Get Mystery Box with random crypto!

በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለተማሪዎች የምግብ አገልግሎት የሚመደበው በጀት ማስተካከያ እንዲደረግበት | Ethio University

በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለተማሪዎች የምግብ አገልግሎት የሚመደበው በጀት ማስተካከያ እንዲደረግበት ተቋማቱ ጠይቀዋል።

እስካሁን ባለው አሰራር ለተማሪዎች ቀለብ በቀን ለአንድ ተማሪ 15 ብር ሲበጀት ቆይቷል፡፡ ዩኒቨርሲቲዎች ግን ለአንድ ተማሪ በቀን እስከ 100 ብር እንደሚያወጡ ይገልጻሉ፡፡

አሁን ባለው የኑሮ ውድነት ምክንያት ለሌላ ሥራ የሚመደበው በጀት ለተማሪ ምገባ እየዋለ መሆኑን አስተያየታቸውን ለኢፕድ የሰጡ የዩኒቨርሲቲ አመራሮች ገልጸዋል፡፡ መንግሥት ወቅታዊ ገበያውን መሠረት ባደረገ መልኩ የዋጋ ማሻሻያ ሊያደርግ ይገባልም ብለዋል፡፡

ለዩኒቨርሲቲዎቹ ለምግብ አገልግሎት የሚመደበውን በጀት ለማስተካከል ትምህርት ሚኒስቴር መመሪያውን የማሻሻል ሥራ እየሠራ መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር የአስተዳደርና መሠረተ ልማት መሪ ሥራ አስፈጻሚ ሰለሞን አብርሀ (ዶ/ር) ገልጸዋል፡፡

በ19 ዩኒቨርሲቲዎች ላይ የተደረገ ጥናትን መሰረት ያደረገ አማካይ የምግብ ዋጋ ለገንዘብ ሚኒስቴር መቅረቡን ሥራ አስፈጻሚው አስረድተዋል፡፡

ለተጨማሪ መረጃ


@EthioUniversty1 @EthioUniversty1