Get Mystery Box with random crypto!

ETHIO-MEREJA®

የሰርጥ አድራሻ: @ethio_mereja
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 130.68K
የሰርጥ መግለጫ

Addisababa, Ethiopia🇪🇹
News & Media Company®
.
USA : Washington
.
.
.
ለጥቆማ እና ማስታወቂያ ለማሰራት
ከታች ያለውን ሊንክ ይጠቀሙ!!
👉 @ethio_merejabot ✔

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 267

2022-06-13 21:12:55
ኢትዮጵያ የበርበራ ወደብ ላይ ያላትን ሼር አላጣችም ሲሉ የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሺዴ ለካፒታል ገለፁ።

ሚንስትሩ እንዳሉት ባለቤትነቱን በተመለከተ ንግግሮች አሁንም እንደቀጠሉ እና ተጨማሪ ስራዎች የሚቀሩ እንዳሉ ገልፀው ባለቤትነቷን አታለች የሚባልበት ደረጃ እንዳልደረሰ ገልጸዋል።

T.me/ethio_mereja
ኢትዮመረጃ
9.4K viewsedited  18:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-13 20:35:50
ደሴ ምንድነው የሆነው?

በደሴ ከተማ አስተዳደር በቧንቧውሀ ክፍለ ከተማ 4ኛ ፓሊስ ጣቢያ በነፍስ መጣፋት ተፈላጊ የነበሩ ግለሰቦች በምርመራ ክፍል ውስጥ በጣሉት ቦንብ የ5 ሰዎች ሂወት አለፈ!!

መነሻቸውን ከደሴ ዙሪያ ወረዳ ፅድ ገበያ አካባቢ ያደረጉ በነፍስ ማጥፋት ወንጀል ሲፈለጉ የነበሩ እና ተፈላጊ ወንጀለኞች የ25 ዓመት ፍርደኛ የነበሩ 4 ሽፍቶች ወደ ደሴ ከተማ አስተዳደር በመግባት የተለያዩ ጥፋቶችን ለመሰንዘር አቅደው የገቡ ቢሆንም እነዚህን ወንጀለኞች በደሴ ከተማ አስተዳደር እና በደቡብ ወሎ ፓሊስ ጥመረት ከቀኑ 10:00 አካባቢ ተይዘው ወደ 4ኛ ፓሊስ ጣቢያ ለምርመራ እንዲገቡ ተደርጓል ።

በዚህ ሂደት ውስጥ በወንጀል ሲፈለጉ የነበሩትን 4 ሽፍቶች የያዛችሁትን ትጥቅ አውርዱ የሚል ከፓሊስ የተሰጣቸውን መመሪያ ባለመቀበል እና መመሪያውን በመተላለፍ የታጠቁትን ቦንብ አውጥተው በማፈንዳት ተፈላጊ ሽፍቶቹን ጨምሮ አንድ መደበኛ ፓሊስ እና ልዩ ሀይል በጥቅሉ የ5 ሰዎች ሂወት የጠፋ ሲሆን 1 ወንጀለኛ እጁን ሰጥቷል በማለት የደሴ ከተማ አስተዳደር ፓሊስ መምሪያ ሀላፊ ኮማንደር አሳምን ሙላት ለደሴ ከተማ አስተዳደር የኮሚኒዩኬሽን መምሪያ አስታውቀዋል።
T.me/ethio_mereja
ኢትዮመረጃ
11.3K viewsedited  17:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-13 19:40:40
ዛሬ በመዲናችን አዲስ አበባ ዓለም አቀፍ የቁርአን ውድድር ተካሂዷል!!

በሀገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ በአዲስ አበባ ስታዲየም የተካሄደው አለምአቀፍ የቁርአን ሒፍዝ እና አዛን ውድድር በታላቅ ድምቀት ተካሂዶ በሰላም ተጠናቋል።

ከ56 ሀገራት በላይ በተሳተፉበት የሀጋራችንን መልካም ገፅታ ግንባታ ታላቅ አስተዋፅዖ የሚያድርገው ይህ ውድድር ባማረ ሁኔት ተካሂዶ ለውድድሩ አሸናፊዎችም ሽልማቶች ተበርክቶላቸዋል::

ዚያድ ፈሪጃ ከሉብናን በአዛን ውድድር 1ኛ ደረጃ በመያዝ አሸናፊ ሆኗል። ሙሀመድ ኑር ከኦርዶን በሂፍዝ ውድድር አንደኛ ደረጃ በመውጣት 10 ሺህ የአሜሪካን ዶላር አሸናፊ መሆኑን ተገልጿል።
T.me/ethio_mereja
ኢትዮመረጃ
12.2K viewsedited  16:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-13 19:18:37
ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ነገ በአገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለሚቀርብላቸው ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ እንደሚሰጡ ምክር ቤቱ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል።

