2023-07-23 13:28:57
የወተት ሻጩ ሃውልት ሂጃብ በሃገረ ቱርክ
“””””””””@“@“@“””””@“”””@“””””””@
አየህ ወንድሜ ተመልከች እህቴ ይህ በምስሉ የምትመለከቱት ታሪካዊ ሃውልት በቱርክ የሚገኝ እና የወተት ሻጩ ሃውልት በሚል ስታሜ የሚታወቅ ቅርስ ነው።
ይህ ሃውልት የሂጃብን አስፈላጊነት እና ትልቅነት ህያው ሆኖ የሚናገር እውነት ነው።
ይህ ሃውልት ለሂጃብ መከፈል ያለበትን መስዋእትነት በግልፅ የሚናገር እኔስ ብለህ እራስህን እንድትጠይቅ የሚያስገድድ እኔስ ብለሽ እራስሽን እንድትመረምሪ ቃል ሳያወጣ ግን የሚናገር ሃውልት ነው።
የወተት ሻጩ ሃውልት አሁንም በሀገረ ቱርክ ከነሙሉ ታሪኩ እና ክብሩ ቆሞ ይገኛል ። አሳዛኙ ጉዳይ ግን በዚህ ሃውልት አጠገብ ያለምንም አስገዳጅ በገዛ ፈቃዳቸው የተራቆቱ ሴቶች ሲያልፉ መመልከት ነው አሳዛኙ ግን ሂጃብ መልበስን እንደኋላ ቀርነት የሚያስቡ ወንዶች በዚህ ሃውልት ጎን ሲያልፉ ማየት ነው።
ነገሩ እንዲህ ነው የኦቶማን ቱርክ መውደቅን ተከትሎ ቱርክን የተቆጣጠሩት ፈረንሳዊያን ከተማዋን ሲያስሱ ሂጃብ ለባሽ ሴቶችን በመንገድ ላይ ያያሉ ጀነራሉም ድምፁን ከፍ አድርጎ “ይህን ኮተት እንድትለብሱ የሚያስገድዳችሁ አካል አሁን ወድቋል ።እናንተ ነፃ ህዝቦች ናችሁ ።አሁን ቱርክ በፈረንሳዩች እጅ ናት ።ክንብንባችሁን አውልቁ እና ስልጡን ህዝቦች ሁኑ “አለ።
ሴቶች አናወልቅም መራቆት እንሰሳነት እንጅ ስልጣኔ አይደለም አሉ ጀነራሉ አበደ ተናደደ ከአንዲት ቱርካዊት ላይ ሂጃቧን ለመግፈፍ እጁን ሰደደ በዚህ ጊዜ ነው እንግዲ ወተት ሻጩ አዛውንት ከቆመበት ተወርውሮ ጀነራሉ የታጠቀውን ሽጉጥ የነጠቀው በተለመደው ጠንካራ የቱርክ ጥፊ ከመሬት የደባለቀው እና በገዛ እራሱ ሽጉጥ ወደጀሃነም የላከው።
ቱርካዊያን ይህ ትልቅ ታሪክ በአፍ ብቻ እንዳይቀር ሲሉ ከጎዳናወቸቸው በአንዱ ላይ የወተት ሻጩን መታሰቢያ ሃውልት አቆሙ ።ሃውልቱ አሁን ላይ ያሉትን ሴት እና ወንድ ቱርካዊያን እያየ የሚገረም ይመስለኛል።
እኛም አገር ይህ ኋላ ቀርነት እንደስልጣኔ ተቆጥሮ ሂጃብን በከፊልም ይሁን በሙሉ መጣል እና መጣላችንን በምስክር ለማስረዳት በሚመስል መልኩ ቪዲዮ ቀርፀን ቲክቶክ ላይ መልቀቅ ይዘናል ።ሂጃብ ጥላ ፎቶ የለጠፈችን እህት ዋው ቆንጆ ስታምሪ ልዩ ነሽ የሚሉ ኮመንቶች የሚያደርጉ ወጣት ወንዶችም ተበራክተዋል።
ተይ ሂጃብ አድርጊ የሚሉ ለወተት ሻጩ የቀረቡ ወጣቶች በምላሹ የሚደርስባቸውን ስድብ ስንመለከት የፈረንሳዩ ጀነራል ሞቶም ምን ያህል ህያው እንደሆነ እንረዳለን።
ለምን?????
6.5K views10:28