Get Mystery Box with random crypto!

በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በዩኒቨርሲቲዎች መሰጠቱ በርካታ ጠቀሜታዎች እንደሚኖሩት | Ethio University

በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በዩኒቨርሲቲዎች መሰጠቱ በርካታ ጠቀሜታዎች እንደሚኖሩት  የፈተናዎች አገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር እሸቱ ከበደ ገልፀዋል፡፡

የፈተና ስርቆትና ኩረጃ  ላይ ከፍተኛ ቁጥጥር በማድረግ ተማሪዎች የራሳቸውን ብቻ እንዲሰሩ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ ፈተናውን በማጓጓዝ ወቅት የሚያጋጥሙ ችግሮችንም ለመፍታት ትልቅ እገዛ እንዲሚኖረውም አብራርተዋል፡፡

ተማሪዎችን በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ መፈተኑ የፈተናውን ሂደት ለማበላሸት ጥረት ከሚያደርጉ ሰዎችም ለመጠበቅ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንደሚኖረው ገልፀዋል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ መፈተናቸው ቀድመው ዩኒቨርሲቲዎቹን በአካል እንዲያውቋቸው ያደርጋልም ብለዋል።

ለፈተናው ተማሪዎች ተገቢውን ዝግጅት እንዲያደርጉና ወላጆችም አስፈላጊውን ድጋፍ ለልጆቻቸው እንዲያደርጉ ዋና ዳይሬክተሩ ጠይቀዋል።

የ2014ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሁለት ዙር በዩኒቨርሲቲዎች ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ እንዳለ ይታወቃል፡፡