Get Mystery Box with random crypto!

በኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የተመራ የልዑካን ቡድን ቱርክ | ETHIO-MEREJA®

በኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የተመራ የልዑካን ቡድን ቱርክ ገባ

በኢፌዲሪ መከላከያ ሰራዊት ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የተመራ የልዑካን ቡድን በዛሬው ዕለት ቱርክ ገብቷል፡፡ ልዑካኑ የቱርክ መንግስት ባዘጋጀው ኢ ኤፍ ኢ ኤስ 2022 በተሰኘው ወታደራዊ ልምምድ ላይ ለመሳተፍ ነው ቱርክ የገቡት፡፡

ከዝግጅቱ ጎን ለጎን ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ከቱርክ አቻቸው ጄነራል ያሳር ጉለር ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ዙሪያ መምከራቸውን በቱርክ ከኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ በአቅም ግንባታና ወታደራዊ ድጋፎች ላይ በትብብር ለመስራት ስምምነት ላይ መድረሳቸውም ተመላክቷል፡፡
T.me/ethio_mereja
@ethio_mereja