Get Mystery Box with random crypto!

የሀጅ ተጎዦችን ወደ ሐገር ቤት የመመለሻ መርሐ ግብር ሐምሌ 18/2015 እንደሚጠናቀቅ ተገለፀ። | "ኡማ ቲቪ " Tv

የሀጅ ተጎዦችን ወደ ሐገር ቤት የመመለሻ መርሐ ግብር ሐምሌ 18/2015 እንደሚጠናቀቅ ተገለፀ።

ሰኔ 28/15 ዓ.ል የተጀመረው 1444 ኛውን የአሏህ እንግዶችን ወደ ሐገር ቤት የመመለሻ መርሐ ግብር የፊታችን ማክሰኞ ሐምሌ 18/15(ጁላይ 25) እንደሚጠናቀቅ በጠቅላይ ምክር ቤቱ የሐጅና ዑምራ ዘርፍ ተጠባባቂ ምክትል ስራ አስኪያጅ ሼይኽ ኢስሐቅ አደም ገለፁ።

ይህ ዜና እስከ ተጠናቀቀበት ጊዜ ድረስ በኢትዮጵያ አየር መንገድ በሰላሳ ስድስት በረራዎች እንዲሁም ሐምሌ 11/15(ጁላይ 18) ወደ ሐገር ቤት ሑጃጁን የመመለሻ መርሐ ግብሩን ያጠናቀቀው የሳዉዲ አየር መንገድ ሰባት በረራዎች በአጠቃላይ በ አርባ ሶስት በረራዎች የሀጅ ተጎዦች ወደ ሐገር ቤት መመለሳቸውን ሼይኽ ኢስሐቅ ገልፀዋል።

በዘንድሮው ሑጃጆችን በመደበኛ ጉዞ ወደ ሐገር ቤት የመመለሻ መርሐ ግብር ማክሰኞ ሐምሌ 18/15 ዓ.ል የሚጠናቀቅ በመሆኑ ወደ ሐገር ቤት ለመመለስ በዝግጅት ላይ ለሚገኙትን ሑጃጆች የቅድመ ጉዞ ስራዎችን እየተሰሩ መሆናቸውን ገልፀዋል።

ጠቅላይ ምክር ቤቱ ከኢትዮጵያና ከሳዉዲ አየር መንገዶች ጋር ባደረገው የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ምክንያት
በሁለቱም አየር መንገዶች በዘንድሮ ወደ ሐገር ቤት የመመለሻ መርሐ ግብር የዘገየ ወይም የተሰረዘ በረራ አለመኖሩን የገለፁት ተጠባባቂ ምክትል ስራ አስኪያጁ በተለይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሑጃጁን ወደ ሐገር ቤት የመመለሻ ጉዞ ውጤታማ እንዲሆን የበኩሉን አስተዋፅዖ በማበርከቱ ምስጋና ይገባዋል ብለዋል።

በተቀመጠው ወደ ሐገር ቤት የመመለሻ ፕሮግራምን ሳይጠቀሙ በረራ ለሚያመልጣቸው ማንኛውም ሑጃጅ ጠቅላይ ምክር ቤቱ ኃላፊነት የማይወስድ መሆኑን ኃላፊው ማሳሰባቸውን ጠቅላይ ምክር ቤቱ በማህበራዊ ትስስር ገፁ አስታውቋል።