Get Mystery Box with random crypto!

ETHIO-MEREJA®

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_mereja — ETHIO-MEREJA®
ርዕሶች ከሰርጥ:
Ethiopia
የሰርጥ አድራሻ: @ethio_mereja
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 130.68K
የሰርጥ መግለጫ

Addisababa, Ethiopia🇪🇹
News & Media Company®
.
USA : Washington
.
.
.
ለጥቆማ እና ማስታወቂያ ለማሰራት
ከታች ያለውን ሊንክ ይጠቀሙ!!
👉 @ethio_merejabot ✔

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 271

2022-06-09 16:52:11
ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በአዲሱ የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼህ መህሙድ በዓለ ሲመት ላይ!!
T.me/ethio_mereja
@ethio_mereja
11.8K viewsedited  13:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-09 16:44:26
በሽብርተኛው ሸኔ ጉዳት ደርሶበት የነበረው የመልካ ጉባ ድልድይ ተገንብቶ ተጠናቀቀ

በሽብርተኛው የሸኔ ታጣቂ ኃይል ጉዳት ደርሶበት የነበረው የመልካ ጉባ ድልድይ መገንባት ዘርፈ ብዙ ወታደራዊ ጠቀሜታዎች እንዳሉት በቦታው የሚገኙ የፀጥታ ተቋማት አመራሮች ተናገረዋል። ሰራዊቱ በዳዋ ወንዝ ሙላት ምክንያት ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሶ ግዳጅ ለመፈፀም የነበረውን ተግዳሮት መፍታት ተችሏል።

በደቡብ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ ብርጌድ አዛዥ ኮሎኔል ብርሃነ ልጃለም እንዳሉት ከዚህ ቀደም የሸኔን ታጣቂ ሃይል ለመደምሰስ በተደረገው ዘመቻ የዳዋ ወንዝ ለተልዕኮ ችግር እንደነበር ጠቁመው የድልድዮ ዳግም መገንባት በሁሉም ቀጠናዎች ተንቀሳቅሶ ለድል የሚበቃ ሰራዊት የመገንባት አንድ አካል ተደርጎ ይወሰዳል ብለዋል። በዕዙ የሬጅመንት አዛዥ ሻለቃ ገበረ ጋሞ በበኩላቸው ግንባታው የሰራዊቱን ድካም በመቀነስ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተልዕኮን በብቃት የመወጣት ስራ የሚያቀላጥፍ ከመሆኑ ባሻገር የሶማሌና የኦሮሚያ ክልል ህዝቦችን ትስስር የበለጠ የሚያጠናክር እንደሆነ ተናግረዋል።

ለአመታት አስቸጋሪ የመሬት ገፆችን እንደምሽግ በመጠቀም የሽብር ስራውን ሲያከናውን የቆየውን የሸኔ ቡድን ለመደምሰስ ቅንጅታዊ ስራ ተግባራዊ መደረጉ ለተገኘው ድል ወሳኝ ሚና እንዳለው የገለፁት፣ በኦሮሚያ ልዩ ሃይል የሬጅመንት አዛዥ ኢንስፔክተር ጅብሪል አደም በዘመቻው ወቅት ፈተና የነበረው የዳዋ ወንዝ ሙላት አሁን ላይ በተረጋገጠው ሰላም የድልድይ ግንባታ ተሰርቶለት መላው የፀጥታ ሃይል ለቀጣይ ተልዕኮ ዝግጁ መደረጉን አስረድተዋል።

በኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን የተገነባው የብረት ድልድይ የሶማሌ ክልል ዳዋ ዞንን እንዲሁም የኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ጉጅና ቦረና ዞኖችን የሚያዋስን መሆኑን ከሀገር መከላከያ ሠራዊት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
@ethio_mereja
12.2K viewsedited  13:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-08 23:17:58
#ጤናመረጃ

የእንቁላል 7 አስገራሚ የጤና በረከቶች!

እንቁላል በርካታ የጤና ጥቅሞች ያሉት ሲሆን የሚከተሉት ጥቂቶቹ ናቸው፡፡

1. ለአእምሮ ጤንነት አስፈላጊ ነው!
እንቁላል ክሎሪንን ለአእምሮ በመመገብ ጤንነቱን ይጠብቃል፡፡ ክሎሪን መልዕክት አስተላላፊ በመሆን ያገለግላል፡፡ አስኳል ውስጥ የሚገኝው ፎሌት ንጥረ ነገር የነርቭ ሴሎችን በመጠበቅ አእምሮ ተግባሩን በትክክል እንዲወጣ ያደርገዋል፡፡