ጠቅላይ ሚንስትሩ ከምክር ቤቱ አባላት ለሚቀርቧላቸው ጥያቄዎች የሚሰጡት ምላሽ እና ማብራሪያ በመንግሥታዊው ቴሌቪዥን በቀጥታ ይተላለፋል ተብሏል።
T.me/ethio_mereja
ኢትዮመረጃ
11.5K viewsedited  16:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-13 19:10:39
አዲሱን ሁሉግራም 4.0 ያውርዱ!

ሁሉግራም 4.0 አፕዴት ሲያወርዱ፤ የአየር ሰዓት በቀላሉ ይሞላሉ፣ የአየር መንገድ ቲኬቶን፣ የዲኤስቲቪ እና የካናል ፕላስ ክፍያዎችን መፈፀም ይችላሉ።

ሁሉም በሁሉግራም ይቻላል!
Download Hulugram SuperApp

https://play.google.com/store/apps/details?id=plus.ride.huluchat
11.8K views16:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-13 14:45:41
ግዙፉ ባለ 60 ወለል ህንፃ - በአዲስ አበባ!

አቢሲኒያ ባንክ በአፍሪካ 2ኛ በምስራቅ አፍሪካ ረጅሙን 270 ሜትር ከፍታና ባለ 60 ወለል ግዙፍ ህንፃ ለማስገንባት ከቻይና ስቴት ኮንስትራክሽን ጋር ተፈራርሞ ወደ ስራ ገብቷል።

አቢሲኒያ ባንክ በመዲናይቱ ፋይናንስ ዲስትሪክት ተብሎ በሚጠራው ሰፈር በ400 ሚሊዮን ዶላር አዲስ ዋና መሥሪያ ቤት ለመገንባት ተፈራርሞ ወደ ስራ ገብቷል። ግንባታው ሜክሲኮ ዋቢሸበሌ አጠገብ በ9ሺ 763 ካ.ሜ ቦታ ላይ ይገነባል። ይህ ህንፃ አሁን ካለው ሰማይ ጠቀሱ የCBE ህንፃ በ61 ሜትር ይበልጣል።

T.me/ethio_mereja
ኢትዮመረጃ
16.1K viewsedited  11:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-13 00:03:47
#Ethiopia | በትግርኛ ዘፈኑ፤አክሱማዊት የተሰኘ ሙሉ አልበም አውጥቷል። ባባ ኢለን፣ ዘዊደሮ፣ ወዛመይ፣ ቸኮላታ፣ ኣጆኺ ትግራይ፣ ደስ ይበለኒ'ሎ፣ ቕዱስ ፀባያ የተሰኙ ሥራዎቹ በሕዝብ ዘንድ የሚታወቁ ነጠላ ዜማዎቹ ናቸው -ይህ ድምፃዊ ዳዊት ነጋ ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል።

አዲስ ህይወት ሆስፒታል ደረስኩ።

የሆስፒታሉ በር፣ ግራ እና ቀኝ ቤተሰቦቹ ፣ ወዳጆቹና አድናቂዎቹ ተሰብሰበው ያለቅሳሉ።

ለቅሷቸው በጣም ይረብሻል፣ ያስለቅሳል።

ግቢው ድንጋጤ ባረበበባቸው ሰዎች ተጨናንቋል።

አርቲስት ዳዊት ነጋ #Dawit Nega ህመም አጋጥሞት ያለፉትን ቀናት በአዲስ ህይወት ሆስፒታል በበጽኑ ሕክምና ላይ ነበር።

አርቲስት ዳዊት ነጋ (ሰላምተኛዬ) የሙዚቃ ሥራዎቹ የትግርኛ ቋንቋ ከሚያደምጡ ሰዎች ባለፈ ቋንቋውን በማያቁትም ዘንድ እጅግ ተወዳጅ የነበሩ ናቸው። ሙዚቃ የዓለም ቋንቋ ነው የሚባለውም ለዚህም ነው።

ከሙዚቃ ሥራዎቹ መካከል ፦ ባባ ኢለን፣ ዘዊደሮ፣ ወዛመይ፣ ቸኮላታ፣ ኣጆኺ ትግራይ፣ ደስ ይበለኒ'ሎ፣ ቕዱስ ፀባያ የሚባሉት ይጠቀሳሉ።

