Get Mystery Box with random crypto!

ETHIO-MEREJA®

የሰርጥ አድራሻ: @ethio_mereja
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 130.68K
የሰርጥ መግለጫ

Addisababa, Ethiopia🇪🇹
News & Media Company®
.
USA : Washington
.
.
.
ለጥቆማ እና ማስታወቂያ ለማሰራት
ከታች ያለውን ሊንክ ይጠቀሙ!!
👉 @ethio_merejabot ✔

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 268

2022-06-12 14:42:54
የአማራ ክልል የወልቃይት ጉዳይ ለድርድር የማይቀርብ ቀይ መስመር መሆኑን ገለጸ!!

የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር) የወልቃይት ጉዳይ ለድርድር የማይቀርብ ቀይ መስመር መሆኑን አስታወቁ።

ርዕሰ መስተዳድሩ ይህንን ያሉት ዛሬ በጎንደር ከተማ ከህዝብ ጋር ባደረጉት ውይይት ላይ ነው።

"የወልቃይትን ጉዳይ ለድርድር የማናቀርበው ቀይ መስመራችን ነው" ያሉት የክልሉ ርዕሰ መንግስት የህዝብ አንድነት መጠናከር አለበት ብለዋል።መንግስት በሽብርተኝነት የፈረጀው ህወሃት የትግራይ ግዛት የነበሩ ቦታዎችን ማለትም ወልቃይትትን በማንኛውም አማራጭ እንደሚያስመልስ ከሰሞኑ መዛቱ ይታወሳል።የግንባሩ ቃል አቀባይ ጌታቸው ረዳ ህወሃት "ምዕራብ ትግራይ" በሚለውና ወልቃይት ጠገደ ተብሎ የሚጠራውን ቦታ በተመለከተ በቅርቡ የይገባኛል ጥያቄዎች በይፋ እንደሚያቀርቡ ቢገልፁም የአማራ ክልል ፕሬዝዳንት ግን በወልቃይት ድርድር እንደማያደርግ ገልጸዋል።

"የትግራይ መንግስት ያወጀው ዓላማና አቋም ነው፣ እያንዳንዱን ኢንች የትግራይን ግዛት በሚቻለው መንገድ ሁሉ በሰላማዊም ሆነ በሌላ አካሄድ ለማስመለስ ሁሉንም እናደርጋለን" ሲሉ አቶ ጌታቸው ገልጸው ነበር። ዶ/ር ይልቃል በጎንደር ከተማ ከህዝብ ጋር ባደረጉት ውይይት ላይ አክለውም፤ "አንዳችን ለአንዳችን አስፈላጊ መሆናችንን በመገንዘብ ሐይማኖትን ሽፋን በማድረግ ግጭት የሚቀሰቅሱ አካላትን ማጋለጥ ይገባል"ም ብለዋል ።
T.me/ethio_mereja
@ethio_mereja
16.0K viewsedited  11:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-12 12:52:04
ዘመናዊ የሆነው የመኖሪያ መንደር ዛሬ ተመርቋል።

ፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ያስተዋወቀበትን የገርጂ መኖሪያ መንደር ግንባታ ፕሮጀክትን አስመረቀ!!

የመኖሪያ መንደሩ በ 3 ሄክታር ይዞታ ላይ የተገነባ ሲሆን 510 ቤቶችን የያዙ16 ብሎክ ዘመናዊ አፓርትመንቶች ያሉት ነው።

የቤቶቹ የግንባታ ቴክኖሎጂ የአልሙኒየም ፎርም ዎርክ በመባል የሚታወቅ ሲሆን ከተለመደው የሕንጻ ግንባታ ለየት የሚያደርገው ጥራትን እና ፍጥነትን ያማከለ ብክነትን የሚቀንስ የአሰራር ስልት በመከተሉ ነው ፡፡

ቤቶቹን ገንብቶ ለማጠናቀቅ 1 ዓመት ከ6 ወራት ብቻ እንደወሰደ ተነግሯል።

የቤቶቹ ዓይነት የስካይ ቪላ ዱፕሌክስ እና የአፕርትመንት ቤቶችን ሲሆኑ ከ150 ካሬ ሜትር እስከ 500 ካሬ ሜትር ስፋት ያላቸው ናቸው።

