Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ ጦር ከሶማሊያ ለቆ እንዲወጣ አንፈልግም ሲሉ የሶማሊያ ፌደራል መንግስት አካል የሆኑት “ | ETHIO-MEREJA®

የኢትዮጵያ ጦር ከሶማሊያ ለቆ እንዲወጣ አንፈልግም ሲሉ የሶማሊያ ፌደራል መንግስት አካል የሆኑት “ጁባላንድ” እና “ደቡብ ምዕራብ” ግዛቶች ገለጹ

የሶማሊያ ፌደራል መንግስት አካል የሆኑት “ጁባላንድ” አስተዳደር እና “ደቡብ ምዕራብ” በሚል የሚጠራው የሶማሊያ ግዛት አስተዳደር የኢትዮጵያ ጦር ከሶማሊያ ለቆ እንዲወጣ እንደማይፈልጉ አስታወቁ።

የኢትዮጵያ ጦር ከሶማሊያ ለቆ መውጣት የተወሳሰበው የሶማሊያ የጸጥታ ሁኔታው ያባብሰዋል፣ አልሸባብ እንዲንሰራራ ያደርገዋል ሲሉ ግዛቶቹ ገልጸዋል። ሁኔታው በሀገሪቱ በሚገኙ ባለድርሻ አካላት ዘንድ ስምምነት ሊፈጠርበት የማይችል ነው ያሉት የጁባላንድ ምክትል ፕሬዝዳንት ሞሃሙድ ሰይድ አደን ውይይት ሊደረግበት ይገባል፤ ማንም በተናጠል ውሳኔ ሊያሳልፍ አይችልም ሲሉ አስታውቀዋል።

የደቡብ ምዕራብ ግዛት የጸጥታ ጉዳዮች ሚኒስትር በኤክስ (ትዊተር) ገጹ በሶማሊያ የሰላም ማስከበር ስራ በተሰማራው የአፍሪካ ጦር ሀይል ውስጥ የሚገኘው የኢትዮጵያ ጦር አስቸጋሪ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል ሲል ገልጾ ለአበርክቶው ምስጋና እናቀርባለን፣ የጦሩ ቆይታ ይቀጥላል፣ የድርሻውንም ይወጣል ሲል አወድሷል። የኢትዮጵያ ጦር ለቆ ይውጣ መባሉ አላስፈላጊ እና የተሳሳተ ምክር ሲል ተችቷል።

     T.me/ethio_mereja
           ኢትዮ-መረጃ