Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮጵያ የሶማሌላንድ መንግስት በበርበራ ወደብ ላይ የባለቤትነት መብትን አስመልክቶ ያስቀመጠውን ቅ | ETHIO-MEREJA®

ኢትዮጵያ የሶማሌላንድ መንግስት በበርበራ ወደብ ላይ የባለቤትነት መብትን አስመልክቶ ያስቀመጠውን ቅድመ ሁኔታ ማሟላት ባለመቻሏ በበርበራ ወደብ ላይ ያላትን የ19 በመቶ ድርሻዋን አጣች።

የሶማሌላንድ ገንዘብ ሚኒስቴር እንደገለጸው የኢትዮጵያ መንግስት ማሟላት የነበረበትን የባለቤትነት መስፈርቶች በጊዜው ባለሟሟላቱ ባለቤትነቱን ተነጥቋል። ሚኒስትሩ እንዳመለከቱት ከቅድመ-ሁኔታዎች አንዱ ለወደቡ ግንባታ የገንዘብ መዋጮ ሲሆን ኢትዮጵያ ይህን ማድረግ ሳትችል ቀርታለች ተብሏል።

በሌላ በኩል ሳምንታዊ መግለጫ የሰጡት አምባሳደር ዲና ሙፍቲ እንዳሉት የበርበራ ወደብን በተመለከተ መንግስት መረጃን እያጣራ ይገኛል ብለዋል፡፡ (ካፒታል)
T.me/ethio_mereja
@ethio_mereja