Get Mystery Box with random crypto!

"ኡማ ቲቪ " Tv

የሰርጥ አድራሻ: @ethioomahtvchannle
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 44.00K
የሰርጥ መግለጫ

መረጃወችን ለወዳጄ ዘመድ ሼር ያርጉ!
የቴሌግራም ቻናላችን ከስር በሊንኩ ይቀላቀሉ👇
https://t.me/ UAKV32q7U2HKzEMf

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 6

2023-05-20 19:55:02 ዛሬም አለም ባንክ ጋራ ላይ ዳሩል አርቀም እና ጀበል መስጂድ ፍዳ ተደርጓል!!
መስጂድ ዛሬም ፈርሷል!!
4.5K viewsedited  16:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-20 18:25:28
ነፃነትና እኩልነት ፓርቲ (ነእፓ) በመስጅድ ፈረሳው ዙሪያ ይህን መግለጫ ዛሬ አውጥቷል።
4.8K views15:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-20 17:10:30
በስፔሻሊስትና ሰብ ስፔሻሊስት ሀኪሞች  ቅዳሜና እሁድ እንዲሁም የበዓል ቀናትን ጨምሮ 24 ሰዓት አገልግሎት
እጅግ ዘመናዊ አውሮፓና ኮሪያ ሰራሽ የህክምና መሳሪያዎች በመጠቀም አገልግሎት እንሰጣለን።

አዲሱን 4D አልትራሳውንድ ቴክኖሎጂና በሌሎችም ዘመናዊ መሳሪያዎች የታገዘ ህክምናና የጤና ምርመራ ...።

➛የምንሰጣቸው አገልግሎት
ሙሉ የውስጥ ደዌ ህክምና

➛ሙሉ የማህፀንና ስንፅ እንዲሁም የእናቶች ህክምና

➛የማዋለድ አገልግሎት

➛የማህፀን ጫፍ ካንሰር ምርመራ

➛የፅንስ አፈጣጠርና እድገት ክትትል(including Anatomic Scaning)
በባለ 6 ፕሮብ 4D አልትራሳውንድ ማሽን

➛የኢኮካርዲዮ ግራፊ የልብ ምርመራ(የህፃናትና የአዋቂዎች)

➛ቀላል የቀዶ ጥገና ህክምና

➛ሙሉ የጤና ምርመራ

አይበለውና የጤና ችግር ከገጠማቹህ ወይም የታመመ ወዳጅ ዘመድ ካላቹህ ወደ ማዕከላችን በመምጣት ከፈጣሪ በታች ለህመማቹህ ፈውስ ታገኛላቹህ ።

ወደ ማዕከላችን ሲመጡ በአገልግሎታችን ተደስተው በዋጋችን ተማርከው ይመለሳሉ!!

➔አድራሻ አለም ባንክ ሂጅራና ኦሮሚያ ባንኮች ፊትለፊት

➾ስልክ ለማገኘት እነዚህን አማራጭ ይጠቀሙ !!
             0975033303
              0933332724
             0113694977
ህክምናውን የማዘመን ተግባራዊ ትጋት በዶ.ር መሊሀ ስፔሻላይዝድ ክሊኒክ

➭ለበለጠ መረጃ የቴሌግራም አድራሻችንን በመጠቀም ቤተሰብ ይሁኑ!!
t.me/DrMelihaMedicalCenter
1.5K views14:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-20 14:37:57
የትኛው ስልጣን ይኑርህ፣ከየትኛውን ብሄር ተወለድ፣ የትኛውንም የፓለቲካ መስመር ተከተል በዲንህ ግን እንደማትደራደር ይፋ ማድረግን አትፍራ!

