Get Mystery Box with random crypto!

ሸገር ሲቲን ሙስሊም አልባ ከተማ የማድረጉ ዘመቻ እንደቀጠለ ነው። ማን ያስቁመው???? በሸገር ሲ | "ኡማ ቲቪ " Tv

ሸገር ሲቲን ሙስሊም አልባ ከተማ የማድረጉ ዘመቻ እንደቀጠለ ነው።
ማን ያስቁመው????

በሸገር ሲቲ ዙርያ መስጅድ ፈረሳው ዛሬም እንደቀጠለ ነው።
——————————————————————————
አሰላሙአለይኩም ወረህመቱላሂ ወበረካቱ አሸዋሜዳ ጠቼ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ልዩ ስሙ ኸድጀተል ኩብራ ተብሎ ሚጠራው መስጂድ ሊያፈርሱብን ቀብተውብናል ቶሎ አንሱ ብሎናል እባካቹ ድምፅ ሁኑን
——————————————————————————
ይህ መልእክት ከአካባቢው ነዋሪዎች ዛሬ ግንቦት 3 ደረሰኝ ። ወደተባለው መስጅድ ኮሚቴዎች ደውየ አጣራሁ ኮሚቴዎቹ የደረሰኝ መልእክት እውነት እንደሆነ ከፎቶግራፍ ማስረጃ ጋር አረጋገጡልኝ ።

ዛሬ ግንቦት 3 2015 ከአስር ሰላት በኋላ አፍራሽ ግብረሀይሉ ፈራሽ ቤቶች ላይ ምልክት እያደረጉ መስጅዱ ያለበት ቦታ ላይ ደረሱ ። ሰጋጆቹ እና ኮሚቴዎች መስጅድ ነው ይህን አትንኩ ቢሏቸውም ሃላፊው ግን ንቀት በተሞላበት አነጋገር “አትስሟቸው ሶስት ቦታ ላይ ምልክት አድርጉ “ብሎ ማዘዙን ኮሚቴዎች ነግረውኛል።

መስጅዱ የተመሰረተው ከ10 አመታት በፊት 2005 ሲሆን ከመጅሊሱ እውቅና ያገኘው ደግሞ ከተመሰረተ ከአምስት አመት በኋላ በ2010 ነው ።

ከ10 አመታት በላይ የተሰገደበት ይህ መስጅድ በአካባቢው የሚገኙ ህፃናት ቁርአን እና ኪታቦችን የሚማሩበት እንደሆነ ነዋሪዎች ነግረውኛል።

መጅሊሳችን ሆይ የፃፋችሁት ደብዳቤ ምን ላይ ደረሰ ???
የመስጅዶችን ፈረሳ ለማስቆም ምነው አቅም አጣችሁ???
በመስጅዶች ፈረሳ ዙርያ ዝመታችሁ አልበዛምን???

ሸር በማድረግ መስጅዱን ከመፍረስ እንታደግ
መስጅዶች ጉዳያችን ናቸው