Get Mystery Box with random crypto!

Ethio University

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiouniversty1 — Ethio University E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiouniversty1 — Ethio University
የሰርጥ አድራሻ: @ethiouniversty1
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 4.85K
የሰርጥ መግለጫ

ለማንኛውም አይነት የማስታወቂያ ስራ እና ክሮስ(Cross)
💰💰 @Cozboy0 💰💰
ያናግሩን🎫🎟🎪🎪🎪🎪

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2023-03-28 17:34:25
#ETA

በትምህርት ስልጠና ባለሥልጣን የትክክለኛነት ማጣራት ከሚደረግባቸው የትምህርት ማስረጃዎች ውስጥ ከ5 እስከ 10 በመቶ የሚሆኑት ሐሰተኛ ሆነው እንደሚገኙ ተቋሙ ኣሳውቋል፡፡

ማስረጃዎቹ በተጭበረበረ መንገድ ከመዘጋጀታቸው በተጨማሪ ከባለሥልጣኑ ዕውቅና ባላገኘ ተቋም አማካይነት የተሰጡ መሆናቸውን ባለሥልጣኑ ገልጿል፡፡

ማስረጃዎቹ በብዛት የትምህርት ክፍሉን ለማስተማር ፈቃድ ሳይኖረው ከሚያስተምር የትምህርት ተቋም የተወሰዱ መሆናቸውን በባለሥልጣኑ የተቋማት ቁጥጥርና ኢንስፔክሽን የትምህርት ማስረጃ ማረጋገጥ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ቸሩጌታ ገነነ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል።

የግል እና የመንግስት ተቋማት የሠራተኞቻቸውን የትምህርት ማስረጃ ትክክለኛነት ወደ ተቋሙ ልከው እንዲጣራ የማድረግ ፍላጎታቸው እየጨመረ እንደሚገኝ ኃላፊው ጠቁመዋል፡፡

ለተጨማሪ መረጃ


@EthioUniversty1 @EthioUniversty1
270 viewsedited  14:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-28 03:09:22 #NationalExam

" ምዝገባውን ያላደረገ ተማሪ የመልቀቂያ ፈተናውን አይፈተንም " - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች ምዝገባ ከመጋቢት 20 እስከ ሚያዚያ 15/2015 ዓ.ም እንደሚከናወን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ምዝገባ በበይነ መረብ አማካይነት እንደሚከናወን ነው የተገለፀው።

የፈተና ሂደት ላይ ችግር እንዳይፈጠር ተማሪዎች መረጃዎቻቸውን በወቅቱ ማስመዝገብ እንዳለቸው ማሳሰቢያ ተላልፏል።

የመደበኛ እና የማታው ክፍለ ጊዜ ተማሪዎች ምዝገባ በትምህርት ቤቶች እንደሚካሄድ የተጠቀሰ ሲሆን ተማሪዎች የምዝገባ ሂደቱን ለማካሄድ በአካል መገኘት ይኖርባቸዋል፡፡

የድጋሚ ተፈታኞች እና የርቀት ተማሪዎች ምዝገባ ደግሞ በተመረጡ የወረዳ ትምህርት ጽ/ቤቶች ይካሄዳል።

የምዝገባ ሂደቱ በተጠቀሱት ቀናት ተከታታይ የሥራ ቀናት የሚከናወን ሲሆን ምዝገባውን ያላደረገ ተማሪ የመልቀቂያ ፈተናውን እንደማይፈተን አገልግሎቱ አሳውቋል።

የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የመልቀቂያ ፈተና በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ይሰጣል።

ለምዝገባ ምን ያስፈልጋል / ተማሪዎች ምን ማሟላት አለባቸው ?