የስራ እና ክህሎት ሚኒስትር ዴታ ክብርት Nebiha Mohammed Abedulhakim በመስጂድ ህልውና ዙሪያ የፃፉት ፅሁፍ

"ምድርን ያለሞሶሶ ያቆመ አንድ አላህ መኖሩን የሚክድ ካለ ማስተዋል የማይችል ነው ። ሰባት ሰማይንና ሰባት ምድርን ፈጣሪ አምላካችን ፈጥሯል እኛንም እንደዛው ። እኛ ሰዎች 50 ካሬ ላይ ቤት ለመስራት የማንጠቀመው ፌሮ ብረት ድንገይ ሲሚንቶ አሸዋ ሜትር ጉርጓድ ማንቆፍረው ማናደርገው የለ ይህ ደግሞ ሰውኛ ማንነታችን አቅም የሌለን ከእኛ የሚበልጥ ፈጣሪ ያለ መሆኑን አንዱ ማሳያችን ብዬ ብል ማንም ሊያብል አይችልም:: ስለዚህ እኔን የፈጠረኝ ጌታ አላህ አለ ልፈራው ያዘዘኝን ጥሩ ስራ ለመስራት ከከለከለኝ ልቆጠብ ። ፈሪሀ አላህ ስሆን ለሰው ልጅ አክብሮት ይኖረኛል አትስረቂ ስለሚለኝ አልሰርቅም አትበድይ ስለሚለኝ አልበድልም ለሰው ልጅ እኩል ፍትሀዊ ሁኚ ስለሚለኝ እሆናለው ።

ይህን ስሆን ህዝቤን የማገለግልበት አቅም ይኖረኛል የሰው ልጅ በሙሉ ለእኔ እኩል ነው በዘር በሀይማኖት ልዩነት እንዳልፈጥር ያዘኛል ይህን ማደርገው እምነት ስላለኝ ነው እምነቴን የምማረው ፀሎቴን የማደርሰው በመስጂዴ ነው መጥፎም ሰርቼ ጥሩም ሰርቼ ወደፈጣሪዬ የምጠጋው በመስጂዴ ነውና የእምነት ቦታዬ ህልውናዬ ነው ለልጆቼ መጥፎ ታሪክ አስቀምጬ አልሄድም በዘመኔ ከአባቴ ይህን አልወረስኩም ።
5.2K views11:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-20 11:30:28 ሸገር ከተማ መስጂዶችንና ሙስሊሞችን የሚያጸዳ ከሆነ፣ ለሙስሊሞች «ፈተና» እንጂ «የኩራት ምንጭ» ፈጽሞ ሊሆን አይችልም!


መንግስት ሀገርን የሚያስተዳድረው በዜጎች ስም ዜጎችን በመወከል መሆኑ ለሁሉም ግልጽ ነው። ይህ ባይሆን ኖሮ የመንግስት ባለስልጣናት የሚባሉት በጠቅላላ እንደኛው ተርታ ዜጋና፣ ከእያንዳንዳችን የተለየ ምንም መብትም ስልጣን ሊኖራቸው አይገባም ነበር።

ሀገር የጋራ መሆኑ ካልተካደ በቀር የሀገር ሀብትና በሀገር ውስጥ ያሉ እድሎች በጠቅላላ የጋራ ናቸው። ይህ ሆኖ ሳለ በመላ ሀገራችን ከተሞች ማስተር ፕላን ሲዘጋጅ ዘወትር ለፕላን አዘጋጆቹ ብቻ ሳይሆን ለፖለቲካ አመራሮቹ ጭምር መስጂድ ብቻ ተለይቶ ትዝ የማይላቸው እስከመቼ ነው?

ሕዝበ ሙስሊሙ እንደዜጋና መስጂዶች በሀገሪቱ በሚዘጋጁ ማስተር ፕላኖች ላይ ሆነ ተብለው እየተረሱ፣ የሙስሊሞች ጥያቄዎች መስጂድና ሂጃብ ብቻ ላይ ታጥረው እንዲቀሩ የማድረግ፣ በውጤቱም ዘወትር የሕዝበ ሙስሊሙ ጥያቄዎች እነዚሁ ብቻ እንዲመስሉ በማድረግ ሃይማኖታዊ እንቅስቃሴዎቹ በአቀበት የተሞላ እንዲሆን የማድረግ ስልት መሆኑ ግልጽ ነው።

እነዚህ መሠረታዊ መብቶች የሆኑ ጉዳዮች፣ ጥያቄዎች ሳይጠየቁም በፊት «በማስተር ፕላኑ መሠረት እዚህ ጋር መስጂድ ያሳያል» እየተባለ ሊመለሱ ይገባቸው የነበሩ፣ አልያም ከተጠየቁም በቀላሉ ሊመለሱ የሚገባቸው ጥያቄዎች ነበሩ። ሆኖም በመላ ሀገሪቱ ሙስሊሞች መስጊድን በልመና፣ ወይም መሬት በገንዘባቸው እየገዙ ለመስገጃነት በማዋል፣ ባስ ሲልም በትግልና በደም [የመስጂድ ይዞታን ለማስከበር በሚደረግ ትግል በጸጥታ አካላት ሙስሊሞች የሚገደሉበት አጋጣሚ በርካታ ነው] የመጎናጸፍ ጉዳይ ካልቆመ በቀር፣ በሀገራችን የሙስሊሞች መብት ተከበረ ማለት አይቻልም።

