Get Mystery Box with random crypto!

የአማራ ክልል የወልቃይት ጉዳይ ለድርድር የማይቀርብ ቀይ መስመር መሆኑን ገለጸ!! የአማራ ክልል | ETHIO-MEREJA®

የአማራ ክልል የወልቃይት ጉዳይ ለድርድር የማይቀርብ ቀይ መስመር መሆኑን ገለጸ!!

የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር) የወልቃይት ጉዳይ ለድርድር የማይቀርብ ቀይ መስመር መሆኑን አስታወቁ።

ርዕሰ መስተዳድሩ ይህንን ያሉት ዛሬ በጎንደር ከተማ ከህዝብ ጋር ባደረጉት ውይይት ላይ ነው።

"የወልቃይትን ጉዳይ ለድርድር የማናቀርበው ቀይ መስመራችን ነው" ያሉት የክልሉ ርዕሰ መንግስት የህዝብ አንድነት መጠናከር አለበት ብለዋል።መንግስት በሽብርተኝነት የፈረጀው ህወሃት የትግራይ ግዛት የነበሩ ቦታዎችን ማለትም ወልቃይትትን በማንኛውም አማራጭ እንደሚያስመልስ ከሰሞኑ መዛቱ ይታወሳል።የግንባሩ ቃል አቀባይ ጌታቸው ረዳ ህወሃት "ምዕራብ ትግራይ" በሚለውና ወልቃይት ጠገደ ተብሎ የሚጠራውን ቦታ በተመለከተ በቅርቡ የይገባኛል ጥያቄዎች በይፋ እንደሚያቀርቡ ቢገልፁም የአማራ ክልል ፕሬዝዳንት ግን በወልቃይት ድርድር እንደማያደርግ ገልጸዋል።

"የትግራይ መንግስት ያወጀው ዓላማና አቋም ነው፣ እያንዳንዱን ኢንች የትግራይን ግዛት በሚቻለው መንገድ ሁሉ በሰላማዊም ሆነ በሌላ አካሄድ ለማስመለስ ሁሉንም እናደርጋለን" ሲሉ አቶ ጌታቸው ገልጸው ነበር። ዶ/ር ይልቃል በጎንደር ከተማ ከህዝብ ጋር ባደረጉት ውይይት ላይ አክለውም፤ "አንዳችን ለአንዳችን አስፈላጊ መሆናችንን በመገንዘብ ሐይማኖትን ሽፋን በማድረግ ግጭት የሚቀሰቅሱ አካላትን ማጋለጥ ይገባል"ም ብለዋል ።
T.me/ethio_mereja
@ethio_mereja