Get Mystery Box with random crypto!

"ኡማ ቲቪ " Tv

የሰርጥ አድራሻ: @ethioomahtvchannle
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 44.00K
የሰርጥ መግለጫ

መረጃወችን ለወዳጄ ዘመድ ሼር ያርጉ!
የቴሌግራም ቻናላችን ከስር በሊንኩ ይቀላቀሉ👇
https://t.me/ UAKV32q7U2HKzEMf

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 9

2023-05-12 17:14:37
ጉዞ ወደ ኢስላም

በወራቤ ከተማ አቡበክር መስጂድ አንድ ቄስ ወደ ተፈጠርበት እምነት በኡስታዝ ሙሐመድ ከድር ዒሳ እጅ ወደ ኢስላም ተቀላቅሏል።
4.9K views14:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-12 15:50:20
ይህን ልጅ አስታወሳችሁት??

#ነፊስ_ያዕቆብ ይባላል ለስራ ሲል በህገ ወጥ መንገድ ወደ ማሌዥያ የገባ ታይላንዳዊ ወጣት ነው። አንድ ቀን ምሽት ታዲያ ከተደበቀበት አፓርታማ ምግብ ለመግዛት ይወጣል እንደ አጋጣሚ በመንገዱ ፓሊስ ያገኘዋል የመኖሪያ ፍቃድ ቢጠይቀውም ነፊስ እንደሌለው ይነግረዋል። ፓሊሱም ወደ ሃገሩ ሊመልሰው ወደ እስር ቤት ይዞት ይሄዳል።

እስር ቤቱ በጣም ሞቃታማ ስለነበር ነፊስ ቲሸርቱን አውልቆ በመቀመጥ ምግብ መጠበቅ ያዘ በዚህ ጊዜ ነበር በሚያምር ድምፁ የቁርአን አንቀፆችን #ቲላዋ ማድረግ የጀመረው በር ላይ የነበረው ፓሊስ ታዲያ  ይህን ድምፅ ሰምቶ ዝም ማለት አልቻለም ሞባይሉን በማውጣት  ቪዲዩ ሪከርድ አርጎ በኢንተርኔት ይለቀዋል ቪዲዩው በመላው አለም አድናቆትን አገኘ በሰፊው ተሰራጨ።

ቪዲዩውን ይመልከቱ

ነፊስ በዚህች ቪዲዩ ታዋቂ ሆነ ፓሊሶቹም ከእስር እንዲለቀቅ አደረጉ።በማሌዥያ አንድ መስጅድ ኢማም ሆነ ብዙ ሽልማቶችን ዶላሮችን ማግኘት ቻለ ያገኘውን ብዙ ዶላሮችም ለበርማ ስደተኞች ሰጠ።በአሁን ሰአት ነፊስ በማሌዥያ ከሚገኙ ታዋቂ  ኢማሞች አንዱ ነው። #ሱብሃን_አላህ

إن الله يرفع بهذا الكتاب أقواماً ويضع به آخرين
"አላህ በዚህ የአላህ ንግግር(ቁርዓን) ህዝቦችን ከፍ ያደርጋል! ሌሎችንም በዚሁ ቁርዓን ዝቅ ያደርጋል››" ረሱል ﷺ
5.1K viewsedited  12:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-12 14:34:48 ጁሙዓን የት ሃገር፣ የት መስጅድ ሰገዳችሁ? ኹጥባው ስለምን ነበር? ለሌሎችም እንዲጠቅም ከሰማችሁት ውስጥ የኹጥባውን ጭብጥ በአጭር አስፍሩት።
4.8K views11:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-12 09:13:14 የአልጀዚራ ቴሌቪዥን ጉብኝታችን