- መደበኛ ተመዝጋቢዎች ከ9 - 12ኛ ክፍል በተከታታይ ሲማሩ የነበሩ እና በ2015 ዓ.ም  በመማር ላይ መሆን ይጠበቅባቸዋል።

- የማታ እና የርቀት ተማሪዎች የ11ኛ ክፍል ሶስት ሴሚስተር እንዲሁም ለ12ኛ ክፍል የሁለት ሴሚስተር የትምህርት ማስረጃ ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።

- ድጋሜ ተፈታኞች ከዚህ ቀደም የተፈተኑበትን የትምህርት ማስረጃ በመያዝ መመዝገብ አለባቸው።

- ተማሪዎች ለምዝገባ ሲመጡ ማንነታቸውን የሚገልፅ መታወቂያ በመያዝ በአካል ተገኝተው በበይነ መረብ መመዝገብ ይጠበቅባቸዋል።

ፈተናው መቼ እና የት ይሰጣል ?

ፈተናው የሚሰጥበት ቀንን በተመለከተም  ፈተናው በዩኒቨርስቲ ውስጥ እንደሚሰጥና ቀኑ ወደ ፊት የሚገለፅ መሆኑን ዋና ዳይሬክተሩ ገልፀዋል።

Credit : #MoE

ለተጨማሪ መረጃ


@EthioUniversty1 @EthioUniversty1
404 viewsedited  00:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-28 02:59:04 #ተጨማሪ

የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች ምዝገባ ከመጋቢት 20 እስከ ሚያዚያ 15/2015 ድረስ ለመደበኛና የማታ ተማሪዎች በመንግሥት የመደበኛ ትምህርት ቤቶች ለድጋሜ ተፈታኞች እና የርቀት ትምህርት ተማሪዎች በተመረጡ የወረዳ ትምህርት ጽ/ቤቶች አማካኝነት በበይነ መረብ #ብቻ እንደሚያካሂዱ ተገልጿል።

መደበኛ ተመዝጋቢዎች ከ 9 እስከ 12ኛ ክፍል በተከታታይ ሲማሩ የነበሩ እና በ2015 በመማር ላይ ያሉ መሆን ይጠበቅባቸዋል ተብሏል።

ተማሪዎች ማንነታቸውን የሚገልፅ መታወቂያ በመያዝ በአካል ተገኝተው በበይነ መረብ መመዝገብ እንደሚጠበቅባቸውም ተገልጿል።

በመግለጫውም ተማሪዎ፣ ወላጆች፣ መዝጋቢዎች እና ከመምህራን የሚጠበቅባቸውን ሃላፊነት እንዲወጡ  የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ጥሪ አቅርቧል።

ፈተናው የሚሰጥበት ቀንን በተመለከተም ፈተናው በዩኒቨርስቲ ውስጥ እንደሚሰጥና ቀኑ ወደ ፊት የሚገለጽ መሆኑን ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።

ለተጨማሪ መረጃ


@EthioUniversty1 @EthioUniversty1
396 viewsedited  23:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-27 12:46:06 #ExitExam

ምን ያህል ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ይወስዳሉ ?

የትምህርት ሚኒስቴር የኮሚኒኬሽን እና ህዝብ ግንኙነት ስራ አስፈፃሚ አመለወቅር ህዝቅኤል በዚህ ዓመት የሚሰጠውን የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና በተመለከተ (ምን ያህል ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚወስዱ፣ ዝግጅት እና ፈተናውን ማለፍ የማይችሉ ተማሪዎችን በተመለከተ) ከሰሞኑን ለቪኦኤ ሬድዮ ቃላቸውን ሰጥተው ነበር።

ምን አሉ ?

