቨርሲቲ መውጫ ፈተና ጋር በተያያዘ የጅማ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ህብረት ከትምህርት ሚኒስቴር አመራሮች ያገኙትን መረጃ እናጋራቹህ

1. ጥያቄ፡- የመዉጫ ፈተናው የሚሰጠዉ ከምርቃት ቧላነዉ ወይስ በፊት?

፨መልስ፡- የመውጫ ፈተና አንድ ተመራቂ ተማሪ ከመመረቁ በፊት በትምህርት ህግ ማሟላት ያለበት መስፈርት ሰለሆነ ፈተናዉ የሚሰጠዉ ከ ምርቃት አስቀድሞነዉ፡፡

2.ጥያቄ፡- ፈተናው በኦንላይንነዉ ወይስ ወረቀት?

፨መልስ፡- ፈተናው የሚሰጠዉ ኦንላይንነዉ። ሁሉም ጥያቄዎች ምርጫ ብቻ ናቸው።የሒሳብ ጥያቄዎችም ስለሚኖሩ ተማሪዎች ወረቀት እና ኢስክሪፕቶ ይዞ ይገባሉ።

3.ጥያቄ: - ፈተናዉ የሚሰጥብት በቋሚነት መቼነዉ?

፨መልስ፡- ከ ሰኔ 20 እስከ ሐምሌ 20 ባሌ ጊዜ ዉስጥ ይሰጣል

4.ጥያቄ፡ ስለ ሞጁል የተነሳ ጥያቄ

፨መልስ፡-የተለያዬ ሞጁል ሆኔ የሚለዉ ተማሪዉ ጊዜዉን ሰያባክን በዲፐርትመንት በኩል በሰነድ መልክ የተላከለትን (Core Competencies) ላይ ተመርኩዞ ተጨማሪ የማንበቢያ ማቴሪያሎችን እና የሚሰጡ ቲቶሪያሎችን በመከተታል ለፈተናዉ መዘጋጀት ይችላል ፡፡

5 ጥያቄ፡- በፈተና ወቅት የሚሰጠዉ ሰዓት አጠቃቀሙ ምን ይመስላል የሚላዉ ነዉ፡፡

፨መልስ፡- ለዚህ ፈተና አዲስ ሶፍትዌር ተፈብርኮ ተዘጋጅቷል። ለዚሁ አላማ ተብሎ የተዘጋጀ ማለት ነዉ።አዲስ ሶፍትዌር ለየት ሚያደርገዉ ለአንድ ጥያቄ ብቻ ሰዓት ሰጥቶ የሚያልፍ ሳይሆን ለአጠቃላይ ጥያቄ የተሰጠዉን ሰዓት ተፈታኙ ሚችለዉን ጥያቄዎችን እንዲሰራ ሙሉ ሰዓቱ የተሰጠዉ እስኪያልቅ የሚጠብቅ እና አስተራረሙ ደግሞ ተማሪው ሙሉ መዉጫ ፈተናውን ከጨረሰ በኋላ ነው ዉጤቱን የሚያየዉ፡፡እዛዉ ይታረማል ከፈተና ክፍል ሳይወጣ የሚለዉ ወሬ ሀሰት ነዉ ሁሉንም የትምህርት ፈተናዎችን ከጨረሰ በኋላ ዉጤቱን ማወቅ ሚቺለዉ፡፡

6 ጥያቄ ፦የጥያቄ ብዛት ምን ያህል ነው?

፨መልስ በ አጭሩ ለማስረዳት በአንድ ዲፓርትመንት 17 ኮርስ ለመዉጫ ፈተና የሚሰጥ ከሆነ እነኚህ 17ቱ ኮርሶች ለ 5 ግሩፕ ተከፍለው ነው ፈተናዉ ሚወጣው። ለ አንድ ግሩፕ 100 ጥያቄ ማለት ነዉ። ይህ ማለት ደግሞ ለ 5 ግሩፕ ከ 500 ይሆናል ማሌትነዉ፡፡

የጅማ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ህብረት

ለተጨማሪ መረጃ

@EthioUniversty1 @EthioUniversty1
885 viewsedited  08:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