በኳታር ዶሃ የሚገኘውን የአልጀዚራ ሳተላይት ቴሌቪዥን ጣቢያን መጎብኘት እንደምፈልግ እና እንዲያመቻቹልኝ ወንድሞችን ጠየቅኩ። ከተለያየ ጥረት በኋላ የፓስፖርትና የቪዛ ኮፒያችንን እንድንልክ ተጠየቅን። ላክን።አስፈላጊው ማጣራት ከተደረገ በኋላ ፈቃድ ተሰጠን።መግቢያ ዲጂታል ካርድና ቀጠሮ ተላከልን። ከባልደረቦቼ መካከል አብረውኝ መጎብኘት ፈልገው የተመዘገቡት ሼህ ሐሚድ ሙሳ፣ሼህ ዛኪር ኢብራሂምና በዶሃ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ት/ቤት ወንድም አብዱልባሲጥ ጀማልና እኔ በቀጠሯችን በሰዓቱ ደረስን። በር ላይ ስማችን ስለተላለፈ ከአስፈላጊ ማጣራት በኋላ ታጅበን ወደ ዉስጥ ገባን።

የአረብኛውንና የእንግሊዘኛውን ስቱዲዩ ተዘዋውረን ጎበኘን። እጅግ ተጽዕኖ ፈጣሪ የሆነው አልጀዚራን እንደጠበቅሁት አላገኘሁት። ስቱዲዮውና ኤዲቲንግ ክፍሉ የተያያዘና ጠባብ ነው። የዜና፣የኢኮኖሚ፣የስፖርት፣የአየር ሁኔታ አርታኢዎች (ኤዲተሮች) እና ይዘቱ ላይ ዉሳኔ የሚሰጡት በሙሉ በአንድ ክፍል ዉስጥ በተጣበበ ክፍል ለዚያውም ከዋናው ስቱዲዮ ጎን ብቻ ሳይሆን በመካከላቸው ባለ መስታወት የተጋረደ ነው።

በእርግጥ የአልጀዚራ ቴሌቪዥን ኔትወርክ ቅጥር ጊቢው ከስቱዲዮው አንጻር ሲታይ ሰፊ ነው።በዉስጡ አልጀዚራ ዐረብኛ፣እንግሊዘኛ፣ ዶኩዩመንተሪ፣አልጀዚራ ላይቭ፣ የጋዜጠኞች ማሰልጠኛ ማዕከል እና ሌሎች ተያያዥ ግልጋሎት የሚሰጡ ማዕከላትን የያዘ ነው።

አልጀዚራ በአጠቃላይ በሁሉም ዘርፉ አራት ሺህ ሰራተኞች ሲኖሩት ኳታሩ ዋና ማዕከል በተጨማሪ በ20 የተለያዩ የዓለም ሀገራት ዉስጥ የራሱ ስቱዲዮች አሉት።የኳታሩ ስቱዲዮ ግን ተጽዕኖውን ስንመለከት እንደ ሀገረ ኳታር ሁሉ ስፍራው ጠባብ ነው።ኳታር በቆዳ ስፋቷ እጅግ ትንሽ ሀገር ስትሆን የሲዳማ ክልልን ወይንም የስልጤ ዞንን ታክላለች።በቆዳ ስፋት ኢትዮጵያ ኳታርን 100 ጊዜ ትበልጣለች።
4.9K views06:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-12 09:12:42
4.5K views06:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-12 08:25:11
ስለ የትኛውን መስጂድ ተናግረን ስለ የትኛውን መስጂድ እንተው?

በሸገር ከተማ ውስጥ ያሉት መስጂዶች ካርታ ያላቸውም የሌላቸውም ብሎ ነገር የለም ሁሉም የመፍረስ አደጋ ተገርጦበቸዋል

የመልካ ኖኖ ክፍለ ከተማ ቤሮ ወረዳ ደግሞ ይለያል ጧት ዩኑስ መስጂድን አፍርሱ ብሎ ቀይ ቀለም ቀብቶ ሄዶዋል።
4.8K views05:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-11 22:51:14
በኳታር -ዶሃ

ልዩ ዉይይት በኳታር ዶሃ ከኢትዮጵያ ሙስሊም ኮሚኒቲ ጋር። ነገ ጁምዓ ከቀኑ 10:00 ሰዓት ጀምሮ።
ቦታ -ፈናር ኢስላማዊ ማዕከል::
5.2K views19:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-11 22:42:46
ሸገር ሲቲን ሙስሊም አልባ ከተማ የማድረጉ ዘመቻ እንደቀጠለ ነው።
ማን ያስቁመው????