ወ/ሮ አመለወርቅ እዝቅኤል ፦

" አሁን የለየናቸው አሉ ፤ የደረሰን መረጃ አለ ወደ 240 ሺህ ተማሪዎች ናቸው እጃችን ላይ ያሉት።

ነገር ግን ጥር ላይ በተለያየ ምክንያት ያላጠናቀቁ ልጆች በአንደኛ ሴሚስተር የሚያጠናቅቁና ወደ ምዘናው ሊመጡ የሚችሉ ልጆች ሊኖሩ ይችላሉ።

ከዛ ባሻገር የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በዚህ System ውስጥ የሚያልፉ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የደረሱን መረጃዎች አሉ።

አሁን በቁጥር ነው የተቀበልነው ልክ እንደ ሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና በስም እያንዳንዱ ስም በሚመጣ ሰዓት የተወሰነ የቁጥር ለውጥ ሊኖረው ይችላል አሁን ባለንበት ሁኔታ ወደ 240 ሺህ ተማሪዎችን እንፈትናለን ብለን እናስባለን።

ከመጀመሪያው ጀምሮ በዩኒቨርሲቲዎች በኩል ተማሪዎች መረጃው እንዲደርሳቸው ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ እየተሰራ ነው የሚገኘው። ከዛ ባሻገር አንዳንድ ዩኒቨርሲቲዎች ሞዴል ፈተናዎች እንዲፈተኑ በማድረግ፣ Sociologically እንዲዘጋጁ እንዲያጠኑ እየተሰራ ነው ተማሪዎችን በዛ ልክ አውቀው እየሰሩ ነው።

ፈተናው እንዴት manage ይደረጋል በሚለው ላይ የተለያዩ ማስፈፀሚያዎች ወደ ታች ወርደዋል በዚያ መሰረት ቅድመ ዝግጅቶች እየተደርጉ ነው የሚገኙት። "

የመጀመሪያውን ፈተና የማያልፉ ተማሪዎች ዕጣ ፋንታ ምንድነው ?

" ፈተናውን ያላለፉ ተማሪዎች መልሰው መላልሰው የሚወስዱበት ዕድል አለ።

ይሄ የሚሆነው እንዴት ነው የመጀመሪያው ዙር መንግሥት በራሱ መንገድ የሚያስኬደው ነው ከዛ በኃላ ልክ 12ኛ ክፍል Private እንደሚፈተነው ሁሉ መውጫ ፈተና ላይም ዝግጁ ነን በሚሉ ሰዓት በተዘጋጁ እና ይሄን ፈተና አልፋለሁ ብለው እራሳቸውን አብቅተው በሚመጡበት ሰዓት መፈተን ይችላሉ። ተፈትነው ሲያልፉ ዲግሪያቸውን የሚወስዱበት አሰራር አለ።

እስከዛ ድረስ ደግሞ ለምሳሌ የመውጫ ፈተና የዩኒቨርሲቲ ዲግሪ የሚያስገኘውን ፈተና ማለፍ ባይችሉ እንኳን ዝቅ ባሉ ደረጃዎች በLevel ደረጃ ባሉት (ከዲግሪ በታች ባሉ መመዘኛዎች) ተፈትነው ልክ COC እንደሚፈተነቱ ተፈትነው ማለፍ የቻሉበት ደረጃ ላይ Certify ይደረጋሉ በዛ ስራ ማግኘት የሚችሉበት አማራጭ ይኖራቸዋል። "

ለተጨማሪ መረጃ


@EthioUniversty1 @EthioUniversty1
530 viewsedited  09:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-26 13:01:16 #Point #ForRemedial #ShareForAll

ዩኒቨርስቲ ላይ ውጤት መስራት አስቸጋሪ ነው የ Remedial ተማሪዎች አራት ወር ቆይታችሁ ወደ ቤት መመለስ የማትፈልጉ ካሁኑ በደንብ #ማንበብ ይኖርባችኋል።

ከዚህ በፊት የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች  አብዛኞቹ ከ 100 ውስጥ 40 ማምጣት እየከበዳቸው "D" ይመጣባቸው ነበር  በዩኒቨርስቲ የምትማሩ Remedial ተማሪዎች ጥንቃቄ ማድረግ አለባችሁ።

በተለይ ከ 30% ዩኒቨርስቲ ላይ ያለውን ውጤት ከ 20% በላይ መስራት አለባችሁ ከ 70% አጠቃላይ ፈተና ስለሆነ ልከብዳችሁ እና ላትሰሩት ትችላላችሁ።

