Get Mystery Box with random crypto!

በጋዜጠኞች ዋስትና ላይ የተሰማው የዓቃቤ ሕግ ይግባኝ ዛሬም ውሳኔ አላገኘም!! የፌደራል የመጀመሪ | ETHIO-MEREJA®

በጋዜጠኞች ዋስትና ላይ የተሰማው የዓቃቤ ሕግ ይግባኝ ዛሬም ውሳኔ አላገኘም!!

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት «ኹከት እና ብጥብጥ በማነሳሳት» ወንጀል ተጠርጥረው በእስር ላይ በሚገኙት ጋዜጠኞች ተመስገን ደሳለኝ፣መዓዛ መሐመድ እና በሰለሞን ሹምዪ ላይ አቃቤ ሕግ ባቀረበበቸው የዋስትና ይግባኝ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ዛሬ እሮብ ሰኔ አንድ ቀን 2014 ዓም በዋለው ችሎት ለነገ ቀጥሮ ሰጥቶዋል።

ሶስቱ ጋዜጠኞች እያንዳንዳቸው በ1ዐሥር ሺህ ብር ዋስትና እንዲወጡ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ትላንት ማክሰኞ ግንቦት 30/2014 ረፋዱ ላይ ውሳኔ ማስተላለፉ ይታወሳል። ይህን ተከትሎ በእለቱ ውሳኔው ይቀልበስልኝ ሲል አቃቢ ሕግ ያቀረበውን ተቃውሞ የሚሰማ ዳኛ የለም ተብሎ ጋዜጠኞቱ ሳይፈቱ ይግባኙም ሰይደመጥ ለዛሬ መተላለፉ ይታወሳል።

ዛሬ በአቃቤ ሕግ የሥር ፍርድ ቤት የዋስትና ውሳኔ መቃወሚያ ይግባኝ በፁሁፍ የቀረበለት ችሎቱ የተከሳሽ ጠበቆችን ምላሽ በቃል ካደመጠ በኋላ ጉዳዪን ከሁለቱም ወገን ሰምቶ ውሳኔ ለመስጠት ለነገ ሀሙስ ሰኔ 2 ቀን 2014 ዓም ተለዋጭ ቀጥሮ ሰጥቷል።

ጋዜጠኞቹ እያንዳንዳቸው የ10 ሺህ ብር ዋስትና በማስያዝ ከእስር እንዲለቀቁ ግንቦት 30 ቀን ትዕዛዝ ሰጥቶ የነበረ ቢሆንም ጋዜጠኞቹ ግን እስካሁን በእስር ላይ መሆናቸውን ተዘግቧል።
T.me/ethio_mereja
@ethio_mereja