2023-05-15 22:59:36
የሆነ ሰውዬ ነው፡፡
አብዛኛውን ጊዜ ቁሽሽ ያለ ልብስ ነው የሚለብሰው፡፡
ኑር መስጊድ አካባቢ ሕይወቱን "በጎዳና ተዳዳሪነት" ነው የሚመራው፡፡
እርሱ እንደሚለው የመጣው ከአርሲ ነው፡፡
ከአፋን ኦሮሞ በቀር የሚችለው ቋንቋ የለም፡፡
አልፎ አልፎ መሰጊድ ይመጣል፡፡
ከድህነት ወለል በታች የሚኖር ሚስኪን ነው፡፡
ሰውየው ከረመዷን አጋማሽ በኀላ ድንገት ተሰወረ፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ከቀናት በኀላ መስጊድ መጥቶ አገኘሁት፡፡
..የት ጠፍቶ እንደነበር..
በአስተርጓሚ በኩል ሳነጋግረው እንደዚህ አለኝ፦
"ልክ ረመዷን መጨረሻ አካባቢ እኔን የመሳሰሉ በርካታ የጎዳና ተዳዳሪዎችን ፖሊሶች አፍሰው ወሰዱን፡፡ የት እነደሆነ የማላውቀው ራቅ ያለ ቦታ አምስት መቶ የምንሆን ሰዎችን ለሃያ አምስት ቀናት ያክል የሆነ ትልቅ ጊቢ ውስጥ አቆዩን፡፡
ምንም የተጠየቅነው ነገር የለም፡፡
ፍርድ ቤትም አልቀረብንም፡፡
ምግብ የምናገኘው በቀኑ ክፍለ ጊዜ አንዴ ብቻ ስለነበር ረመዷንን ሳልጾም አሳለፍኩ፡፡
ቦታው ለመጾም አመቺ አልነበረም፡፡
ከሃያ አምስት ቀናት በኀላ አንድ ቲሸርትና ሸሚዝ አልብሰው ‘ውጡ’ አሉን፡፡"
ከረመዷን አጋማሽ በኀላ ድንገት ተሰውሮ የነበረው ሚስኪኑ ሰውዬ፣ ከቀናት በኀላ መስጊድ መጥቶ አገኘሁትና ይኼንኑ አጫወተኝ፡፡
...በአርሲ ኦሮምኛ፡፡
አቡበከር አለሙ
6.6K views19:59