ክላስ አልተማርንም ብላችሁ አጠብቁ ትምህርት ሚኒስቴር ያዘጋጃቸውን Outline በራሳችሁ ማንበብ ጀምሩ ዩኒቨርስቲ ላይ መምህራን ሁልጊዜ ክላስ አይገቡም ከዛ በአንድ ክላስ 4 Chapter ጨርሶ ይወጣል ይሄ ለናንተ አይፈይድም ።

ሁለቱን መማር የምትፈልጉ መመዝገብ እና ቪዲዮዎችን ማግኘት ይችላሉ።

በተረፈ ካሁኑ ማንበብ ጀምሩ በኋላ እንዳይቆጫችሁ 50% እና ከዛ በላይ ማምጣት አስቸጋሪ ልሆንባችሁ ይችላል። ኩረጃ የሚባል አይኖርም።

በርግጥ ሁሉም አልፎ #Freshman መማር ይፈልጋል ስለዚህ Library ካሁኑ ማንበብ ብትጀምሩ ይመረጣል።

Share share
ለተጨማሪ መረጃ


@EthioUniversty1 @EthioUniversty1
624 viewsedited  10:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-25 20:18:29
#KEU

ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ለ2015 ዓ.ም የቅድመ ምረቃ መርሃ ግብር ዕጩ ተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ሞዴል ፈተና ሰጥቷል፡፡

ሞዴል ፈተናው ዕጩ ተመራቂ ተማሪዎቹ ተገቢውን ዕውቀትና ክህሎት መያዛቸውን ለመገምገምና ክፍተቶችን በቀጣይም ለመሙላት የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡

በቀጣይ ሁለተኛ ሞዴል የመውጫ ፈተና ለተማሪዎች በግንቦት ወር አካባቢ በኢንተርኔት አማካይነት እንደሚሰጥ የዩኒቨርሲቲው የአግባብነትና ጥራት ማረጋገጫ ዳይሬክቶሬት ገልጿል።

Share share
ለተጨማሪ መረጃ


@EthioUniversty1 @EthioUniversty1
175 viewsedited  17:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-25 20:16:00
ወልድያ ዩኒቨርሲቲ በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ ያሰለጠናቸውን 592 ተማሪዎች አስመርቋል።

ከተመራቂዎቹ 235 የሚሆኑት በወልድያ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ ስልጠናቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ናቸው።

ዩኒቨርሲቲው በሌሎች መስኮች ያሰለጠናቸውን የመጀመሪያ እና የሁለተኛ ዲግሪ፣ የከፍተኛ ዲፕሎማ (HDP) እና የPGDT ሰልጣኞችንም አስመርቋል።

በ2004 ዓ·ም የመማር ማስተማርና የምርምር ሥራ የጀመረው ወልድያ ዩኒቨርሲቲ፤ በወልድያ፣ በመርሳ እና በላሊበላ ግቢዎች እያስተማረ ይገኛል።

Share share
ለተጨማሪ መረጃ


@EthioUniversty1 @EthioUniversty1
163 viewsedited  17:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-25 10:54:17 ሰላም ውድ ቤተሰቦች! እኒህን ድንቅ ትምህርታዊ ቻናሎች ግን Join አድርጋችኋል ካላደረጋችሁ አሁኑኑ ተቀላቀሉ። ለትምህርት ሂወታችሁ ያስፈልጓችኋል።

>> Ethio Science and Astronomy >> በዚህ ቻናል በየቀኑ ከአለም የተሰበሰቡ አዳዲስ እና ቆየት ያሉ ሳይንሳዊ ፁሑፎች የሚለቀቅበት ቻናል ነው።

ይቀላቀሉ Join us Here !