የመኖሪያ መንደሩ ዘመናዊ የደህንነት ስርዓት የተገጠመለት፣ ከ800 በላይ ተሽከርካሪዎችን የመያዝ አቅም ያለው የመኪና ማቆሚያ ፣ የጋራ መጠቀሚያ አዳራሽ፣ ጂሚናዚየም፣ ካፌና ሬስቶራንት፣ የአረንጓዴ ቦታና መናፈሻ፣ አምፊ ቴአትር የያዘ ነው።

ከዚህ በተጨማሪ ዘመናዊ የቆሻሻ ማስወገጃ ፣ የስፖርት ሜዳ ፣ የልጆች መጫዎቻ ቦታና የመዋኛ ገንዳ እና ሌሎች አስፈላጊ ነገሮች አሟልቶ የያዘ ዘመናዊ መንደር ነው፡፡
T.me/ethio_mereja
@ethio_mereja
15.6K viewsedited  09:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-12 12:23:06
በአዲስ አበባ በጎርፍ የተወሰደው ህጻን እስካሁን አለመገኘቱ ተገለፀ!!

በአዲስ አበባ ከተማ አዲሱ ገበያ አካባቢ በሚገኘው ላዘሪስት ት/ ቤት ወንዝ ውስጥ የገባው ማርኮን ይገረም አለመገኘቱን የእሳት እና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ።

የአዲስ አባባ እሳትና የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የኮሙኒኬሽን ባለሙያ የሆኑት አቶ ንጋቱ ማሞ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ ንጋቱ ማሞ ለአል ዐይን እንዳሉት የኮሚሽኑ ሰራተኞች ፍለጋ ላይ ናቸው። ህጻኑ ከጠፋ አምስት ቀናት ቢቆጠሩም እስካሁን አለመገኘቱን አቶ ንጋቱ ገልጸዋል። በጎርፍ የተወሰደውን ማርኮን ይገረም አካል ለማግኘት ፍለጋው ቀጥሏል ብለዋል።

ህጻኑ ረቡዕ ዕለት ወንዝ ውስጥ የገባው።ዘንድሮ ትምህርትን "ሀ" ብሎ ሊጀምር በአዲስ አበባ አዲሱ ገበያ አካባቢ በሚገኘው ላዘሪስት ት/ ቤት የገባው ማርኮን ይገረም ባለፈው ረቡዕ ከት/ ቤት ሲወጣ ከት/ ቤቱ አጥር ውጭ ያለው ትቦ ውስጥ በመግባቱ በትቦ ውስጥ የነበረው የጎርፍ ውሃ ይዞት ሄዷል።

ቤተሰብ ቀብሮ እርም ማውጣት ቢፈልግም የ 4 አመቱ ልጅ አስክሬን ግን እስካሁን አልተገኘም።በት/ ቤቱ አካባቢ ካሉ ወንዞች ጀምሮ የአፍንጮ በር በቀበና በአቃቂ በአባ ሳሙኤልም ባሉ ወንዞች ጎረቤትና ዘመድ አዝማድ እንዲሁም የእሳት እና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ሰራተኞች ፍለጋ ማድረጋቸውን ቀጥለዋል።

ምንጭ ፣ አልአይን
T.me/ethio_mereja
@ethio_mereja
14.0K viewsedited  09:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-12 00:58:40
#ጤናመረጃ
ለቆዳ ላይ ችግር ሎሚን እንዴት እንጠቀም?

ሎሚን በመጠቀም ብቻ ባክቴሪያን በመግደል፥ የሚከሰት የቆዳ መቀረፍን፣ የተጎዳ ቦታ ህመም ማስታገስና ወደቀድሞ ይዞታው መመለስ፣ ጥርት ያለ ቆዳ እንዲኖር ማስቻልና በተፈጠረው ህመም ሳቢያ የተጎዳውን ቦታ በአግባቡ ማከም ያስችልዎታል።

እንዴት ማዘጋጀት ይቻላል?

