Get Mystery Box with random crypto!

ሹመት!! ለትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን አዲስ የስራ አመራር የቦርድ አባላት ተሾሙ! ለትምህርትና | ETHIO-MEREJA®

ሹመት!!
ለትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን አዲስ የስራ አመራር የቦርድ አባላት ተሾሙ!

ለትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን አዲስ የስራ አመራር የቦርድ አባላት በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ተሹመዋል። ባለስልጣኑ ለኢፕድ በለከው መግለጫ ሰኔ 1 ቀን 2014 ዓ.ም ከጠቅላይ ሚኒስቴር ፅህፈት ቤት በተላከ ደብዳቤ አዲስ የስራ አመራር የቦርድ አባላት እንደተመደበለት አስታውቋል።

ለባለስልጣኑ አዲስ የስራ አመራር የቦርድ አባላት ሆነው የተሾሙት፤
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል ‥.....ሰብሳቢ
የሴቶችና ማሕበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ....... አባል
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር በለጠ ሞላ .......አባል
የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ተስፋዬ ዳባ ...... አባል
የኢንፎርሜሽ መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሹመቴ ግዛው..... አባል
የነዳጅና ኢነርጂ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሳህረላ አብዱላሂ ........አባል
የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተዶክተር አንዱዓለም አድማሴ አባልና ጸሀፊ ሆነው ተሸመዋል።
T.me/ethio_mereja
@ethio_mereja