Get Mystery Box with random crypto!

የመንግስት ዩንቨርሲቲዎች በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት ውስጥ ከመንግስት ቁጥጥር ነጻ ሊሆኑ ነው!! የ | ETHIO-MEREJA®

የመንግስት ዩንቨርሲቲዎች በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት ውስጥ ከመንግስት ቁጥጥር ነጻ ሊሆኑ ነው!!

የመንግስት ዩንቨርሲቲዎች በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት ውስጥ ከመንግስት ቁጥጥር ነጻ እንደሚሆኑ ትምህርት ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

በኢትዮጵያ የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ነጻ ሆኖ የመመራት መብት የሚሰጥበት የውይይት መድረክ በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ነው።የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሰቲን ተከትሎ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ከሁለት እስከ አምስት ዓመት ባለው ጊዜ ውስጥ በሂደት ወደ ነጻ ዩኒቨርሰቲነት እንደሚቀየሩ ተናግረዋል።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከመንግስት ጣልቃ ገብነት ውጪ በመሆን ነጻ ተቋም እንዲሆን የተወሰነውም መንግስት ዩኒቨርሲቲዎችን በራስ ገዝ አስተዳደር እንዲተዳደሩ የሚያስችል ውሳኔ ማሳለፉን ተከትሎ መሆኑን ሚኒስትሩ አብራርተዋል፡፡በውይይት መድረኩ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ጣሳው ወልደሃና “የዩኒቨርሲቲዎች በነጻ የመመራት ፈተና እና እድል” በሚል የመነሻ ጽሁፍ አቅርበዋል፡፡

በጽሑፋቸውም ዓለም አቀፍ ተሞክሮዎች እንደሚያሳዩት ዩኒቨርሲቲዎች ነጻነታቸው ተጠብቆ የመምራት፣ ሰራተኛ የመቅጠር፣ተማሪን የመቀበል፣ ሃብት የማፍራትና የማስተዳደር፣ ከተቋማት ጋር በራስ ግንኙነትን በመፍጠር የሁለትዮሽ ስራን ማጠናከር፣ የራሳቸውን አቅም የሚፈቅደውን ደረጃዎችን ማውጣትና መሰል ተግባራትን መፈጸም እንደሚችሉ አስረድተዋል፡፡

በኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች ነጻ ባለመሆናቸው ምክንያት ይህን ሁሉ ማድረግ አይችሉም ያሉት ፕሮፌሰር ጣሳው፣ በዚህ ምክንያትም የሚጠበቅባቸውን ሃላፊነት በሚፈልጉት ፍጥነትና ጥራት ማከናወን አለመቻላቸውን ጠቁመዋል።
T.me/ethio_mereja
@ethio_mereja