2023-03-10 19:40:24
TENSION
ጭለላ
(ለ 1ኛ አመት ተማሪዎች ይድረስልኝ)
ግቢ ላይ ከሚያጋጥሙን ጥቂት ችግሮች ውስጥ አንዱ ከልክ ያለፈ ጭንቀት ወይም በግቢ ስሙ #Tension ብለን የምንጠራው ነገር ነው።
ይሄ ችግር ብዙውን ጊዜ በአንደኛ አመት ተማሪዎች ላይ በስፋት የሚስተዋል ቢሆንም በሁሉም ዘንድ ማለትም ተመራቂ ተማሪዎችንም ሳይቀር የሚያጦዝ ደስ የሚል ሙድ ያለው ጭለላ ነው።
እኔ ግን ጥሎብኝ የሚሰማኝ ሰው ሳገኝ ብዙ አወራለሁና ዛሬም ከሰማችሁኝ ትንሽ ስለ ግቢ Stress or Tension ባካፍላቹህ ደስ ይለኛል ፤ በተጨማሪም አዲስ ገቢ ተማሪዎች ለቴንሽን አዲስ በመሆናቸውና ከሁሉም በይበልጥ የታላላቆቻቸውን ምክር ስለሚቀበሉ ይቺን ምክር እንድታደርሱልኝ አደራ ማለት እወዳለሁ
አይይ እንግዲህ ብዙ አታቅራራ ፡ ወደ ገደለው ግባ
Tension ብዙውን ጊዜ የሚገጥመን የሆነ ክስተት አንጎላችንን ሲቦጠብጠው እንደሆነ የአንጎል ስፔሻሊስትና የሳይኮሎጂ ሊቅ ለመሆን የሚመኙት Dr abz ይገልፃሉ አስከትለውም ጭንቅላታችን በጣም በሚጨናነቅበት ጊዜ የሚገጥመን failure ነው ይላሉ ።
ስልካችንን አንዳንዴ busy ሲሆን stack እንደሚያደርገው ማለታቸው ነው።
በግቢ ተማሪዎች ሳይኮሎጂ ላይ ከፍተኛ ጥናት ያደረጉት ኢንጂነር ዱባለ እንደጠቀሱት ደግሞ " ግቢ ውስጥ ብዙውን ጊዜ ተማሪዎች በተለይም አንደኛ አመት ተማሪዎች ፈተና በሚቃረብበት ወቅት የሚገጥማቸው ከፍተኛ መጨናነቅ መንስኤው አስቀድመው ተገቢውን ዝግጅት አለማድረጋቸው ነው" በማለት ይጠቅሳሉ ።
እኔም የኢንጂነሩን ጥናት ዋቢ በማድረግ የተወሰኑ ገጠመኞቼን ላካፍላቹህ
*አንደኛ አመት ተማሪ እያለሁ Drawing ኮርስ አጨልሎኝ አድሮ ጥዋት ከፈተና በፊት ካፌ ላይ የተፎገርኩት ፉገራ እስካሁን ሳስታውሰው ያስቀኛል ፤ (አሁን ግን Drawing የለም )
ምን መሰላቹህ pictorial drawing የሚሉት ነገር አልገባህ ብሎኝ እንቅልፍ ባይኔ ሳይዞር ወረቀት ላይ አፍጥጬ ስላደርኩ መሰለኝ ከምላቹህ በላይ ጭልል ብዬ ነበር
እናም ምንም ቁምነገር ሳልይዝ ነጋና ቁርስ መብያ ሰዓት ደርሶ ሁሌም አብሮኝ የሚበላው ጓደኛዬ ጋር በመሆን ወደ ካፌ ሄድን ፡ ስንደርስም ያን ጨርቅ የመሰለ ፊቴን ታጥቤ ወደ ሆድ ሸንቁሬው አዝግ ሰልፍ አመራን ፥ የማይደርስ የለምና ተራችን ደርሶ ባንደኛው እጃችን ትሪና ኩባያ ይዘን በሌላኛው ደግሞ binder( for drawing exam) ይዘን ወደ ጨላፊዎች ተጠጋን ጨላፊዋም ትሪህን አስጠጋ ስትለኝ ትሪዬን' ሰጠኋት ፨ የሚገርማቹህ ትሪ ብዬ ፍርፍሩን የተቀበልኩት በ binderu ነበር እሷም አውቃ ይሁን እንደኔ ጨልላ ባላቅም ጭልፋ ሙሉ ፍርፍር በትሪዬ' ሞላችልኝ kikikikikiki
በBindeሬ ፍርፍር ማስደረጌን ያስተዋልኩት አብሮኝ የነበረው ጓደኛዬ በሳቅ ፍርፍር ብሎ ፍርፍሩ ሲደፋበት ነበር ።
