Get Mystery Box with random crypto!

ደሴ ምንድነው የሆነው? በደሴ ከተማ አስተዳደር በቧንቧውሀ ክፍለ ከተማ 4ኛ ፓሊስ ጣቢያ በነፍስ | ETHIO-MEREJA®

ደሴ ምንድነው የሆነው?

በደሴ ከተማ አስተዳደር በቧንቧውሀ ክፍለ ከተማ 4ኛ ፓሊስ ጣቢያ በነፍስ መጣፋት ተፈላጊ የነበሩ ግለሰቦች በምርመራ ክፍል ውስጥ በጣሉት ቦንብ የ5 ሰዎች ሂወት አለፈ!!

መነሻቸውን ከደሴ ዙሪያ ወረዳ ፅድ ገበያ አካባቢ ያደረጉ በነፍስ ማጥፋት ወንጀል ሲፈለጉ የነበሩ እና ተፈላጊ ወንጀለኞች የ25 ዓመት ፍርደኛ የነበሩ 4 ሽፍቶች ወደ ደሴ ከተማ አስተዳደር በመግባት የተለያዩ ጥፋቶችን ለመሰንዘር አቅደው የገቡ ቢሆንም እነዚህን ወንጀለኞች በደሴ ከተማ አስተዳደር እና በደቡብ ወሎ ፓሊስ ጥመረት ከቀኑ 10:00 አካባቢ ተይዘው ወደ 4ኛ ፓሊስ ጣቢያ ለምርመራ እንዲገቡ ተደርጓል ።

በዚህ ሂደት ውስጥ በወንጀል ሲፈለጉ የነበሩትን 4 ሽፍቶች የያዛችሁትን ትጥቅ አውርዱ የሚል ከፓሊስ የተሰጣቸውን መመሪያ ባለመቀበል እና መመሪያውን በመተላለፍ የታጠቁትን ቦንብ አውጥተው በማፈንዳት ተፈላጊ ሽፍቶቹን ጨምሮ አንድ መደበኛ ፓሊስ እና ልዩ ሀይል በጥቅሉ የ5 ሰዎች ሂወት የጠፋ ሲሆን 1 ወንጀለኛ እጁን ሰጥቷል በማለት የደሴ ከተማ አስተዳደር ፓሊስ መምሪያ ሀላፊ ኮማንደር አሳምን ሙላት ለደሴ ከተማ አስተዳደር የኮሚኒዩኬሽን መምሪያ አስታውቀዋል።
T.me/ethio_mereja
ኢትዮመረጃ