Get Mystery Box with random crypto!

#የትምህርትና_ስልጠና_ባለሥልጣን የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በሀገር አቀፍ ደረጃ በ2014 | Ethio University

#የትምህርትና_ስልጠና_ባለሥልጣን

የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በሀገር አቀፍ ደረጃ በ2014 ዓ.ም ብቻ እርምጃ የወሰደባቸው የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ካምፓሶችና ቅርንጫፎች ብዛት #357 ደርሷል።

ባለሥልጣኑ በ5ኛ ዙር የስነ ስርዓት ጥሰት ፈጽመው በመገኘታቸው የማስተካከያ እርምጃ የወሰደባቸውን 25 ካምፓሶችና ቅርንጫፎችን ይፋ አድርጓል።

ባለስልጣኑ በ2014 ዓ.ም ብቻ በአዲስ አበባ ከተማ እና በክልል ከተሞች በሚገኙ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ ባደረገው ድንገተኛ ፍተሻ የመመሪያ ጥሰት ፈጽመው የተገኙ ካምፓሶች እና ቅርንጫፎቻቸውን በአምስት ዙር አሳውቋል።

በ1ኛ ዙር በአዲስ አበባ (106) እንዲሁም በክልል ከተሞች በ2ኛ ዙር (95)፣ በ3ኛ ዙር (104)፣ በ4ኛ ዙር (27) እና በ5ኛ ዙር (25) በድምሩ #357 የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ የማስተካከያ እርምጃ መወሰዱን ባለስልጣኑ ገልጿል።

ተቋማቱ የእርምት እርምጃ የተወሰደባቸው የእውቅና ፈቃድ ባልተሰጠባቸው ካምፓሶች፣ ቅርንጫፎች እና የትምህርት መስኮች ተማሪ ተቀብለው ሲያስተምሩ፣ የእውቅና ፈቃድ እድሳት ባልተሰጠባቸው የትምህርት መስኮች መዝገበው ሲያስተምሩ በመገኘታቸው መሆኑ ተመላክቷል፡፡