Get Mystery Box with random crypto!

ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የ2013 በጀት ዓመት የኦዲት ግኝት ላይ የማስተካከያ እርምጃ መውሰድ መጀመ | Ethio University

ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የ2013 በጀት ዓመት የኦዲት ግኝት ላይ የማስተካከያ እርምጃ መውሰድ መጀመሩን አሳውቋል።

በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ወጪ አስተዳደር እና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲን የ2013 በጀት ዓመት የኦዲት ሪፖርትን መገምገሙ ይታወቃል።

ቋሚ ኮሚቴው ከዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት የተገኘውን የሒሳብ ህጋዊነት ኦዲት ሪፖርት መነሻ በማድረግ ለዩኒቨርሲቲው የማስተካከያ አቅጣጫዎችን አስቀምጧል።

ቋሚ ኮሚቴው ባስቀመጠው አቅጣጫ መሠረት ማስተካከያ ለመውሰድ፤ የዩኒቨርሲቲው ማኔጅመንት ግኝቱን ለማረም ከተቋቋመ ግብረ ኃይል ጋር መክሯል።

የፋይናንስ ህግጋትና አሰራሮችን ተከትሎ ከመስራት አኳያ የነበረውን የአሰራር ክፍተት በማረም በቀጣይ ጊዜያት ከኦዲት ግኝት ነጻ ለመሆን ተቀናጅቶ መስራት ተገቢ መሆኑን ማኔጅመንቱ ገምግሟል።

ያለ አግባብ የተከፈሉ ክፍያዎች በፍጥነት ተመላሽ እንዲሆኑ ማኔጅመንቱ ወስኗል።