1ኛ) 1ዱን ሎሚ ከ2 በመሰንጠቅ በንጹህ የብርጭቆ ውሃ ውስጥ ጨምቆ ማዘጋጀት፥ፊትዎን በሳሙና ታጥቦ ማድረቅ። ከዚያም በንጹህ ጥጥ በተጎዳው ቆዳ ላይ መቀባት፣ከ10 ደቂቃ በኋላ በንጹህ ውሃ መለቃለቅ፥ ይህን ህክምና በቀን 2 ጊዜ እስከሚሻለዎት ድረስ መደጋገም።

2ኛ) 1 የሾርባ ማንኪያ የሎሚ ጭማቂና 2 የሾርባ ማንኪያ ማርን በንጹህ ብርጭቆ በአግባቡ ማዋሃድና ለመቀላቀል ያህል ትንሽ ውሃ ጠብ ማድረግ። በመቀጠልም ውህዱን በንጹህ እጅ የቆዳ ክፍል ላይ መቀባትና ከ5 ደቂቃ በኋላ በንጹህ ውሃ በመለቃለቅ ማደራረቅ ይህንንም በቀን 1 ጊዜ ማድረግ።

3ኛ) መለስተኛ መጠን ያለው 1 የፈረንጅ ዱባና 1 ማንኪያ የሎሚ ጭማቂን ማዘጋጀት፥ የፈረንጅ ዱባውን በመላጥ በአነስተኛ መጠን ቆራርጦ ከሎሚ ጭማቂው ጋር ማዋሃድ። ውህዱን በተጎዳው ክፍል ላይ በመቀባት ለ20 ደቂቃ አቆይቶ በንጹህ ውሃ ተለቃልቆ ማድረቅ፥ ይህንን ደግሞ በቀን 1 ጊዜ ማድረግ።

4ኛ) 2 የሾርባ ማንኪያ የሎሚ ጭማቂና 1 እንቁላል ማዘጋጀት፥ እንቁላሉንና የሎሚ ጭማቂውን ቀላቅሎ በደንብ ማዋሃድ። ውህዱን ለ3 ቦታ በመክፈል በመቀባት ከ5-7 ደቂቃ ማቆየት። በንጹህ ውሃ ተለቃልቆ ማደራረቅና ከህመሙ እስከሚድኑ ድረስ በየቀኑ ይህን መደጋገም። ከላይ በተገለጸው መንገድ ሎሚን ከተለያዩ ነገሮች ጋር በመቀላቀል የቆዳ ላይ ሽፍታ እና መሰል ችግሮችን ማስወገድ ይቻላል።

ጠቃሚ ነውና ለወዳጆ ያካፍሉ! ሼር!
T.me/ethio_mereja
1.2K viewsedited  21:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-12 00:16:36
ኢትዮ ቴሌኮም የ1 ሰአት ገደብ የሌለው የሞባይል ኢንተርኔት ጥቅል ጨምሮ ሌሎች ቀለል ያሉ ገደብ የሌለው የጥቅል አገልግሎቶችን ለደንበኞች አቅርቧል!

12 ብር ከፍላቹ ለ1 ሰአት የፈለጋቹትን ያለ ገደብ ኢንተርኔት መጠቀም ትችላላችሁ፣
በተጨማሪም 35ብር ብቻ በመክፈል የ1ቀን ገደብ የሌለው የድምፅ ጥቅል እና
50 ብር በመክፈል ለ1 ቀን ገደብ የሌለው የሞባይል ኢንተርኔት አገልግሎት መጠቀም ትችላላችሁ። አገልግሎቱን በቴሌብር ፣ ማይ ኢቲዮቴሌ እና ኢትዮ ገበታ ላይ ታገኙታላችሁ።

T.me/ethio_mereja
1.9K viewsedited  21:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-11 23:37:13
ቪዲዮ ፎቶ

ያለምወርቅ - ወርቅ ልበሺ !

ወይ_ልምጣ_ወይ_ምጣን እጅን በአፍ በሚያስጭን ብቃት ዛሬ በፋና ላምሮት ላይ ተጫውተዋለች

ድምፃዊት ያለምወርቅ ጀንበሩ ዳኞችንም ሕዝብንም አሳምና አሸንፋለች!... እንኳን ደስ አለሽ !

የሙዚቀኛ ኤልያስ መልካ ድርሰት የሆነውንና ኤልያስ መልካ የራሱን ህይወት የገለፀበት ድምፃዊት መሰሉ ፋንታሁን የተጫወተችውን "#ወይ_ልምጣ_ወይ_ምጣ የተሰኘውን ሙዚቃ በተለመደው አስገራሚ ብቃት ተጫውታ ዳኞችን እና ተመልካቾችን በብቃቷ በእንባ አራጭታለች !