ብዙ ተማሪ እየሳቀብኝ እንደሆነ ሳይ ደግሞ ይብስኑ የምገባበት ጠፋኝ ( ሳሳዝን)
እንዴትም ብዬ ከዛ ደባሪ ሙድ በመውጣት ፍርፍሬን ወደ ትሪዬ ገልብጬ ወደ መቀመጫዬ በመሄድ በእልህ ምግቡን ስበላው እሱም ለካ ቂም ይዞብኝ ነበር አነቀኝ ፡ ባክህ አልሰማህም በሻይ ድራሽህን ነው ማጠፋው ብዬ ወደ ኩባያዬ እጄን ስሰድ አለወትሮዋ ኩባያዋ ቀለለችኝ ምንሼ ነው ብዬ ወደ ኩባያዬ ሾፍ ሳደርግ ሻይም ሳላስቀዳ ነበር የተቀመጥኩት ( አይ drawing)
ድጋሚ ይስቁብኛል ብዬ ባልፈራ ኖሮ ተነስቼ ሻይ አስቀዳ ነበር ግን ምንም ማድረግ አይቻልም ከጓደኛዬ እየተዋስኩ ታሪካዊ ቁርሴን በላሁ ።
ከካፌው ወጣ ብለን እጃችንን በመታጠብ ላይ ሳለን ሳላስበው ጧ ብዬ ሳቅኩ አብሮኝ የነበረው ጓደኛዬ በመገረም " ይሄ ልጅ ዛሬ ምን ነካው" ሲል ባሰብኝ ....
እንዴት ብዬ ልንገረው ገና ት ብዬ ስጀምር ሳቄ ይቀድመኛል እንዴትም ብዬ በምልክት ወደ ትሪው ጠቆምኩት ፥ ደንግጦ ትሪውን ይዞ ወደ ካፌ ሲሮጥ ህዝቤ ፈተናዋን ረስታ ሳቀችበት
ብድር በምድር አሉ ፥ ለካስ freind ከኔው ብሳ ትሪዋን ይዛ ወደ ፈተና ልትገባ ነበር
የሚገርም ግጥምጥሞሽ እያልኩ ፏ ብልጭ ብዬ ተፈተንኩ እላቹሃልው ።
ተረቴን መልሱ አፌን በዳቦ አብሱ*
Final exam ሲቃረብ እንደዚህ አይነት የካፌ comedy መመልከት የተለመደ ነው ምክንያቱ ደግሞ ቅድም ኢንጅነሩ የጠቀሱት ቅድሚያ አለመዘጋጀት ነው።
ፈተና ሲደርስ ከሚስተዋሉ ገጠመኞች ውስጥ ጥቂቶቹ
ካፌ ላይ መፎገር
ስልክን library, class, cafe etc መርሳት ወይም መጣል
Calculator መርሳት / መጣል
PC መርሳት ለዛውም space ( class)
ያነበቡትን መርሳት
ራስን መሳት ( በተለይ ሴቶች)
ወዘተ....
ታድያ ምን ይሻላል
የሚሻለውማ
ፈተና ሳይደርስ ሁሉንም course cover ማድረግ
ከጭንቀታም ጓደኛ መራቅ ( በሰላሙ ሰአት እናንተ ስታነቡ ከማያነበው ማለቴ ነው)
ከጎበዝ ተማሪ ጋር መጎዳኘትና አብሮ ማንበብ
ጥያቄዎችን በgroup መስራት
ስለ ፈተና አወጣጥ ከታላላቆቻችን መጠየቅ ( from seniors)
Information gather ማድረግ
ከበግ ተራ በመራቅ ሴቶችን info መጠየቅ ( affirmative ምናምን ብለው ....)
በተረፈ Tension መጠኑ ይለያይ እንጂ አይቀሬ ነገር በመሆኑ ፈታ በሉ።
እንደኔ እንደውም Tension ምንም የማይዘው ተማሪ ካሮት አምራች ገበሬ ይመስለኛል፤ ምክንያቱም አንብቦ ሳይሆን የሚፈተነው position አስተካክሎ ነው ።
ሲበዛ ነው እንጂ የማይነፋው ተማሪ ካነበበ እስከሚፈተን ድረስ Tension Normal ነው።
ጨርሻለሁ (በ Eng.Muja የተዘጋጀ )
ለተጨማሪ መረጃ
@EthioUniversty1 @EthioUniversty1
554 viewsedited 16:40