Get Mystery Box with random crypto!

ሩሲያ ምእራባውያን ለዩክሬን የለገሱትን መሳሪያ የያዘ መጋዘን አወደመች!! ሩሲያ በዩክሬን ውስጥ | ETHIO-MEREJA®

ሩሲያ ምእራባውያን ለዩክሬን የለገሱትን መሳሪያ የያዘ መጋዘን አወደመች!!

ሩሲያ በዩክሬን ውስጥ የሚገኝ ግዙፍ ወታደራዊ መጋዘን ማውሟን የሀገሪቱ ጦር አስታውቋል።የሩሲያ ጦር ያወደመው መጋዝን ምእራባውያን ለዩክሬን የሰጡትን በርካታ የጦር መሳሪያው የያዘ መሆኑንም የሩሲያው ኢንትራፋክስ የዜና ኤጀንሲ አስነብቧል።

የሩሲያ ጦር በቴርኖፒል ክልል ውስጥ የሚገኘውን መጋዝን ለማውደም ካሊበር በተባለ ከሩዝ ሚሳዔል መጠቀሙንም የኢንትራፋክስ ዘገባ ያመለክታል። በተጨማሪም የሩስያ ሃይሎችም ሶስት የዩክሬን SU-25 ተዋጊ ጄቶችን በምስራቅ ዩክሬን ዶኔትስክ እና ካርኪቭ አቅራቢያ መትተው መጣላቸውን የሩሲያ መከለከያ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።
T.me/ethio_mereja
@ethio_mereja