@ethiotefer1 @ethiotefer
=====================

>> Habesha Cyber >>
ሰለ ኮንፒተር ፕሮግራሚንግ እንዲውም ሰለ ሐከሮች ይፃፍል እንዲውም እንዴት የሌሎችን ስልክ እንደምትጠልፉ ትምህርት ትወስዳላቹ።

ይቀላቀሉ Join us Here !

@habeshatech2 @habeshatech2
==================

>>Ethio-English-Lerne>>

This channel help you learn english in simple way. Join and get more knowledge in English language

ይቀላቀሉ Join us
Here !

@ethioenglish1 @ethioenglish1
>> ሰለ ኮከቦ ይወቁ>>
የተወለዳቹበት ወር ሰለናት እንደሚናገር ያውቃሉ?

ይቀላቀሉ join us

@ethioastrology1 @ethioastrology1

>>Ethio University >>

የ 2014 የ 12ኛ ክፍል ውጤት ከ 50% በታች አምጥተው #Remedial ለመከታተል ላሰቡ እንዲውም ለውቃቲዊ መረጃዎች።

ይቀላቀሉ join us
@EthioUniversty1 @EthioUniversty1

>>Yegna ቁምነገር>>

ሁሉንም ነገር የሚያገኙበት ወቅታዊ እንዲውም ሳይንሳዊ ፁሑፎች የሚለቀቁበት ቻናል ነው።

ይቀላቀሉ join us
@ethioastrology
@ethioastrology
323 views07:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-24 20:23:54
#ማስታወቂያ

ጅማ ዪኒቨርስቲ ባለፈው የትምህርት ዘመን የተሻለ ውጤት ያመጡ ተማሪዎችን መሸለም ይፈልጋል።

ለሴት Cgpa 3.25 እና በላይ
ለወንድ Cgpa 3.85 እና በላይ

ያመጣችሁ ተማሪዎች ግሬድ ሪፖርታችሁን በተባለው ቢሮ ቁጥር ከ18-20/07/2015 ባሉት ቀናት ማስገባት ትችላላችሁ።

Share share
ለተጨማሪ መረጃ


@EthioUniversty1 @EthioUniversty1
466 viewsedited  17:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-24 12:24:29
ሠራተኞችን ለቅጥር ከሚያቀርብ የትኛውም ድርጅት ጋር የሥራ ስምምነት የለኝም! የኢትዮጵያ አየር መንገድ

ሠራተኞችን ለቅጥር ከሚያቀርብ የትኛውም ድርጅት ጋር የሥራ ስምምነት እንደሌለው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታውቋል።

ከሰሞኑ ራሱን “እንቻለው ልጥገብ የአቪዬሽን ተቋም” ብሎ የሚጠራ ድርጅት ወይም ግለሰብ ሠራተኞችን ለቅጥር እንዲያቀርብ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ፍቃድ የሰጠው በማስመሰል ሰዎችን በማሳሳት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የከፈተውን የሒሳብ አካውንት በመጠቀም ገንዘብ በመቀበል ላይ እንደሚገኝ አየር መንገዱ ገልጿል።

ይሁንና ከተጠቀሰው ድርጅትም ይሁን ከየትኛውም ሠራተኞችን ለቅጥር ከሚያቀርብ ድርጅት ጋር የሥራ ስምምነት እንደሌላው አየር መንገዱ አስታውቋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሠራተኞችን የሚቀጥረው በራሱ ዌብሳይት መሆኑን በመጥቀስ፣ ከተቀጣሪዎች ምንም ዓይነት ክፍያ እንደማይቀበልም ነው የገለጸው።

በመሆኑም ሥራ ፈላጊዎች በነዚህ ድርጅቶች ሳይታለሉ ለሥራ ቅጥር መረጃዎች የአየር መንገዱን ድረገጽ Ethiopian Airlines-Careers እንዲከታተሉ ማሰሳቡን ከአየር መንገዱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል ሲል EBC ዘግቧል።

Share share
ለተጨማሪ መረጃ


@EthioUniversty1 @EthioUniversty1
494 viewsedited  09:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