Get Mystery Box with random crypto!

የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በ2014 ዓ.ም ሀገር አቀፍ ፈተና ወስደዉ የአቅም ማሻሻያ ትመህርት ለመማር | Ethio University

የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በ2014 ዓ.ም ሀገር አቀፍ ፈተና ወስደዉ የአቅም ማሻሻያ ትመህርት ለመማር ወደ ዩኒቨርሲቲዉ የተመደቡትን ተማሪዎች ለመቀበል ዝግጅት ማጠናቀቁን ገለፀ፡፡
በ2014 ዓ.ም የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና ወስደዉ የማለፍያ ነጥብ ያመጡ ተማሪዎች ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ገብተዉ የአቅም ማሻሻያ ትምህርት እንዲማሩ ትምህርት ሚኒስተር ማሳወቁ ይታወሳል፡፡

በመሆኑም መንግስት ያስቀመጠዉን አቅጣጫ መሠረት በማድረግ በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የተመደቡትን ተማሪዎች ለሁለት ተከታታይ ቀናት መጋቢት 4 እና 5 ለመቀበል ዝግጅት ማጠናቀቁን የዩኒቨርሲቲዉ ተማሪዎች አገልግሎት ጉዳይ ዳይሬክተር ፕሮፌሰር ቦሩ በደያ ገልፀዋል፡፡

እንደ ዳይሬክተሩ ገለፃ ከሆነ የአቅም ማሻሻያ ትምህርቱን እንዲማሩ የተመደቡት ተማሪዎች ጠቅላላ ብዛታቸዉ 2700 ሲሆኑ ከነዚህም 1346 ሴት ተማሪዎች መሆናቸዉን አሳዉቀዋል፡፡

በመጨረሻም የተመደቡት ተማሪዎች ምንም ዓይነት ስጋት ሳይኖርባቸና ትምህርታቸዉን የሚከታተሉበት ሁኔታ እንደሚመቻች ዳይሬክተሩ ገልፀዋል፡፡


ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ


ለተጨማሪ መረጃ

@EthioUniversty1 @EthioUniversty1