2. ለጡት ካንሰር የመጋለጥ እድልን ይቀንሳል!
እንቁላል የሰውነታችንን በሽታ የመከላከል አቅምን በከፍተኛ ደረጃ ይጨምራል፡፡ የተለያዩ ጥናቶች እንደሚያሳዩት በሳምንት ቢያንስ 6እንቁላል መመገብ በጡት ካንሰር የመጋለጥ እድላችንን በ44% ይቀንሳል፡፡

3. ለአይን ጤንነት ይጠቅማል!
2 ካሮቲኖይድ፣ ሉቲይንና ዜክሳንቲን የጠራ እይታ እንዲኖረን እና አይናችን ጤናማ እንዲሆን ይረዱናል፡፡ እንቁላል ተመጋቢ ከሆኑ ከካታራክትና ከፀሃይ ጐጂ ጨረር ከመጋለጥ ይከላከልልዎታል፡፡

4. የፀጉር እና ጥፍር ጤንነትን ለመጠበቅ!
በሰልፈር የበለፀገ አሚኖ አሲድ በእንቁላል ውስጥ ይገኛል፡፡ የጥፍር ጤንነትና ጥራትን ይጨምራል፡፡ ሌሎች እንደ ብረት፣ ዚንክና ሴሊኒየም ለፀጉር ጤንነት የበኩላቸውን ድርሻ ይወጣሉ፡፡

5. የሰውነት ክብደትን ያመጣጥናል!
በፕሮቲን የበለፀገ ስለሆነ የሰውነት ክብደትን ለመጨመር ተመራጭ ነው፡፡እንቁላል ስንጠቀም ከመጠን በላይ እንዳንመገብ አስተዋጽኦ ያደርጋል።

6. አጥንታችን ጠንካራ እንዲሆን ያደርጋል!
እንቁላል ከፍተኛ የቫይታሚን ዲ፣ ፎስፈረስና ካልሲየም መጠን አለው እነዚህ በአንድነት በመሆን የአጥንት ችግርን ይከላከላል፡፡

7. ከድንገተኛ የልብ ህመም፣ የደም መርጋትና ድንገተኛ ከሆነ የጭንቅላት ውስጥ ደም መፍሰስን ይከላከላል፡፡

ጠቃሚ ነውና ለወዳጆ ያካፍሉ! ሼር!
T.me/ethio_mereja
2.7K viewsedited  20:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-08 21:47:53
#News Alert!!

ብሄራዊ የደኅንነት ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው ስብሰባ የአገሪቱን ወቅታዊ የጸጥታ እና የብሄራዊ ደኅንነት ስጋቶች መገምገሙን ማምሻውን ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ምክር ቤቱ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት፣ የትግራዩ ጁንታ፣ የሱማሊያው አልሸባብ፣ በኮንትሮባንድ የተሠማሩ አካላት፣ ሕገወጥ ታጣቂዎች፣ ጽንፈኛ መገናኛ ብዙኀን፣ የፖለቲካ ቡድኖች እና አክራሪ ሐይማኖተኞች እንዲሁም የውጭ ጣልቃ ገብነት በአገሪቱ ላይ የደቀኑትን ስጋት መገምገሙን አብራርቷል።

መንግሥት እነዚህን አገራዊ ስጋቶች በሆደ ሰፊነት መያዙ እንደ ድክመት እንደተቆጠረበት ማረጋገጡን የገለጠው ምክር ቤቱ፣ መንግሥት ከእንግዲህ በመገናኛ ብዙኀን፣ ማኅበረሰብ አንቂነት፣ በሐይማኖት እና በፖለቲካ ድርጅት ሽፋን የሚደረጉ አገር የማፍረስ ሴራዎችን መንግሥት አይታገስም ብሏል። ምክር ቤቱ በዚሁ መግለጫው፣ አልሸባብ ከትግራዩ "ጁንታ" እና ከኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ጋር ለመፍጠር የሞከራቸውን ትስስሮችም የመንግሥት ጸጥታ ኃይሎች በተሳካ ሁኔታ አክሽፈዋል ብሏል።

ምክር ቤቱ ባለፈው ሚያዝያ ወር ባደረገው ግምገማ ያስቀመጣቸው ግቦች ባብዛኛው እንደተሳኩ ማረጋጠን እና የመንግሥት ሕግ የማስከበር ርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል መግለጫው አክሎ ገልጧል። ምክር ቤቱ በዚሁ መግለጫው፣ በተለይ በኦሮሚያ፣ ቤንሻንጉል ጉሙዝ እና አማራ ክልሎች በርካታ ሕገወጥ ቡድኖች እና ታጣቂዎች በቁጥጥር ስር እንደዋሉ፣ ሕገወጥ የጦር መሳሪያዎች እንደተሰበሰቡ እና በሕገወጥ እንቅስቃሴ የተገኙ የማኅበረሰብ አንቂዎች ሥርዓት እንዲይዙ መደረጉንም አብራርቷል።

