የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎችን የሚያጓጉዙ ተሽከርካሪዎች እየተዘጋጁ እንደሚገኝ ተገለፀ ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ፈተና ለሚወስዱ 12ኛ ክፍል ተማሪዎች የትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠት እየተሰራ እንደሚገኝ የምስራቅ ጎጃም ዞን አስታውቋል ። በምስራቅ ጎጃም ዞን ለሚፈተኑ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ተሽከርካሪዎች እንዲሁም የመፈተኛ ተቋማት በማዘጋጀት በኩል ግብረሃይል ተቋቁሞ እየተሰራ እንደሚገኝ የምስራቅ ጎጃም ዞን ትምህርት መመሪያ ሀላፊ አ/ቶ ጌታሁን ፈንቴ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል ። በዞኑ ተማሪዎች የሚፈተኑባቸው አምስት ተቋማት እየተዘጋጁ እንደሚገኝ ተገልጿል ። የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከመስከረም 30 ጀምሮ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እንደሚሰጥ ቀደም ብሎ በትምህርት ሚኒስቴር መገለፁ ይታወቃል ። #ዳጉ_ጆርናል 555 views16:54