2022-06-13 23:17:22
#ጤናመረጃሙቅ ውሃ መጠጣት የሚያስገኛቸው የጤና ጥቅሞች!!በቂ ንፁህ ውሃ መጠጣት ለቆዳ፣ ለጡንቻና ለመገጣጠሚያ ክፍሎች ጤንነት ያለው ጥቅም የላቀ ነው። ውኃ የሰውነት ሕዋሳት ንጥረ ነገሮችን እንዲመገቡና በሽታን እንዲከላከሉም ይረዳቸዋል።
ሙቅ ውሃ መጠጣት ደግሞ ጤናን ለማሻሻል የሚረዳ ቀላል ዘዴ መሆኑ የተነገረ ሲሆን፥ ከሚያስገኛቸው ጠቀሜታዎች መካከል፦
1. ውሃን አሙቆ መጠቀም የሽንት ችግር እና ኪንታሮትን እና የሆድ በሽታን ከመከላከል ይረዳል በተጨማሪ
የሆድ ድርቀትን ይቀንሳል ሲሉ ባለሙያዎች ገልፀዋል።
2. ምግብ በሆዳችን ውስጥ ቶሎ እንደዲዋሃድ!
አንድ ሰው በቂ ውሃ ካልጠጣ ትንሹ አንጀት በምግብ እና በመጠጥ የሚወስደውን ፈሳሽ መጠቀምን ይመርጣል።
3. መርዛማ ነገሮችን ከሰውነት ለማስወገድ!!ጥናቶች ሙቅ ውሃ መጠጣት መርዛማ ነገሮችን ከሰውነታችን እንዲወገዱ ያግዛል። የሰውነት ሙቀት መጠን በመጨመር በላብ እንዲወጣ ያደርጋል።
4. የተሻለ የደም ዝውውር እንዲኖር!!
የሞቀ ውሃ መጠጣት የደም ቧንቧን ወይም ሥሮችን በማስፋት የደም ዝውውርን ያሻሽላል። ይህ ደግሞ ጡንቻዎች እንደፈለጉት እንዲንቀሳቀሱ እና ህመምን ለመቀነስ ይረዳል።
5. የሰውነት ክብደት ለመቀነስ!ሁል ጊዜ ውሃን መጠጣት ሰውነታችን ንጥረ ነገሮችን እንዲመገብ እና ውፍረት እንዲቀንስ ይረዳል።
6. የህመም ስሜት ይቀንሳል!
ለተጎዱ ጡንቻዎች የደም ዝውውርን እና ፍሰትን ያሻሽላል፤ የህመም ስሜታትን ሊቀንስ እንደሚችል ተረጋግጧል።
7. ጉንፋንን በመዋጋት የአፍንጫ ጤንነትን ያሻሽላል እንዲሁም የአፍንጫ መቆጣት ጫና ለመቀነስ ይረዳል።
8. ጭንቀትን ለመቀነስ:- የሞቀ ውሃ መጠቀም የአእምሮ ጭንቀት እና ውጥረት ይከላከላል።
ምንጭ፦ medicalnewstoday
ጠቃሚ ነውና ለወዳጆ ያካፍሉ! ሼር!
T.me/ethio_mereja
3.2K viewsedited 20:17