አርቲስት ዳዊት ነጋ ባለትዳር እና የአንድ ልጅ አባት ነበር።

ለወዳጅ ዘመዶቹና የቅርብ ቤተሰቦቹ ልዑል እግዚአብሔር መጽናናትን ይስጥልን። እንወድሃለን


--ጋዜጠኛ ጌጡ ተመስገን---
T.me/ethio_mereja
2.2K viewsedited  21:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-12 21:50:53
አሳዛኝ ዜና

ድምፃዊ ዳዊት ነጋ በድንገተኛ ህመም ከዚህ አለም በሞት ተለየ

ወዛመይ ፣ ዘዊደሮ እና በሌሎች የትግረኛ ዘፈኖች የሚታወቀው ወጣት ድምፃዊ ዳዊት ነጋ ዛሬ ማረፉ ተሰምቷል።

ድምፃዊ ዳዊት አዲስ አበባ በሚገኘው በአዲስ ሒወት ሆስፒታል ላለፉት አራት ቀን ህክምና ሲከታተል ነበር ሲሉ ከዘፋኙ ጋር ቅርበት ያላቸው ወዳጆች ገልፀዋል። ለወዳጅ ዘመዶቹ እና አድናቂዎቹ መጽናናትን እንመኛለን። ነብስ ይማር

T.me/ethio_mereja
ኢትዮመረጃ
9.2K viewsedited  18:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-12 19:10:47
መከላከያ ሰራዊቱ ከሌሎች የጸጥታ ሀይሎች ጋር በመሆን ፀረ-ህዝብ ኃይሎችን በማጥፋቱ ረገድ ውጤታማ ስራ እየሠራ መሆኑ ተገለጸ!!

በደቡብ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ በኦሮሚያ ከምዕራብ አርሲ፣ ከቦረና፣ ከምዕራብና ምስራቅ ጉጅ፣ ከባሌና ከአርሲ ዞኖች እንዲሁም ከደቡብ እና ከሲዳማ ክልል ዞኖች ከተውጣጡ የፀጥታና የአስተዳደር አካላት ጋር ውይይት ተደርጓል፡፡

በውይይቱ የኮማንዶና አየር ወለድ ኃይል አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ሹማ አብደታ እንደገለፁት የሠላም ዕጦት የዜጎችን ኑሮ የሚያናጋ ከመሆኑም በተጨማሪ ለሀገር ዕድገት ፀር ነው።

የህዝብ ሰላም በተሟላ መልኩ ለማረጋገጥ ሁሉም የፀጥታ እና የአስተዳደር አካላት ከሀገር መከላከያ ሠራዊት ጋር በተጠናከረ መንገድ ተቀናጅቶ በቀጣይነት መስራት እንዳለባቸው መናገራቸውን የመከላከያ ሰራዊት መረጃ ያመላክታል።

የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው የሀገርን ሠላምና የህዝብ ተረጋግቶ የመኖር ዋስትናን የሚፈታተኑ ፅንፈኛ ኃይሎችን ህልውና ለማክሠም እርስ በእርሳቸው በመደጋገፍ ከሠራዊቱ ጋር ተባብሮ ለመስራት ቁርጠኛ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
T.me/ethio_mereja
@ethio_mereja
13.8K viewsedited  16:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-12 16:51:39
ሩሲያ ምእራባውያን ለዩክሬን የለገሱትን መሳሪያ የያዘ መጋዘን አወደመች!!

ሩሲያ በዩክሬን ውስጥ የሚገኝ ግዙፍ ወታደራዊ መጋዘን ማውሟን የሀገሪቱ ጦር አስታውቋል።የሩሲያ ጦር ያወደመው መጋዝን ምእራባውያን ለዩክሬን የሰጡትን በርካታ የጦር መሳሪያው የያዘ መሆኑንም የሩሲያው ኢንትራፋክስ የዜና ኤጀንሲ አስነብቧል።

የሩሲያ ጦር በቴርኖፒል ክልል ውስጥ የሚገኘውን መጋዝን ለማውደም ካሊበር በተባለ ከሩዝ ሚሳዔል መጠቀሙንም የኢንትራፋክስ ዘገባ ያመለክታል። በተጨማሪም የሩስያ ሃይሎችም ሶስት የዩክሬን SU-25 ተዋጊ ጄቶችን በምስራቅ ዩክሬን ዶኔትስክ እና ካርኪቭ አቅራቢያ መትተው መጣላቸውን የሩሲያ መከለከያ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።
T.me/ethio_mereja
@ethio_mereja
15.1K viewsedited  13:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