አንዳንድ ወገኖች መስጂዶች እየፈረሱ ያሉት «ሕገ-ወጥ ስለሆኑ ነው» ይሉናል። ይገርማል! እነኚህንና መሰሎቻቸውን የምንጠይቀው በሀገራችን «ሕጋዊ» የሚባሉት መስጂዶች የትኛቹ እንደሆኑ እንዲነግሩን ነው።

አዲስ አበባን ጨምሮ መስጂዶች ለአስርት ዓመታት ሲሰገድባቸው ቢቆይም፣ ካርታ የሚያገኙት በስንት ጥረትና መንከራተት መሆኑን ሁሉም የሚያውቀው ሀቅ ነው።

ከንጉሠ ዘመን ጀምሮ የኖሩት ታላቁ አንዋር መስጂድና ኑር (በኒን ሰፈር) መስጂድን ጨምሮ ሌሎችም በአዲስ አበባ የሚገኙ ጥንታዊ መስጂዶች ካርታ ያገኙት አቶ አርከበ እቁባይ ከንቲባ በኾኑበት በ1990ዎቹ ነበር። ሆኖም አንዋር መስጂድ የተሠራው በጣሊያን ዘመን ሲሆን፣ ኑር መስጂድ ግን ከጣሊያን ወረራ በፊት ነበር በአባቶቻችን የተገነባው። እነዚህ መስጂዶች በህዝበ ሙስሊሙ ያላሰለሰ ትግል ተሰርተው፣ ለዘመናት እየተሰገደባቸው ቢቆዩም፣ ሕጋዊ ካርታ ያገኙት ግን ከበርካታ አስርት ዓመታት እንግልት በኃላ ነበር።

በበርካታ ከተሞች በሕዝብ ስም ስልጣን ላይ ያሉ አስተዳደሮች በሚያስተዳድሩት ከተማና ዜጎች በሚኖሩበት አከባቢ ማስተር ፕላኑ ሆነ ብሎ መስጂዶች እንዳይኖሩት ማድረጋቸው ሳያሳፍራቸውና ሳያሸማቅቃቸው፣ የአከባቢው ሕዝበ ሙስሊም በነጻ ሊሰጠው ይገባ የነበረውን የመስጂድ ይዞታ ከግለሰቦች ሳንቲም አሰባስቦ ለመግዛት ሲገደድ ነው የኖረው። ሆኖም ይህንንም ይዞታውን ጭምር «ለመስጊድነት አልተፈቀም፣ ሕገ-ወጥ ነው!» ብለው ሲያፈርሱ በተደጋጋሚ ጊዜ ታይቷል።

የሚያሳዝነው ከብዙ ደጅ መጥናትና ዉትወታ በኋላም በሕጋዊ መንገድ ተብሎ ሙስሊሙ ማኅበረሰብ ከሌሎች እጅግ ያነሰ መሬት፣ ማለትም ለአንዱ በካሬ ለሌላው በሔክታር ተለክቶ፣ አድልዎ የተሞላበት አሰራር አሁንም ድረስ መቀጠሉ አሳዛኝ ነው።

ይህንና መሰል እኩይ አድሎ የተሞላበት አካሄድና አሠራር መጅሊስና ሕዝበ ሙስሊሙ በጋራ በሚያደርጉት የአጭር፣ የመካከለኛና የረጅም ጊዜ ትግል ውጪ ሊለወጥ አይችልም።

«ሕገ-ወጥ» ያሉዋቸው መስጂዶች ዛሬ በአንድ ጀምበር ተሰርተው ያደሩ ሳይሆኑ፣ ይልቁንም ሕዝብም መንግስትም እያወቁ ለዓመታት ለአካባቢያቸው ሕዝበ ሙስሊም ግልጋሎት ሲሰጡ የቆዩ ናቸው።