በሸገር ሲቲ ዙርያ መስጅድ ፈረሳው ዛሬም እንደቀጠለ ነው።
——————————————————————————
አሰላሙአለይኩም ወረህመቱላሂ ወበረካቱ አሸዋሜዳ ጠቼ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ልዩ ስሙ ኸድጀተል ኩብራ ተብሎ ሚጠራው መስጂድ ሊያፈርሱብን ቀብተውብናል ቶሎ አንሱ ብሎናል እባካቹ ድምፅ ሁኑን
——————————————————————————
ይህ መልእክት ከአካባቢው ነዋሪዎች ዛሬ ግንቦት 3 ደረሰኝ ። ወደተባለው መስጅድ ኮሚቴዎች ደውየ አጣራሁ ኮሚቴዎቹ የደረሰኝ መልእክት እውነት እንደሆነ ከፎቶግራፍ ማስረጃ ጋር አረጋገጡልኝ ።

ዛሬ ግንቦት 3 2015 ከአስር ሰላት በኋላ አፍራሽ ግብረሀይሉ ፈራሽ ቤቶች ላይ ምልክት እያደረጉ መስጅዱ ያለበት ቦታ ላይ ደረሱ ። ሰጋጆቹ እና ኮሚቴዎች መስጅድ ነው ይህን አትንኩ ቢሏቸውም ሃላፊው ግን ንቀት በተሞላበት አነጋገር “አትስሟቸው ሶስት ቦታ ላይ ምልክት አድርጉ “ብሎ ማዘዙን ኮሚቴዎች ነግረውኛል።

መስጅዱ የተመሰረተው ከ10 አመታት በፊት 2005 ሲሆን ከመጅሊሱ እውቅና ያገኘው ደግሞ ከተመሰረተ ከአምስት አመት በኋላ በ2010 ነው ።

ከ10 አመታት በላይ የተሰገደበት ይህ መስጅድ በአካባቢው የሚገኙ ህፃናት ቁርአን እና ኪታቦችን የሚማሩበት እንደሆነ ነዋሪዎች ነግረውኛል።

መጅሊሳችን ሆይ የፃፋችሁት ደብዳቤ ምን ላይ ደረሰ ???
የመስጅዶችን ፈረሳ ለማስቆም ምነው አቅም አጣችሁ???
በመስጅዶች ፈረሳ ዙርያ ዝመታችሁ አልበዛምን???

ሸር በማድረግ መስጅዱን ከመፍረስ እንታደግ
መስጅዶች ጉዳያችን ናቸው
5.5K views19:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-29 22:53:38
#ማሻ_አላህ
የየቲሞች አባት ኡስታዝ አብዱልፈታ ሸይኽ ሙስጠፋ
የChevrolet መኪና ሽልማት ተበረከተለት።
2.3K views19:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-29 21:39:14
በሀገረ ግብፅ አንዲት እናት የ5 አመት ልጇን አርዳ ሬሳውን አብስላ ከፊሉን እንደበላች በፖሊስ ተይዛ ለዐቃቤ ህግ ተላልፋ ስትሰጥ "ለዘልዓለም እንዳይለየኝ አካሉን ለመብላት ሞከርኩ" በማለት መናገሯን አልጀዚራ ዘግቧል።

"ዲን መያዝ ፍም የመጨበጥ ያህል ከባድ ይሆናል" ተብሎ በረሱል (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) አንደበት የተገለፀው ዘመን ይህ ነው እንዴ?!" በማለት አንድ ወጣት አላህን አብዝተው የሚፈሩትን ዓሊም ጠየቀ

ዓሊሙም በአርምሞ እየተመለከቱት "ያ ዘመንማ ካለፈ ቆይቷል። አሁን ያለንበት ዘመን "አንድ ሰው ሙስሊም ሆኖ ያነጋል። ካፊር ሆኖ ያመሻል። በጥቂት ዱንያዊ ጥቅም ዲኑን ይሸጣል" እንዲህ በረሱል አንደበት የተገለፀበት ዘመን ላይ ነን አሉት።
3.7K views18:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