Get Mystery Box with random crypto!

ETHIO-MEREJA®

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_mereja — ETHIO-MEREJA®
ርዕሶች ከሰርጥ:
Ethiopia
የሰርጥ አድራሻ: @ethio_mereja
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 130.68K
የሰርጥ መግለጫ

Addisababa, Ethiopia🇪🇹
News & Media Company®
.
USA : Washington
.
.
.
ለጥቆማ እና ማስታወቂያ ለማሰራት
ከታች ያለውን ሊንክ ይጠቀሙ!!
👉 @ethio_merejabot ✔

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 270

2022-06-10 12:15:47
ኢትዮጵያ የሶማሌላንድ መንግስት በበርበራ ወደብ ላይ የባለቤትነት መብትን አስመልክቶ ያስቀመጠውን ቅድመ ሁኔታ ማሟላት ባለመቻሏ በበርበራ ወደብ ላይ ያላትን የ19 በመቶ ድርሻዋን አጣች።

የሶማሌላንድ ገንዘብ ሚኒስቴር እንደገለጸው የኢትዮጵያ መንግስት ማሟላት የነበረበትን የባለቤትነት መስፈርቶች በጊዜው ባለሟሟላቱ ባለቤትነቱን ተነጥቋል። ሚኒስትሩ እንዳመለከቱት ከቅድመ-ሁኔታዎች አንዱ ለወደቡ ግንባታ የገንዘብ መዋጮ ሲሆን ኢትዮጵያ ይህን ማድረግ ሳትችል ቀርታለች ተብሏል።

በሌላ በኩል ሳምንታዊ መግለጫ የሰጡት አምባሳደር ዲና ሙፍቲ እንዳሉት የበርበራ ወደብን በተመለከተ መንግስት መረጃን እያጣራ ይገኛል ብለዋል፡፡ (ካፒታል)
T.me/ethio_mereja
@ethio_mereja
14.3K viewsedited  09:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-10 12:04:28
ቴሌግራም https://telegram.me/onlineshoppingce
አድራሻችን:- ቦሌ መድሐኔዓለም ቦሌ መሰናዶ ት/ቤት ፊትለፊት አለምነሽ ፕላዛ ሱቅ ቁጥር 05

+251941661030 / +251943190237
14.3K views09:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-10 12:01:46
የስራ ማግኛ ኦንላይን ፕላትፎርም /ሊንኮችህ/ ዝርዝር ለማግኘት

Join our telegram

https://t.me/+P7ctetopPExiY2Rk
14.5K views09:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-09 22:23:29
"2ሚሊዮን ብር ሽልማት"

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ግብፅ ላይ ያስመዘገበውን ጣፋጭ ድል ተከትሎ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ ጂራ ባስተላለፉት መልዕክት " ይህ ከእግር ኳስ በላይ ብዙ ትርጉም ያለውን ጨዋታ በድል በማጠናቀቃችሁ ኩራት ተሰምቶናል። ...ከስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ጋር በአስቸኳይ ተነጋግረን ለዛሬው ድል እና ባለፈው ጨዋታ ላደረጋችሁት ሁሉ 2 ሚልየን ብር ሽልማት ለቡድኑ አባላት እናበረክታለን " ብለዋል ።

Via Ethiopian Football Federation
T.me/ethio_mereja
@ethio_mereja
6.0K viewsedited  19:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-09 20:57:22
ጨዋታው በኢትዮጵያ አሸናፊነት ተጠናቀቀ

ኢትዮጵያ ግብጽን በአስደማሚ ሁኔታ 2 ለ0 አሸንፋለች!!

ለአፍሪቃ ዋንጫ ማጣሪያ ሁለተኛ የምድብ ግጥሚያውን ሐሙስ፤ ሰኔ 2 ቀን፣ 2014 ዓም ማላዊ ቢንጉ ብሔራዊ ስታዲየም ውስጥ ያካኼደው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የግብጽ አቻውን 2 ለ0 አሸንፏል።

ለኢትዮጵያ የመጀመሪያውን ግብ በ21ኛው ደቂቃ ላይ ያስቆጠረው ዳዋ ሆቴሳ ነው። ሁለተኛውን ግብ ደግሞ በ40ኛው ደቂቃ ላይ ከመረብ ያሳረፈው ሽመልስ በቀለ ነው። ሁለቱም ግቦች የኢትዮጵያ አጥቂዎች ድንቅ ብቃት የታየበት ነው።

