Get Mystery Box with random crypto!

Ethio University

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiouniversty1 — Ethio University E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiouniversty1 — Ethio University
የሰርጥ አድራሻ: @ethiouniversty1
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 4.85K
የሰርጥ መግለጫ

ለማንኛውም አይነት የማስታወቂያ ስራ እና ክሮስ(Cross)
💰💰 @Cozboy0 💰💰
ያናግሩን🎫🎟🎪🎪🎪🎪

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2023-03-19 22:34:50
የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ህብረት በቅርቡ በስሙ በተሰራጨው መረጃ ዙርያ በትላንናው እለት መጋቢት 09/2015 ዓ.ም ያወጣውን ሙሉ መግለጫ ይመልከቱ

Share share
ለተጨማሪ መረጃ

@EthioUniversty1 @EthioUniversty1
483 viewsedited  19:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-19 22:32:10
#አሳዛኝ_ዜና

4 የቀብሪ ደሃር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በመኪና አደጋ ህይወታቸው አለፈ።

ትላንት መጋቢት 9 ቀን 2015 ዓ/ም በደረሰ የመኪና አደጋ 4 የቀብሪ ደሃር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ህይወታቸው ማለፉን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ዩኒቨርሲቲው ስለ አደጋው ዝርዝር መረጃ ባይሰጥም አደጋው እጅግ በጣም አስደንጋጭ ድንገተኛ ክስተትና መላው የተቋሙን ማህበረሰብ መሪር ሃዘን ላይ የጣለ ነው ብሏል።

ተቋሙ በመኪና አደጋ ህይወታቸው እንዳለፈ ካሳወቃቸው ተማሪዎች ሶስቱ የሶስተኛ ዓመት ተማሪዎቹ አንዱ ደግሞ የአራተኛ አመት ተማሪ መሆኑን ገልጿል።

፨በደረሰው ድንገተኛ አደጋ ህይወታቸው ላለፉ ተማሪዎች ቤተሰቦች፣ጓደኞቻቸው እንዲሁም ለመላው የየቀብሪ ደሃር ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ መፅናናት እንመኛለን።

Share share
ለተጨማሪ መረጃ

@EthioUniversty1 @EthioUniversty1
459 views19:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-19 13:29:06
ጅማ ዩኒቨርሲቲ የእንስሳት ደህንነትና ጤና ማሻሻያ ማሰልጠኛ ማዕከል አስመርቋል።

ማዕከሉ የጅማ ዩኒቨርሲቲ የእንስሳት እና ግብርና ኮሌጅ፣ ብሩክ ኢትዮጵያ ከተባለ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ጋር በመተባበር በ5.1 ሚሊዬን ብር ወጪ የተገነባ መሆኑ ተገልጿል።

ማዕከሉ በእንስሳት ህክምና ዘርፍ ለሚሰማሩ ባለሙያዎች የተሻለ ስልጠና ለመስጠት የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል።

Share share
ለተጨማሪ መረጃ

@EthioUniversty1 @EthioUniversty1
554 viewsedited  10:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-18 19:35:48
#HaramayaUniversity

ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የአቅም ማጠናከሪያ (ሪሚዲያል) ፕሮግራም ተማሪዎችን በመቀበል ላይ ይገኛል።

ዩኒቨርሲቲው እስከ እሁድ መጋቢት 10/2015 ዓ.ም ድረስ ተማሪዎቹን መቀበል ይቀጥላል።

Share share
ለተጨማሪ መረጃ

@EthioUniversty1 @EthioUniversty1
610 viewsedited  16:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-18 19:34:15 " ትምህርት ቤቶቹን በመጪው ሚያዝያ ወር እንደገና ለመክፈት ዕቅድ ተይዟል " - UNICEF

በትግራይ በጦርነቱ ምክንያት ከሁለት ዓመታት በላይ ተዘግተው የነበሩ ትምህርት ቤቶችን እንደገና ለመክፈት ዕቅድ መውጣቱ ተገልጿል።

በትግራይ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው ከመራቃቸው ባለፈ መምህራንም ለሁለት ዓመታት ደመወዝ አልተከፈላቸውም።

ትምህርት ቤቶቹን በመጪው #ሚያዝያ_ወር እንደገና ለመክፈት ዕቅድ እንደተያዘም የዩኒሴፍ (UNICEF) የትምህርት ኃላፊ ቻንስ ብሪግስ ተናግረዋል።