ድምፃዊት ያለምወርቅ ጀንበሩ ቀጣይ ለአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድርና አልበምሽን በጉጉት እንጠብቃለን! በርቺ ! ሼር!

ፋና ላምሮት አዳዲስ እና ምርጥ ድምፃዊያንን ለማውጣት የሚያደርገው ጥረት በጣም የሚበረታታ ነው። ብዙ እንጠብቃለን፣ ቀጥሉበት።
T.me/ethio_mereja
@ethio_mereja
2.8K viewsedited  20:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-11 23:24:58
የመንግስት ዩንቨርሲቲዎች በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት ውስጥ ከመንግስት ቁጥጥር ነጻ ሊሆኑ ነው!!

የመንግስት ዩንቨርሲቲዎች በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት ውስጥ ከመንግስት ቁጥጥር ነጻ እንደሚሆኑ ትምህርት ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

በኢትዮጵያ የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ነጻ ሆኖ የመመራት መብት የሚሰጥበት የውይይት መድረክ በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ነው።የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሰቲን ተከትሎ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ከሁለት እስከ አምስት ዓመት ባለው ጊዜ ውስጥ በሂደት ወደ ነጻ ዩኒቨርሰቲነት እንደሚቀየሩ ተናግረዋል።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከመንግስት ጣልቃ ገብነት ውጪ በመሆን ነጻ ተቋም እንዲሆን የተወሰነውም መንግስት ዩኒቨርሲቲዎችን በራስ ገዝ አስተዳደር እንዲተዳደሩ የሚያስችል ውሳኔ ማሳለፉን ተከትሎ መሆኑን ሚኒስትሩ አብራርተዋል፡፡በውይይት መድረኩ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ጣሳው ወልደሃና “የዩኒቨርሲቲዎች በነጻ የመመራት ፈተና እና እድል” በሚል የመነሻ ጽሁፍ አቅርበዋል፡፡

በጽሑፋቸውም ዓለም አቀፍ ተሞክሮዎች እንደሚያሳዩት ዩኒቨርሲቲዎች ነጻነታቸው ተጠብቆ የመምራት፣ ሰራተኛ የመቅጠር፣ተማሪን የመቀበል፣ ሃብት የማፍራትና የማስተዳደር፣ ከተቋማት ጋር በራስ ግንኙነትን በመፍጠር የሁለትዮሽ ስራን ማጠናከር፣ የራሳቸውን አቅም የሚፈቅደውን ደረጃዎችን ማውጣትና መሰል ተግባራትን መፈጸም እንደሚችሉ አስረድተዋል፡፡

በኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች ነጻ ባለመሆናቸው ምክንያት ይህን ሁሉ ማድረግ አይችሉም ያሉት ፕሮፌሰር ጣሳው፣ በዚህ ምክንያትም የሚጠበቅባቸውን ሃላፊነት በሚፈልጉት ፍጥነትና ጥራት ማከናወን አለመቻላቸውን ጠቁመዋል።
T.me/ethio_mereja
@ethio_mereja
3.2K viewsedited  20:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-11 22:02:53
ክርስቲያኖ ሮናልዶ ክሱን አሸነፈ !!

በ2009 በላስ ቬጋስ ሆቴል ሮናልዶ ሞዴሏን ካትሪን ማዮርጋን ደፍሯል በሚል ክስ ተከፍቶበት ነበር።

ሮናልዶ በዚህ ክስ ምክኒያት አሜሪካ መግባት እስኪከለከል ድረስ ደርሶ ነበር። ሮናልዶ በ2018 ይህ ክስ ሲቀርብበት የFIFA 18 ቪዲዮ ጌም ላይ ምስሉ እንዲጠፋ ተደርጓል፣ ናይክ ከሱ ጋር ያለውን ውል እስከ ማቋረጥ ደርሶ ነበር፣ ብዙ የግል ሽልማቶች በዚህ ምክኒያት እንዳያገኝ ተደርጓል።