ሌላው ቢቀር በአዲስ መልክና በአዲስ ዕቅድ «ሸገር ከተማ» የሚል አዲስ የከተሞች ግንባታ ስለታቀደ እና በከተማው አዲስ ፕላን መሰረት ስፍራው ለመስጊድ ሳይሆን ለሌላ ጉዳይ ተይዞም ከሆነ፣ ፕላኑን ለመጂድ መገንቢያም ምቹ እንዲሆን ማድረግ እንጂ መስጂዶችን ድንገት ተነስቶ፣ ምንም ምክክር ሳያደርጉ በጅምላ ማፍረስ ፈጽሞ ተገቢ አይደለም።

የሸገር ከተማ አስተዳደር «በአዲሱ ፕላን መሰረት ለመስጂድ የተመደበው ስፍራ ይህ ነው» እያለ ተለዋጭ መሬት እያቀረበ፣ በውይይትና በስምምነት በአዲሱ የከተሞች ግንባታ ውስጥ መስጂድ እንዲሰራ በማድረግ ጉዳዮችን መቋጨት እንኳ አልፈለገም። ከዚያ ይልቅ በተግባር ያደረጉት ለሃይማኖቱና ለሙስሊሞች ቅንጣት ታክል ክብር ሳያሳዩ መስጂዶችን በጅምላ ወደ ማፍረስ ነው የገቡት።

ይህ ሁኔታ ሲታይና በተግባርም በሸገር ከተማ በርካታ መስጂዶችን በጅምላ ለማፍረስ የሚደረገው አሳዛኝ እንቅስቃሴ ሲታይ፣ ጉዳዩ የሕጋዊነት ጥያቄ ሳይሆን ከሸገር ከተማ መስጂድንና ሙስሊሞችን የማጽዳት [አብዛኛው ቤቱ እየፈረሰበት ያለው ሙስሊሙ መሆኑን ከግምት በማስገባት] የአሻጥር እርምጃ አስመስሏል።

ይኼን ማሳካት ፈጽሞውኑ በኢትዮጵያ ምድር ከእንግዲህ የማይታሰብና፣ የሸገር ከተማም መስጂድና ሙስሊሞችን ለማጽዳት ቆርጦ ከቀጠለ፣ ከተማው ለሀገሪቱ ግማሽ ለሆነው ለሙስሊሙ ማኅበረሰብ «ችግር» እንጂ «የኩራት ምንጭ» ፈጽሞ ሊሆን አይችልም!
አህመዲን ጀበል
5.4K views08:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-20 11:22:44
አንዳንድ ወገኖች መስጂዶች እየፈረሱ ያሉት «ሕገ-ወጥ ስለሆኑ ነው» ይሉናል። ይገርማል! እነኚህንና መሰሎቻቸውን የምንጠይቀው በሀገራችን «ሕጋዊ» የሚባሉት መስጂዶች የትኛቹ እንደሆኑ እንዲነግሩን ነው።

በሸገር ከተማ በርካታ መስጂዶችን በጅምላ ለማፍረስ የሚደረገው አሳዛኝ እንቅስቃሴ ሲታይ፣ ጉዳዩ የሕጋዊነት ጥያቄ ሳይሆን ከሸገር ከተማ መስጂድንና ሙስሊሞችን የማጽዳት [አብዛኛው ቤቱ እየፈረሰበት ያለው ሙስሊሙ መሆኑን ከግምት በማስገባት] የአሻጥር እርምጃ አስመስሏል።

ይኼን ማሳካት ፈጽሞውኑ በኢትዮጵያ ምድር ከእንግዲህ የማይታሰብና፣ የሸገር ከተማም መስጂድና ሙስሊሞችን ለማጽዳት ቆርጦ ከቀጠለ፣ ከተማው ለሀገሪቱ ግማሽ ለሆነው ለሙስሊሙ ማኅበረሰብ «ችግር» እንጂ «የኩራት ምንጭ» ፈጽሞ ሊሆን አይችልም!

Ahmedin Jebel
5.1K views08:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-20 11:01:02
ሃሳና እና ሃሲና

ባለፈው አመት በናይጃሪያ ተጣብቀው የተወለዱት መንትዮች በሳውዲ የቀዶ ጥገና ስፔሻሊስቶች ለ14 ሰአት በተደረገ ቀዶ ጥገና በትላንትናው ዕለት በተሳካ ሁኔታ ለመለያየት ተችሏል

በሳውዲ አረቢያ ሙሉ ወጪ የሚሸፈነው በተለያዩ ሀገራት ተጣብቀው የሚወለዱትን የመለያየት ውስብስብ ቀዶ ጥገና እስከ ዛሬ 56 የተጣበቁ መንትዮች ተለያይተውበታል
5.1K views08:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-20 05:41:20
ሰለምቴው ኢቦ ለኢስላም የከፈለው ዋጋ

