Get Mystery Box with random crypto!

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ጃዋር መሀመድ የድርጅቱን ህጋዊ ባንዲራ ያለአግባብ እንዳይጠቀም አሳሰበ! | ETHIO-MEREJA®

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ጃዋር መሀመድ የድርጅቱን ህጋዊ ባንዲራ ያለአግባብ እንዳይጠቀም አሳሰበ!

የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) አመራር የሆነው አቶ ጃዋር መሀመድ ህጋዊ ባንዲራዬን ያለአግባብ እየተጠቀመበት ነው ሲል የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ገለፀ።ኦነግ ለኦፌኮ በፃፈው ደብዳቤ እንዳስታወቀው “በህግ እና በምርጫ ቦርድ የተመዘገበውን የኦነግ ባንዲራ አቶ ጃዋር መሀመድ ከህግና ስርዓት ውጪ እየተጠቀመው ስለሆነ እንድታስቆሙልን እንጠይቃለን” ብሏል።

በፓርቲዎቹ መካከል ያለውን ትብብር እንዲሁም የሀገሪቱን ህግ በማክበር ይህ ድርጊት ይቆማል ብለን ጠብቀን ነበር ያለው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ድርጊቱ በመቀጠሉ ይህን ደብዳቤ ለመፃፍ ተገደናል ሲል አስታውቋል።

በመሆኑም ይህ ደብዳቤ ለኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ከደረሰበት ቀን ጀምሮ አቶ ጃዋር መሀመድ የኦነግን ባንዲራ በተለያዩ መድረኮች ላይ እንዳይጠቀም እንድታሳስቡት እንጠይቃለን ብሏል። [አዲስ-ዘይቤ]
T.me/ethio_mereja
@ethio_mereja