በተጨማሪ ም/ቤቱ በሚዲያ፣ በአክቲቪስትነት፣ በፖለቲካ ቡድን እና በብሔር ስም የሚደረግ ሀገር የማፍረስ ሤራን መንግሥት በምንም መልኩ እንደማይታገሥ አስታውቋል።
T.me/ethio_mereja
6.8K viewsedited  18:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-08 21:19:33
በኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የተመራ የልዑካን ቡድን ቱርክ ገባ

በኢፌዲሪ መከላከያ ሰራዊት ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የተመራ የልዑካን ቡድን በዛሬው ዕለት ቱርክ ገብቷል፡፡ ልዑካኑ የቱርክ መንግስት ባዘጋጀው ኢ ኤፍ ኢ ኤስ 2022 በተሰኘው ወታደራዊ ልምምድ ላይ ለመሳተፍ ነው ቱርክ የገቡት፡፡

ከዝግጅቱ ጎን ለጎን ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ከቱርክ አቻቸው ጄነራል ያሳር ጉለር ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ዙሪያ መምከራቸውን በቱርክ ከኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ በአቅም ግንባታና ወታደራዊ ድጋፎች ላይ በትብብር ለመስራት ስምምነት ላይ መድረሳቸውም ተመላክቷል፡፡
T.me/ethio_mereja
@ethio_mereja
8.1K viewsedited  18:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-08 21:19:05
የስራ ማግኛ ኦንላይን ፕላትፎርም /ሊንኮችህ/ ዝርዝር ለማግኘት

Join our telegram

https://t.me/+P7ctetopPExiY2Rk
7.8K views18:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-08 18:15:33
የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ጃዋር መሀመድ የድርጅቱን ህጋዊ ባንዲራ ያለአግባብ እንዳይጠቀም አሳሰበ!

የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) አመራር የሆነው አቶ ጃዋር መሀመድ ህጋዊ ባንዲራዬን ያለአግባብ እየተጠቀመበት ነው ሲል የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ገለፀ።ኦነግ ለኦፌኮ በፃፈው ደብዳቤ እንዳስታወቀው “በህግ እና በምርጫ ቦርድ የተመዘገበውን የኦነግ ባንዲራ አቶ ጃዋር መሀመድ ከህግና ስርዓት ውጪ እየተጠቀመው ስለሆነ እንድታስቆሙልን እንጠይቃለን” ብሏል።

በፓርቲዎቹ መካከል ያለውን ትብብር እንዲሁም የሀገሪቱን ህግ በማክበር ይህ ድርጊት ይቆማል ብለን ጠብቀን ነበር ያለው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ድርጊቱ በመቀጠሉ ይህን ደብዳቤ ለመፃፍ ተገደናል ሲል አስታውቋል።

በመሆኑም ይህ ደብዳቤ ለኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ከደረሰበት ቀን ጀምሮ አቶ ጃዋር መሀመድ የኦነግን ባንዲራ በተለያዩ መድረኮች ላይ እንዳይጠቀም እንድታሳስቡት እንጠይቃለን ብሏል። [አዲስ-ዘይቤ]
T.me/ethio_mereja
@ethio_mereja
13.5K viewsedited  15:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-08 16:32:30
በጋዜጠኞች ዋስትና ላይ የተሰማው የዓቃቤ ሕግ ይግባኝ ዛሬም ውሳኔ አላገኘም!!

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት «ኹከት እና ብጥብጥ በማነሳሳት» ወንጀል ተጠርጥረው በእስር ላይ በሚገኙት ጋዜጠኞች ተመስገን ደሳለኝ፣መዓዛ መሐመድ እና በሰለሞን ሹምዪ ላይ አቃቤ ሕግ ባቀረበበቸው የዋስትና ይግባኝ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ዛሬ እሮብ ሰኔ አንድ ቀን 2014 ዓም በዋለው ችሎት ለነገ ቀጥሮ ሰጥቶዋል።

ሶስቱ ጋዜጠኞች እያንዳንዳቸው በ1ዐሥር ሺህ ብር ዋስትና እንዲወጡ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ትላንት ማክሰኞ ግንቦት 30/2014 ረፋዱ ላይ ውሳኔ ማስተላለፉ ይታወሳል። ይህን ተከትሎ በእለቱ ውሳኔው ይቀልበስልኝ ሲል አቃቢ ሕግ ያቀረበውን ተቃውሞ የሚሰማ ዳኛ የለም ተብሎ ጋዜጠኞቱ ሳይፈቱ ይግባኙም ሰይደመጥ ለዛሬ መተላለፉ ይታወሳል።