ኃላፊው ይህን ያሉት BBC Focus on Africa ሬዲዮ ተናግረዋል።

" በትግራይ ሙሉ በሙሉ የትምህርት ሥርዓቱ ፈርሷል። " ያሉት ቻንስ ብሪግስ " ካለፈው ዓመት ሐምሌ ወር ጀምሮ 2.3 ሚሊዮን ህጻናት ከትምህርት ገበታ ውጪ መሆናቸው የሚያሳይ መረጃ አለን "  ብለዋል።

በመቐለ ከባለቤታቸው እና ከአራት ልጆቻቸው ጋር ነዋሪ የሆኑት አቶ መንግሥት ገብረመድኅን የእርስ በርስ ጦርነቱ በተቀሰቀሰበት ወቅት ሁለቱ ልጆቻቸው የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን ይከታተሉ ነበር።

ትምህርት ከተቋረጠም በኋላ " እነሱን ለማስተማር ሞከርኩ፣ ነገር ግን መረጋጋት እና ትኩረታቸውን መሰብሰብ አልቻሉም " ብለዋል።

" የአየር ጥቃቶች እና የድሮን ጥቃቶች ድምጽ ይሰማሉ። ህጻናቱን ጠመንጃ ይዘው የሚሄዱ ወታደሮችንም ያያሉ። እነሱንም ለማስመሰል ይሞክራሉ። " ሲሉ የነበረውን ሁኔታ ገልጸዋል።

በመቐለ ዩንቨርስቲ ረዳት ፕሮፌሰር የሆኑት አቶ መንግሥት ለወራት ደመወዝ ሳይከፈላቸው መቆየቱን ተናግረዋል።

" ደመወዛችን አየተሰጠን ስላልነበር ልጆቻችን ምን እንደምንመግባቸው ያስጨንቀን ነበር። ስለዚህ እነሱን በማስተማር ላይ ማተኮር ፈታኝ ነበር። ነገር ግን ትናንትና ደመወዜን ተቀበልኩ፣ አሁን ለልጆቼም ልብስ እና ምግብ መግዛት እችላለሁ " ብለዋል።

በትግራይ በነበረው ጦርነት ከዛም በፊት በነበረው የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ሚሊዮኖች ተማሪዎች  ከትምህርት ገበታቸው ርቀዋል ፤ መምህራን ደግሞ በጦርነት ምክንያት ደሞዝ ሳይከፈላቸው ቆይቷል።

#ቢቢሲ #BBCFocusonAfrica

Share share
ለተጨማሪ መረጃ

@EthioUniversty1 @EthioUniversty1
557 viewsedited  16:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-18 19:19:34
#Updated
ለአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም ተማሪዎች በሙሉ የጥሪ ማስታወቂያ ጥቆማ፥
......................................
በዲላ ዩኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ የአቅም ማሻሻያ ተማሪዎች የመመዝገቢያ ቀናት የፊታችን መጋቢት 14 እና 15/2015 ዓ.ም እንደሆነ መግለፃችን ይታወሳል። ስለሆነው ተማሪዎች በተጠቀሱት ቀናት የተፈጥሮ ሳይንስ መስክ ተማሪዎች በኦዳያአ ግቢ እና የማህበራዊ ሳይንስ መስክ ተማሪዎች ደግሞ በሐሴዴላ ግቢ ቀርባችሁ እንድትመዘገቡ እየገለፅን።

የጥሪውን ዝርዝር ማስታወቂያ በኢቲቪ ( Ethiopian Broadcasting Corporation ) በኩል ከምሽት 2:00 ዜና በኋላ ዛሬ ቅድሜ፣ ነገ እሁድ እና ከነ ወዲያ ሰኞ እንድትከታተሉ እንጠይቃለን።

ዲላ ዩኒቨርሲቲ
የአረንጓዴው ምድር ዩኒቨርሲቲ

Share share
ለተጨማሪ መረጃ

@EthioUniversty1 @EthioUniversty1
492 viewsedited  16:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-18 17:43:48
አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና የኦሮሚያ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ባለስልጣን የጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ


አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ከኦሮሚያ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ባለስልጣን ጋር አብሮ መስራት የሚያስችለውን የጋራ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሟል፡፡
የመግባቢያ ስምምነቱን የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር አብርሃም ደበበ እና የኦሮሚያ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ባለስልጣን ስራ አስፈፃሚ አቶ መኮንን በያና ቡሾፍቱ አዶላላ ሪዞርት ተፈራርመዋል፡፡
የመግባቢያ ሰነዱ አላማ በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና በኦሮሚያ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ባለስልጣን መካከል በምርምር እና ልማት፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር እና አቅም ግንባታ ላይ ታማኝ ትብብር መፍጠር ነው።
ከዚህ ጋር ተያይዞ ሁለቱ ተቋማት ራዕያቸውን እና ተልዕኮዎቻቸውን እውን ሊያደርጉ የሚችሉ የትብብር መስኮችን ለይተዋል እነርሱም በጋራ ምርምር ስራዎችን መስራት ፤ በእውቀት እና በቴክኖሎጂ ሽግግር፣ በማማከር አገልግሎቶች፣ የአጭር እና የረጅም ጊዜ የስልጠና ፕሮግራሞችን ያካተተ ነው፡፡ስምምነቱ የሁለቱ ተቋማት ግንኙነት በትምህርት እና በምርምር ስራዎች እኩል ተጠቃሚ የሚያደርጋቸው መሆኑ ተገልፃል፡፡

ምንጭ፡ የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ህዝብና አለምአቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት።


Share share
ለተጨማሪ መረጃ

@EthioUniversty1 @EthioUniversty1
524 viewsedited  14:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-17 19:21:43
የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ለዲግሪ የሚሰጡት ግምት እያነሰ መምጣቱን አንድ ጥናት አመላከተ!

ከግዜ ወደግዜ የትምህርት ጥራት መጎደል በትምህርት ስርዓቱ ላይ ከሚነሱ ጋሬጣዎች አንዱ ሲሆን ይህ ችግር ካመጣቸዉ ዉጤቶች ዉስጥ ደግሞ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ለዲግሪ የሚሰጡት ግምት እንዲያንስ ማድረጉን በኢትዮጵያ የስነምግባር ማዕከል የተሰራ አንድ ጥናት አመላክቷል።

ጥናቱ በተካሄደባቸው የአዲስአበባ ፣ ባህርዳር ፣ ጎንደር እና አዳማ የዩኒቨርስቲዎች የሚገኙ ተማሪዎች ሰጡ በተባለዉ ምላሽ ፤ ተማሪዎቹ "ዲግሪ ቢይዙ ምንም የተለየ ነገር እንደማያገኙ" ምላሽ ሰጥተዋል ተብሏል። በተጨማሪም አንዳንድ ተማሪዎች ዩኒቨርስቲ የገቡት ቤተሰብ ለማስደሰት አልያም ከወላጆች በሚመጣ ጫና በመሆኑ እንጂ በፍላጎት እና እዉቀት ለመቅሰም ከሚኖር ተነሳሽነት አለመሆኑን ተማሪዎቹ በጥናቱ ምላሻቸዉን ሰጥተዋል።

አንዳንድ ተማሪዎች ከተመረቁ በኋላ ስራ አጥ መሆናቸውን ከመመረቃቸዉ በፊት ስለሚረዱ የትምህርት ስርዓቱ አይነተኛ ለዉጥ ሊያመጣ አለመቻሉን የኢትዮጵያ ስነምግባር ማዕከል ገልጿል። ይህንንም ለማሻሻል የሲቪክ ማህበራት ሀላፊነት ያለባቸው በመሆኑ የክርስቲያን በጎ አድራጎት እና ልማት ማህበራት ህብረት ከኢትዮጵያ ስነምግባር ማዕከል ጋር በመቀናጀት በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ላይ እንዲሁም በማህራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ሽግግር ላይ ስላለዉ የስነምግባር መጓደል ለሁለት ቀናት ዉይይት ሲያካሂድ ቆይቷል።

Share share
ለተጨማሪ መረጃ

@EthioUniversty1 @EthioUniversty1
661 viewsedited  16:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-16 21:37:00
#Update

የሀላባዋ ታዳጊ ሊዲያ በ30ሺ ብር ዋስትና እንድትፈታ ተወሰነ።

ባለፉት ቀናት በእስር የቆየችውን ታዳጊ ሊዲያ በተመለከተ በዛሬው ዕለት 07/07/2015 ዓ.ም የከሰዓቱ የወንጀል ጉዳዮች ችሎት ለሀላባ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የጠበቆች ቡድን ባቀረበው የዋስትና መብት ላይ ብይን ሰጥቷል።