ኢትዮጵያ በአንደኛ ደረጃ የምድቡ መሪ ሆናለች።

እንኳን ደስ አላችሁ፣ አለን
T.me/ethio_mereja
@ethio_mereja
11.1K viewsedited  17:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-09 20:52:32 በዛሬው ጨዋታ ዋሊያዎቹ አስደናቂ እንቅስቃሴን እያሳዩ ይገኛሉ። ኢትዮጵያ ግብጽን 2 ለ0 እየመራች ነው!! --ጨዋታው 90" ደቂቃ ላይ ደርሷል።-- ለብሔራዊ ቡድናችን መልካም እድል እንላለን። T.me/ethio_mereja @ethio_mereja
10.3K viewsedited  17:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-09 20:47:14 በዛሬው ጨዋታ ዋሊያዎቹ አስደናቂ እንቅስቃሴን እያሳዩ ይገኛሉ።

ኢትዮጵያ ግብጽን 2 ለ0 እየመራች ነው!!

--ጨዋታው 90" ደቂቃ ላይ ደርሷል።--

ለብሔራዊ ቡድናችን መልካም እድል እንላለን።
T.me/ethio_mereja
@ethio_mereja
10.5K viewsedited  17:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-09 20:16:30
ኢትዮጵያ ግብጽን በአስደማሚ ሁኔታ 2 ለ0 እየመራች ነው!!

ለአፍሪቃ ዋንጫ ማጣሪያ ሁለተኛ የምድብ ግጥሚያውን ሐሙስ፤ ሰኔ 2 ቀን፣ 2014 ዓም ማላዊ ቢንጉ ብሔራዊ ስታዲየም ውስጥ እያካኼደ ያለው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የግብጽ አቻውን 2 ለ0 እየመራ ነው።

ለኢትዮጵያ የመጀመሪያውን ግብ በ21ኛው ደቂቃ ላይ ያስቆጠረው ዳዋ ሆቴሳ ነው። ሁለተኛውን ግብ ደግሞ በ40ኛው ደቂቃ ላይ ከመረብ ያሳረፈው ሽመልስ በቀለ ነው። ሁለቱም ግቦች የኢትዮጵያ አጥቂዎች ድንቅ ብቃት የታየበት ነው።

--ጨዋታው 74" ደቂቃ ላይ ደርሷል።--

ለብሔራዊ ቡድናችን መልካም እድል እንላለን።


T.me/ethio_mereja
@ethio_mereja
11.7K viewsedited  17:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-09 18:55:29
ዛሬ ምሽት 1 ሰአት ላይ ዋሊያዎቹ የግብፅ ብሄራዊ ቡድንን ይገጥማሉ!

በአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ የዋሊያዎቹ የመጀመሪያ አሰላለፍ ይፋ ሆኗል።ከደቂቃዎች በኋላ ከግብፅ ብሔራዊ ቡድን ጋር የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ ሁለተኛ ጨዋታውን የሚያደርገው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የመጀመሪያ የተጫዋቾች አሰላለፍ ይፋ ሆኗል።

በዚህም መሠረት ፦

ግብ ጠባቂ
ፋሲል ገብረሚካኤል

ተከላካዮች
አስራት ቱንጆ፣ ያሬድ ባየህ፣ ምኞት ደበበ፣ ረመዳን የሱፍ

አማካዮች
ጋቶች ፓኖም፣ አማኑኤል ዮሐንስ፣ ሽመልስ በቀለ

አጥቂዎች
ዳዋ ሁቴሳ፣ አቡበከር ናስር፣ አማኑኤል ገብረሚካኤል
T.me/ethio_mereja
@ethio_mereja
12.5K viewsedited  15:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-09 17:05:08
ሹመት!!
ለትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን አዲስ የስራ አመራር የቦርድ አባላት ተሾሙ!

ለትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን አዲስ የስራ አመራር የቦርድ አባላት በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ተሹመዋል። ባለስልጣኑ ለኢፕድ በለከው መግለጫ ሰኔ 1 ቀን 2014 ዓ.ም ከጠቅላይ ሚኒስቴር ፅህፈት ቤት በተላከ ደብዳቤ አዲስ የስራ አመራር የቦርድ አባላት እንደተመደበለት አስታውቋል።

ለባለስልጣኑ አዲስ የስራ አመራር የቦርድ አባላት ሆነው የተሾሙት፤
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል ‥.....ሰብሳቢ
የሴቶችና ማሕበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ....... አባል
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር በለጠ ሞላ .......አባል
የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ተስፋዬ ዳባ ...... አባል
የኢንፎርሜሽ መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሹመቴ ግዛው..... አባል
የነዳጅና ኢነርጂ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሳህረላ አብዱላሂ ........አባል
የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተዶክተር አንዱዓለም አድማሴ አባልና ጸሀፊ ሆነው ተሸመዋል።
T.me/ethio_mereja
@ethio_mereja
13.5K viewsedited  14:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