2022-06-15 01:50:46
#ጤናመረጃ
የአብሽ 10 የጤና ጥቅሞች!አብሽ ለጤና ምን ያህል ጠቃሚ እንደሆነ ያውቃሉ?
ለልብ ድካም፣ ለደም ግፊት፣ ኮሌስትሮል ለመቀነስ፣ ለጨጓራና በስካር በሽታ ለሚሰቃዩ ፍቱን መድሃኒት ነው::ገና ለወለዱ እናቶችም የጡታቸውን መጠን የተወሰነ ለመጨመር ይጠቅማል።
ጥቅሞቹ በዝርዝር ቀጥሎ ቀርበዋል፦
※
የስኳር በሽታን ለመቆጣጠር ይረዳል፦ አብሽ ደም ውስጥ የሚገኘውን የስኳር መጠን በመቆጣጠር ኢንሱሊን መቋቋምን ይቀንሳል።
※
የልብ በሽታን ያስወግዳል፦ የልብ ጉዳትን ለመከላከልና ኦክሲዳቲቭ ውጥረት ለማስወገድ ይረዳል።
※
የወር አበባ ቁርጥማትን ያስታግሳል፦ አብሽ ከቁርጥማት በተጨማሪ ራስ ምታት፣ ማቅለሽለሽና ድካምን ለመቀነስ ይረዳል።
※
የጡት ወተት ምርትን ያሻሽላል፦ አብሽን መጠጣት የወተት ምርትን የሚጨምር ውህድ ስላለው፤ ለሚያጠቡ እናቶች ይረዳል።
※
የምግብ መፍጨት ችግርን ይረዳል፦ የሆድ ድርቀትንና ከጨጓራ መቆጣት የተነሳ ለሚከሰት የምግብ መፍጨት ችግርን ለመከላከል ይረዳል።
※
የጸጉር መሳሳትን ለመከላከልና ለፀጉር እድገት ጠቃሚ ነው። የተፈጨ አብሽን ሳይወፍር በብርጭቆ ውሀ በማዋሀድ መቀባት።
※
አብሽ መጠጣት አቅም ማጣትን ለማከምና የወሲብ ችሎታን ለመጨመር ይረዳል።※
አብሽ መጠጣት ብጉርን ለመከላከል ይረዳል።※
ፀረ-እርጅና ጥቅም አለው፦ለቆዳችን አስደናቂ ጠቀሜታ ያለው ሲሆን የእርጅና ምልክትን እንደ የቆዳ መጨማደድና ቀጫጭን መስመርን ያስወግዳል።
※
ቆዳን ለማርጠብ፦ የአብሽ የሚሙለጨለጨው በሀሪ የደረቁ ቆዳዎችን በማስወገድ ቆዳችን እንዲረጥብ ይረዳናል።
አጠቃቀሙ፣ በ1 ብርጭቆ ውሃ ውስጥ 2 የሾርባ ማንኪያ ነው መጠጣት ያለብዎት። ተፈጥሯዊ ስለሆነ ምንም አይነት ጉዳት የለውም። ክብደት እንዳይጨምሩ በመጠኑ ይጠቀሙ።
ጠቃሚ ነውና ለወዳጆ ያካፍሉ! ሼር!
T.me/ethio_mereja
902 viewsedited 22:50