በዚህም መሠረት ታዳጊ ሊዲያ አበራ የዋስትና መብቷ ተጠብቆ በ30,000 ብር ዋስ እንድትፈታ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት መወሰኑን ጠበቃ አበባየሁ ጌታ ገልጿል።

በሀለባ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ10ኛ ክፍል ተማሪ የሆነችው ታዳጊ ሊዲያ አበራ የካቲት 22/2015 ዓ.ም. ተማሪዎች ላይ መተት አሰርተሻል በሚል ከትምህርት ቤቷ ተወስዳ መታሰሯ ይታወሳይታወሳ።

Share share
ለተጨማሪ መረጃ

@EthioUniversty1 @EthioUniversty1
277 viewsedited  18:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-16 21:13:13 በትግራይ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች ለሰራተኞቻቸው ደመወዝ መክፈል ሊጀምሩ ነው ተባለ

በትግራይ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ለሰራተኞቻቸው ደመወዝ ለመክፈል በዝግጅት ላይ እንደሚገኙ አስታወቁ። የገንዘብ ሚኒስቴር ለሰራተኞች ውዝፍ ደመወዝ መክፈያ እና የአንድ ወር የስራ ማስኬጃ በጀት፤ ባለፈው አርብ መጋቢት 1፤ 2015 እንደፈቀደላቸው ዩኒቨርሲቲዎቹ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል።

ተጠሪነታቸው ለፌደራል ትምህርት ሚኒስቴር የሆኑ አራት ዩኒቨርስቲዎች በትግራይ ክልል ይገኛሉ። በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ምክንያት የመማር ማስተማር አገልግሎታቸውን አቋርጠው የሚገኙት እነኚህ አራት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት፤ የመቐለ፣ አክሱም፣ አዲግራት እና ራያ ዩኒቨርስቲዎች ናቸው።

“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ያነጋገረቻቸው የመቐለ፣ አክሱም እና ራያ እና ዩኒቨርሲቲ አመራሮች፤ በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ምክንያት ላላፉት 20 ወራት በዩኒቨርሲቲዎቹ ለሚሰሩ ሰራተኞች ደመወዝ አለመከፈሉን ገልጸዋል። ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ አንድ የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራር፤ የሰራተኞችን ውዝፍ ደመወዝ ጉዳይ ከገንዘብ ሚኒስቴር አመራሮች ጋር በነበራቸው ስብሰባ ወቅት ገልጸዋል።

በዚሁ ስብሰባ ላይ የሚኒስቴሩ ኃላፊዎች፤ “ ‘ሌላውን የሲቪል ሰርቪስ ሰራተኛም ግምት ውስጥ ባስገባ መልኩ መንግስት ውሳኔ የሚሰጥበት ይሆናል’ የሚል ምላሽ መስጠታቸውንም አስታውሰዋል። የዚሁ ስብሰባ ተሳታፊ የነበሩት የአክሱም ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ፕ/ር ገብረየሱስ ብርሃነ በበኩላቸው፤ “መንግስት በልዩ ሁኔታ የሚወስነው ውሳኔ እንዳለ ነው የተነገረን” ሲሉ የሰራተኞች ውዝፍ ደመወዝን በተመለከተ ጉዳዩ ከሚመለከተው የፌደራል ተቋም የቀረበውን መልስ ጠቅሰዋል።

የገንዘብ ሚኒስቴር ይህ ስብሰባ በተካሄደ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ባሳለፈው ውሳኔ፤ የዩኒቨርስቲዎቹ ሰራተኞች ደመወዝ እንዲከፈል በጀት መልቀቁ ታውቋል። የፌደራል ተቋማት ለሆኑት አራቱ ዩኒቨርስቲዎች ሰራተኞች የደመወዝ ክፍያ የሚሆን ገንዘብ መተላለፉን የገንዘብ ሚኒስቴር ምንጮች ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” አረጋግጠዋል። “የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ገና ስላልተመሰረተ፤ ለክልሉ የተላከ ገንዘብ የለም” ሲሉም የሚኒስቴሩ ምንጮች አክለዋል። 


Share share
ለተጨማሪ መረጃ

@EthioUniversty1 @EthioUniversty1
276 viewsedited  18:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