2023-03-04 14:49:30
የዩኒቨርስቲዎች ጥሪ
#ወልድያዩኒቨርሲቲ
በ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የአቅም ማሻሻያ/Remedial Program/ ፕሮግራም ለመከታተል ከትምህርት ሚኒስቴር ወልድያ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ
ከየካቲት 30/2015 ዓ.ም እስከ መጋቢት 01/2015 መሆኑን አውቃችሁ በተጠቀሱት ቀናት በአካል ተገኝታችሁ ምዝገባ እንድታደርጉ ዩንቨርሲቲው አሳውቋል።
#ቦንጋ_ዩኒቨርሲቲ
በቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በ2015ዓ.ም በአቅም ማሻሻያ ፕሮግራም(Remedial Program) የተመደባችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ቀን መጋቢት 01-02/2015 ዓ.ም መሆኑን ዩንቨርሲቲው አሳውቋል።
#በእንጅባራ_ዩኒቨርሲቲ
የማካካሻ ትምህርት ለመውሰድ በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ ተማሪዎች በሙሉ፦
እንጅባራ የካቲት 27 እና 28/2015 ዓ.ም ያደረገው የተማሪዎች ቅበላ 50% እና ከዚያ በላይ ላመጡ በቀጥታ ወደ ዩኒቨርሲቲ ለሚገቡ ተማሪዎች ብቻ ነው።
የማካካሻ ትምህርት ለመውሰድ የተመደባችሁ ተማሪዎች በአሁኑ ጥሪ ያልተካተታችሁ መሆኑን አውቃችሁ ወደ ፊት በማስታወቂያ እስከሚገለጽ ድረስ ባላችሁበት ሆናችሁ በትዕግስት እንድትጠባበቁ ዩኒቨርሲቲው ያሳውቃል።
#ወሎ_ዩኒቨርሲቲ
በ2015 ዓ.ም ወሎ ዩኒቨርሲቲ ለአቅም ማሻሻያ ትምህርት (Remedial Program) የተመደባችሁ ተማሪዎች በሙሉ የመግቢያ ጊዜ መጋቢት 4 እና 5/2015 ዓ.ም መሆኑን ዩንቨርሲቲው አስውቋል።
#ባህርዳር_ዩኒቨርሲቲ
በ2015 ዓ/ም በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የ‛Remedial” ፕሮግራም ለመከታተል ለተመደባችሁ ተማሪዎች በሙሉ
በ2015 ዓ/ም የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም ለመከታተል ወደ ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ቀናት የካቲት 29 እና 30 ቀን 2015 ዓ/ም መሆኑን ዩንቨርሲቲው ገልጿል።
#HaramayaUniversity
በ2015 ዓ.ም በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች ምዝገባ መጋቢት 08, 09 እና 10/2015 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።
#DirredawaUniversity
በሬሚድያል ፕሮግራም ወደ ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ለተመደባቹ የሪድሚያል ፕሮግራም ተማሪዎች የምዝገባ ቀናት መጋቢት 01-02/2015 መሆኑን ዩንቨርሲቲው አሳውቋል።
#SelaleUniversity
በሬሚድያል ፕሮግራም ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ ለተመደባቹ ተማሪዎች የሪድሚያል ፕሮግራም ምዝገባ የካቲት 29-30/2015 መሆኑን ዩንቨርሲቲው አሳውቋል።
#ጅማ_ዩኒቨርስቲ
በ2015ዓ.ም የት/ት ዘመን በጅማ ዩኒቨርስቲ ለተመደባችሁ አዲስ የተመዝገባችሁ የካቲት 29 እና 30/2015ዓ.ም እንደሚካሄድ ዩንቨርሲቲው አሳውቋል።
Share Share
@EthioUniversty1 @EthioUniversty1
376 viewsedited 11:49