በንቅሳቴ ምክኒያት አትስደቡኝ እኔ አድስ ሙስሊም ነኝ
ማለቱን ከዚህ በፊት አጋርቻችሁ ነበር

ይሄው ዛሬ ደሞ የሰውነቱን ንቅሳት የማጥፋት ህክምና ጀምሯል። የብዙዎች የሂድያ ሰበብ ሁኗል አላህ ያፅናው
5.7K views02:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-20 05:36:00
ይህ ዓጃይብ ነው

በጆርዳን በአንዱ መንደር ሓብሓብ ያለ ማንም ሻጭ ሰው ለመሸጥ ገበያ ወጥቷል። ዋጋው ለአንዱ ሓብሓብ ሁለት ዲናር ሲሆን ገዢው ያለማንም ሻጭ ገንዘቡን አስቀምጦ ሓብሓቡን አማርጦ ይዞ ይሄዳል።
ከዚህ በላይ መታመንና መተማመን ይኖር ይሆን?!
5.6K views02:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-17 07:55:21
የ450ሺ ብር ጎዳና ተዳዳሪ

ዛሬ የሰማሁትን አስገራሚ ነገር እንደወረደ ነው የማቀርብላችሁ፡፡

ባል እና ሚስት ናቸው ወይም ይመስላሉ፡፡ በቪትስ መኪናቸው እየሔዱ በ10 እና በ11 ዓመት የዕድሜ ክልል ውስጥ ያለን የተጎሳቆለ ጎዳና ተዳዳሪ ያዩና መኪናቸውን አቁመው ይጠሩታል፡፡ ሲጠጋቸውም ሊረዱት እንደፈለጉ ነግረው ያግባቡትና መኪናቸው ውስጥ ያስገቡታል፡፡ ከዚያም በልኩ ምርጥ ምርጥ ልብሶች እና ጫማ ገዝተውለት ፀጉር ቤት በመውሰድ ፀጉሩን ያስተካክላሉ፤ ቤት ከሔዱም በኋላ ገላውን አጥበው ጥሩ ምግብ በመመገብ ያሳድሩታል፡፡

በነጋታው ‹‹ስልክ እንግዛልህ›› ብለው በገዙለት ልብስ እና ጫማ በማዘነነጥ ቦሌ አካባቢ ከሚገኙ ሞባይል ስልክ መሸጫ ቤቶች አንዱ ውስጥ ይወስዱታል፡፡ ልጁን እንደልጃቸው አቅርበው ውድ የሆኑትን ስልኮች እየመረጡ ሳለ፣ ‹‹የስምንት ወር ድርስ እርጉዝ ነኝ›› ባይ ሚስት፣ ‹‹መቆም ስለደከመኝ መኪና ውስጥ ልጠብቃችሁ›› ብላ የመኪናን ቁልፍ በመቀበል ትወጣለች፡፡

ባል ‹‹150ሺ ብር›› የተባሉትን ሦስት የተለያዩ ስልኮች መርጦ፣ ‹‹ባለቤቴ የምትፈልገውን ላማርጣት›› በማለት ልጁን ሞባይል ቤት ትቶ ስልኮቹን በመያዝ ይወጣል፡፡ የሞባይል መሸጫ ቤት ሻጮቹ ዝንጥ ያለ ታዳጊ ‹‹ልጃቸውን›› ትተው የወጡትን ሰዎች የሞባይል ምርጫ ተቀብለው የመረጡትን ሊሸጡላቸው ቢጠብቁም ሳይመጡ ደቂቃዎች አለፉ፡፡ ምን እንደተፈጠረ ለማየት ሲወጡ ሰዎቹ በመኪናቸው እብስ ብለዋል፡፡ መጨረሻውን ባናውቅም ታዳጊውን ይዘው ፖሊስ የጠሩት ተጭበርጫሪዎች ‹‹450ሺ ብራችንን ይውለድ!›› ቢሉም የፈሰሰ ውሀ ሆኖባቸዋል፡፡

መረጃው የጋዜጠኛ እስክንድር መርሃፅድቅ ነው
የቴሌግራም ቻናላችን ከስር በሊንኩ ይቀላቀሉ
https://t.me/+UAKV32q7U2HKzEMf
915 viewsedited  04:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