ዛሬ በአቃቤ ሕግ የሥር ፍርድ ቤት የዋስትና ውሳኔ መቃወሚያ ይግባኝ በፁሁፍ የቀረበለት ችሎቱ የተከሳሽ ጠበቆችን ምላሽ በቃል ካደመጠ በኋላ ጉዳዪን ከሁለቱም ወገን ሰምቶ ውሳኔ ለመስጠት ለነገ ሀሙስ ሰኔ 2 ቀን 2014 ዓም ተለዋጭ ቀጥሮ ሰጥቷል።

ጋዜጠኞቹ እያንዳንዳቸው የ10 ሺህ ብር ዋስትና በማስያዝ ከእስር እንዲለቀቁ ግንቦት 30 ቀን ትዕዛዝ ሰጥቶ የነበረ ቢሆንም ጋዜጠኞቹ ግን እስካሁን በእስር ላይ መሆናቸውን ተዘግቧል።
T.me/ethio_mereja
@ethio_mereja
14.2K viewsedited  13:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-08 14:29:34
የኢትዮ ቴሌኮም መልእክት!!

"ውድ ደንበኞቻችን

በመደበኛው ኤሌክትሪክ ሀይል (Commercial Power) መቋረጥ ምክንያት በጅማ፣ መቱ እና አከባቢው፣ በደቡብ (በሆሳዕና፣አርባ ምንጭ፣ሶዶ እና ሳውላ)፣ በምዕራብ ወሎ አከባቢ፣ በነቀምት እና አካባቢው፣ አሶሳና አከባቢው፣ በደቡብ ጎንደር እንዲሁም በአዲስ አበባ (በኮተቤ፣ጉርድሾላ፣ጣፎ፣ቅሊንጦ እና ቱሉዲምቱ) በመጠባበቂያ ሀይል አገልግሎታችንን ለማስቀጠል እየሞከርን ሲሆን በተወሰኑት አካባቢዎችም በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የአገልግሎት መቋረጥ ሊያጋጥም ይችላል። በመሆኑም ችግሩን ለመፍታት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ በመሆናችን በትዕግስት እንድትጠብቁን በትህትና እንጠይቃለን።"

T.me/ethio_mereja
@ethio_mereja
14.9K viewsedited  11:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-08 12:46:52
ለ156 ሰዎች የሙት አመት የሚዘክሩት እናት !

እማማ ሙሉነሽ በደብረዘይት የተከሰከሰዉ #አዉሮፕላን ከተከሰተ ከሰባተኛዉ ቀን ጀምረዉ እስካሁን ድረስ አይተዋቸዉ በአካል አግኝተዋቸዉ እንኳን የማያዉቋቸዉን የተለያዩ ሃገራት ዜግነት ያላቸዉን በተከሰከሰው አዉሮፕላን ህይወታቸዉን ላጡ 156 ሰዎች የሙት አመት ፍትሃት እያስፈቱ የሚገኙ አስገራሚ ባለ ቃልኪዳን እናት ናቸዉ !!

እማማ ሙሉነሽ ከአዲስአበባ ወደ ናይሮቢ በበረራ ላይ የነበረው max 8 -737 አዉሮፕላን ደብረዘይት ላይ ተከስክሶ 156 ሰዎች ህይወት ሲቀጥፍ እማማ ሙሉነሽ ግብር ለመክፈል በእግራቸው ሲጓዙ አዉሮፕላኑ እየጨሰ ቁልቁል ተምዘግዝጎ ሲወድቅ በደመነብስ እየሮጡ በጭሱ መሃል ገብተዉ የተረፈ ካለ ብለዉ ፈለጉ አላገኙም፣ በየቦታው የወደቀዉን የሰዉ አካላት በነጠላቸዉ በሻሻቸዉ ለመሸፈን ሞከሩ፣ አነቡ፣ አዘኑ፣ አለቀሱ።

እኒህ እናት ከዛን ጊዜ ጀምረዉ የሟቾቹን ሰባት፣ አስራሁለት፣ አርባ፣ ሙት አመት እየዘከሩ ፍታት እያስፈቱ ፀሎት እያስደረጉ አመታት ዘልቀዋል።እማማ ሲጠየቁ በህይወት እስካሉ ድረስ ይህንን አላቆምም፣ በየአመቱ ሙት አመታቸዉን እዘክራለሁ ብለዋል።

እማማ በዚህ በዘር በጎሳ በመንደር በምናስብበት ዘመን ሰዉ መሆንን ያሳዩ እናታችም እረጅም እድሜ ተመኘን በመኖርያ ቤታቸዉ በመሄድ ያከበራችኋቸዉ ጋዜጠኞች ምስጋና ይገባችኋል።
T.me/ethio_mereja
@ethio_mereja
15.2K viewsedited  09:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