የአሜሪካ ፍርድ ቤቱ ክሱን ሲከታተል ቆይቶ ዛሬ ውሳኔ አስተላልፏል።

ሮናልዶ ከወንጀሉ ንፁህ መሆኑ እና የሞዴሏ ካትሪን ያቀረበችው ክስ ከእውነት የራቀ መሆኑን አረጋግጧል።
T.me/ethio_mereja
@ethio_mereja
7.2K viewsedited  19:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-11 19:02:59
308 የሰብዓዊ እርዳታ የጫኑ ተሽከርካሪዎች በዚህ ሳምንት ትግራይ ክልል ገብተዋል ሲል የአለም ምግብ ፕሮግራም አስታወቀ

በዚህ ሳምንት ወደ ትግራይ ክልል 308 የሰብዓዊ እርዳታ የጫኑ ተሽከርካሪዎች መድረሳቸዉን የአለም ምግብ ፕሮግራም አስታዉቋል።

ይህም 800 ሺህ ለሚሆኑ ዜጎች ተደራሽ ይደረጋልም ብሏል በትዊተር ገጹ።በተመሳሳይም በአማራ እና አፋር ክልሎች በቀጣይ የምግብ አቅርቦቱን እንደሚጀምር የአለም ምግብ ፕሮግራም አስታዉቋል።
T.me/ethio_mereja
@ethio_mereja
12.4K viewsedited  16:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-11 14:53:43
ህወሓት "የትግራይ ግዛቶችን በሰላምም ሆነ በጦርነት እናስመልሳለን" ሲል ዛተ!

መንግስት በሽብርተኝነት የፈረጀው ህወሃት የትግራይ ግዛት የነበሩ ቦታዎች በማንኛውም አማራጭ እንደሚያስመልስ ዝቷል፡፡የህወሓት ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ ከሰሞኑ ድርድር ይደረጋል በተባለው ጉዳይ ላይ አስተያየት ሰጥተዋል። የኢትዮጵያ መንግስት በህግ ከሚፈልጋቸው የህወሓት አመራሮች መካከል አንዱ የሆኑት አቶ ጌታቸው በፈረንሳዩ ለሞንዴ ጋዜጣ ላይ ስለድርድር በተጻፈው ጹሑፍ ላይ ነው ሃሳብ የሰጡት።

ጋዜጣው ስማቸው ያልተገለፀ ዲፕሎማቶችን ጠቅሶ የትግራይ እና የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጥንቃቄ የተሞላበት ውይይት እንደሚያደርጉ ገለጾ ነበር። በተጨማሪም ህወሃት "ምዕራብ ትግራይ" እያለ የሚጠራቸውን አካባቢዎች ይገባኛል ማለቱን ትቷል ሲል ጋዜጣው ቢጽፍም አቶ ጌታቸው አልተውንም ብለዋል።

አቶ ጌታቸው በቅርቡ እነዚህን የይገባኛል ጥያቄዎች በይፋ እንደሚያቀርቡ ገልጸዋል። "የትግራይ መንግስት ያወጀው ዓላማና አቋም ነው፣ እያንዳንዱን ኢንች የትግራይን ግዛት በሚቻለው መንገድ ሁሉ በሰላማዊም ሆነ በሌላ አካሀድ ለማስመለስ ሁሉንም እናደርጋለን" ብለዋል።

መንግስትና ህወሃት በታንዛኒያ ሊደራደሩ ነው መባሉን ተከትሎ መንግስት የሠጠው ምላሽ የለም።ህወሓት ምዕራብ ትግራይ በሚል የሚጠራቸው ቦታዎች አሁን ላይ በአማራ ክልል የወልቃይት ጠገደ ሰቲት ዞን አካል ናቸው።ትግራይ እና አማራ ክልሎችን የሚያወዛግቡት ራያ እና ወልቃይት አሁንም የጭቅጭቅ እና የግጭት መንስኤ ሆነው ቀጥለዋል።

ከዚህ ቀደም ሲልም ራያና ወልቃይት የአማራ ክልል ግዛቶች ናቸው በሚል ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ ተቋቁሟል።ከ 2010 በፊት የነበረው የትግራይ ክልል መንግሥት ግን ጥያቄዎቹን ውድቅ ማድረጉ ይታወሳል።
T.me/ethio_mereja
@ethio_mereja
15.9K viewsedited  11:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